Monday, June 16, 2014

በጭፍኑ የህዝብ ድምፅ የሆኑ ሚዲያዎችን መቃወም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን



በጭፍኑ የህዝብ ድምፅ የሆኑ ሚዲያዎችን መቃወም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን አውቆ የመተኛት ያህል ነው፡፡ እንዴ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች እኛ ስለምንፅፈውና ስለምናሰራጨው መረጃዎች ሁሉ የተቃውሞ ድምፅ ብቻ እንጅ ምክንያታዊ የሆኑ ገንቢ ወይም ደግሞ አንድ መልዕክት ያለው አውቆ ያጠፋን እንኳን 'አቦ ትክክል ነው እኮ ይህንን ያልኩት ሆን ብየ እኮ ነው' እንድትሉ አያደርጓችሁ፡፡
እንዴ አንዱ የሰጠውን አስተያየት እስቲ እንመልከት
ላይ ግብፅ በሳውዲአረቢያ እርዳታ ማለትም በሁለት ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ከሩሲያ የጦር መሳሪያ መግዛቷን ዘገብን፡፡ ዘገባው እንዲህ ይላል
……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
በቀርቡ ግብጽን በግዜያዊነት አየመሩ የሚገኙት ፊልድ ማርሻል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ሩሲያን እንደጎበኙ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ተዘግቧል:: በጉቡኝታቸውም ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላደሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል::

ጄኔራል አበዱል ፈታህ አል ሲሲ የሩሲያ ጉብኝታቸውም አላማ ግብጽ ከሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ እንድታገኝ ለማግባባት ነበር ይህም ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝታቸው ተሳክቶ ግብጽ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የመሳሪያ ግዥን ተፈራርማለች፡፡

እኔን ትኩረቴን የሳበው ነገር ግብጽ ከሩሲያ መሳሪያ ለመግዛት የተፈራረመችውን 2 ቢሊዮን ዶላር ባላይ ወጪ በሳውዲ አረቢያ መንግስት የሚሸፈን መሆኑን ነው፤፤
እነዚህ አረቦች በተለይ ሳውዲ አረቢያ በባለፈው የወገኔን የውንድሞቼን እህቶቼን ደም አፈሰሰች ገደለች ዛሬ ደሞ ከታሪካዊ የሀገሬ ጠላቶች ጋር በማበር መሳሪያ እንዲገዙ በገንዘብ ትደግፋለች ግብጽ ይህን ሁሉ ዝግጅት እምታደርገው ለማን ይመስላቹኋል?:

በኢንቨስተር በባለሀብት ስም ስንት የሳውዲ ዜጎች ሀገሬን ይቦጠቡጣሉ የዜጎችን ጉልበት ይበዘብዛሉ ይገኛሉ ፡፡
.……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
እንግዲህ ዘገባው ይህን ይመስላል፡፡ እናም ወይ ኮሜንት ባያደርጉ ምንም ባይናገሩ ጥሩ ነበር ልክ '…ወግህ አር ነው ልጄ' እንደተባለው ሰው ዝም ቢሉ ጥሩ ነበር፡፡ ዝም ብለው በጭፍኑ ማለት ስላለባቸው ብቻ አንዳንዶች ፈሪ ሌሎች ደግሞ ከግብፅ ከጠላታችን ጋር የምታብሩ ከሃዲዎች ናችሁ ይሉናል፡፡
እስቲ እንዲያው ማን ይሙት ከእኛ እና ከእነርሱ እጁን እና ህሊናውን ጨጓራው ውስጥ ከትቶ የሚጨማለቅ ማን ነው፡፡ ጨጓራ ውስጥ ከገቡ ደግሞ አንድም ምግብ መሆን ሌላም ፅዳጅ መሆን ነው፡፡ እነርሱ ግን ሙሉ በሙሉ ፅዳጅ ናቸው፡፡ ለምን ቢሉ ይህ መረጃ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅ መደረጉ ህዝቡ ነቅቶ ጠላቱን እንዲጠብቅ ነው የሚያደርገው ወይስ እንኳን ጠላት መጣ ብለው እንዲተኙ ነው የሚያደርግ፡፡
ፖለቲካ ሁሉም ሚስጥር አደለም ይህ ግን በዋናነትም ገሃድ ወጥቶ እንዲያውም መንግስት ህዝቡን ቢችል ጎኑ አድርጎ የኔነት የእኛነት ስሜት እንዲፈጠርበት ማድረግ ነበረበት፡፡ ግብፅ ምን ያህል ታሪካዊ ጠላታችን እንደሆነች ማስረዳት ያለበት ሰዓት ነው፡፡ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መሄድ እስካለበት ድረስ ይሄዳል፡፡ ነገር ግን ጫፉ ላይ ሲደርስ ሊያስቀድምም ይችላል፡፡
በመሰረቱ እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ግዴለሽ መሆኑ አግባብ አደለም፡፡ በቃ አባይ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው፡፡ እኔ አምርሬ የምታገለው ስርዓቱን እንጅ ሃገሪቱን ማን መራ ማን ገዛት በሚል አደለም፡፡
ነገር ግን ይህ መንግስት እንደምናውቀውና በርካታ ጊዜ እንደፃፍኩት በመሆኑና እያንዳንዳችን የራሱ የገዥው ደጋፊዎችም እንደምናውቀው አምባገነን በመሆኑ ስርዓቱ መቀየር አለበት በሚል ነው፡፡
ውሸታም ስርዓት ነው፡፡ ከሃዲ ስርዓት ነው፡፡ ነፍሰ እና ሰዎ በላ ስርዓት ነው፡፡ ለዚህም አምርሬ እታገለዋለው፡፡ ዜጎችን ያስራል ይገድላል ያሰቃያል ይገርፋል እናትን ከልጇ አባትን ከልጁ ወንድምን ከወንድምና እህቱ እህትንም እንዲሁ ፍቅረኛ ለይቶ የሚያጠፋ መንግስት ነው ስለዚህ ይህንን ስርዓት አጥብቄ እታገለዋለው እንጅ የአባይ ግድብማ እኮ የኔ ነው፡፡ በሉዓላዊነታችን ላይ የሚመጣንማ እናውቅበታለን እኔም ቃል እገባለው ይሄው በእውነተኛዋ ብዕሬ ስም እኔ የማልፈልገው ሃገር የሚቆርስን ሃገር የሚደፍርን ሃገር የሚያሰድብን ሃገር የሚክድን ሃገርን ሃገሬ ብሎ የማይጠራን ለነጭ የሚያጎበድድን ነው፡፡
የአባይ ግድብማ እኮ እንኳን ዛሬ ሁሉ ተጨርሶ በተገኘበትና ወደ ትግባር ብቻ በሚገባበት ሰዓት ያኔ ዲዛይኑ 15ኛው ክፍለዘመን ሃሳቡ ሲነሳና በአፄ ዳዊት ሲፀነስ ጀምሮ ሙሉ አሁን ያለውን ዲዛይኑን እስከተሰራበት እስከተጨረሰበትና በደርግ መንግስት በ1976 ዓ.ም በህንድ ውቅያኖስ በኩል ከጣሊያኑ ኩባንያ ጋር በተዋዋለው መሰረት ጥሬ ዕቃ ሲያስገባ በግብፅና ሱዳን ትብብር በሚሳየል እስከጋየበት ድረስም የኢትዮጵያ ህዝብማ በብሽቀትና ቁጭት አንዳንገበገበው ነው የሚኖር፡፡
ታዲያ ሃሳቡና ፅንሱ ከ500 ዓመታ በፊት የነበረው ታሪካዊ ህልማችን እውን ሲሆን ማን ይጠላል፡፡
በምንስ መልኩ ነው እኛ ከጠላት ጋር የምንወግን በምን መንገድ ነውስ እኛ የምንፈራው በምንስ መልኩ ነው ሰውነታችንን አልቀበል ያለ መንግስትን የምንገሰው፡፡
አንድ ቁርጥ ያለ ነገር ልንገራችሁ ለጭፍን ደጋፊዎች
እኔና መሰሎቼ ለአባይ ግድብ ፀር የሚሆንን ሃገር ከባበት ገብተን በአፍ ጢሙ ለመድፋት የምንታትረውን ያህልና እንጦረጦስ እንዲበላው ጠላታችን የምንፈልገውን ያህል ምንም ያድርግ ምን ይህንን ጋጠወጥ ስርዓትንም መብታችን ክብራችን ዳር ድንበራችን  እምነታችን ባህላችን ነክቷልና እንጦረጦስ እንዲገባ የማልፈነቅለው ድንጋይ የማልምሰው ጉድጓድ የለም!!!!!!!!
በቃ በቃ በቃን አቦ!!!
ስለዚህ ከገባችሁ እባካችሁን ትክክለኛ መረጃ የሚያደርስን ሁሉ ስም አታውጡለት፡፡ እባካችሁን ጨጓራችሁ ውስጥ ስለሰፋ ብቻ የተዘፈዘፈውን እጃችሁን አውጡትና ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ፡፡ እጃችሁን ከደሙ አፅዱት፡፡
እስቲ ህሊናችሁ ጋር መጀመሪያ ታረቁ፡፡ እስቲ  ሁላችሁም የገዥው ፓርቲ አባላት ደጋፊዎችም ሆናችሁ የትኛውም ስም ያላችሁ ሁሉ ራሳችሁን ይህንን ጥያቄ ጠይቁት

በእውን እኔ የምደግፈው ስርዓት ዲሞክራሲያዊ ነው ያሰራቸው የሚገርፋቸው በየሽንጉሪትና እስር ቤቱ የሚያጉራቸው የሚያሰቃያቸው የሚገድላቸው እቁብ የገባባቸው ሁሉ በትክክል ለሃገሪቱ ደህንነት ሲል ህዝቧ ደህንነት ሲል ለሉዓላዊነቷ ሲል ለአንድነቷ ሲል ለቤተሰቦቼ ሲል ለወገኖቼ ሲል ነው? አውን ለህዝቦች መብት መከበር ሲል ነውን? እውን እኔ ይህንን መንግስት እየደገፍኩ እያቀናው ነውን? በትክክል ይገባውን ወይስ እኔ ብቻ ስለተጠቀምኩ ነው? እኔ ለኔ ምንም የማይዘመደኝን የማይወዳጄኝን ይህንን ከበረሃም ይምጣ ከየት በምንም በዘር በቀለም በጎጥ በክልል በሃይማኖት ገለመሌ ሳላዳላ አገልግሎት እየሰጠሁት ነው?
ወዘተ…
ብላችሁ እስቲ ራሳችሁን ጠይቁትና ለሁሉም የሚገባውን መሆን ያለበትን መልስ አወንታዊ በሆነ መልስ ካገኛችሁ ቀጥሉ፡፡ ያለዚያ ማስተካከል ያለባችሁን አስተካክሉ ያለያም እኛን ተቀላቀሉ በግል ወይም በቡድን፡፡
ለዚህ መልስ አግኝቶ ከተገቢው ውጭ ህዝብ ላይና ሀገር ላይ በደል የሰራና ለበደሎች ሁሉ አባሪና ተባባሪ መሆን በዛኛውና በትክክለኛው በፍትሃዊው ህግ ከማስጠየቅ አያድንም፡፡ አያያያያያያድንም!!! አያድንም!!
እኛ የምንለው ይህንን ነው ህዝባችን ሃገራችን አትንኩ፡፡ ለህዝባችንና ለሀገራችን መልካምና ገንቢ የሆኑ ሃገራችንና ህዝባችንን አወንታዊ በሆነ መልኩ መገንባትና ማሳደግ የሚችሉ ተግባራትን እስካልሰራችሁ ድረስና ሃገራችን በዚህ ሰዓት መሆን ከሚገባት ደረጃ ካላደረሳችሁ እንጠይቃችኋልን እንጅ አባይማ አባይ ነው፡፡ ግብፅም ያው ግብፅ ናት ህዝቧም ለዚህ ያውቁበታል፡፡ እኛም መረጃ የማይደርሰውን ህዝባችንን እያደረስነው እንጅ እናንተ እንደምትሉት ፈርተንም ከሃዲ ሆነንም አደልም ፈሪም ከሃዲም እናንተ ናችሁ ለእውነት ሳይሆን ለሆዳችሁ አድራችሁ ለውሸታሙ እና ሽንታሙ መንግስታችሁ ያደራችሁ፡፡
እጃችሁን ከአቁማዳችሁና ኪሳችሁ እና ከጨጓራችሁ አውጥታችሁ ኑ!!!
ቸር እንሰንብት
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

No comments:

Post a Comment