Monday, June 16, 2014

…በመሰረቱ እኮ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ብዛት ያሕል እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነት የለውም፡፡



…በመሰረቱ እኮ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ብዛት ያሕል እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነት የለውም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የህዝብ ጥያቄዎችና የሚዲያ ወጎች ልክ እንደ አውሎ ንፋስ ይመስላሉ፡፡ አንድ ጉዳይ እንደተፈጠረ ሰበር ዜና ምናምን እያሉ ከማቅረብና ወጉን ከማውጋት ውጭ ቀጣይነት ያለውን ስራ ሲሰሩና በእቅድ መሰረት ሲያስኬዱት የሚታዩ መሪዎች አልታዩም፡፡
ቆይ ለምንድን ነው ተከታታይነት ያለው እርምጃ መንግስት ላይ ሰላማዊ በሚባለውም ሆነ በየትኛውም መንገድ አይወሰድም?? ለምሳሌ፡
አምቦ ላይ ሰባት ስዎችን የቀጠፈ ግጭት ተጠናቀቀ…ውጤት ሳይኖረው…ሳያበቃ
ሜዳወላቡ ላይ እንዲሁ…
ሃሮማያ ላይ እንዲሁ
ጎነደር ላይ እንዲሁ 8 ስዎችን ህይወት የቀጠፈ ግጭት
ጭልጋ ላይ እንዲሁ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ስዎችና ፌደራል ፖሊሶች የጦር አውሮፕላኖች እስኪያንዣብቡ ድረስ ጦርነት ሊባል የሚችል ግጭት የመንግስት ሃይሎችን ቁስለኛና ሙት ለማመላለስ ብቻ 11 አውቶቡሶች የተመላለሱበት እልቂት፡፡
መተማ ላይ 5 ስዎችን ያስጨረሰ ግጭት…ስለደከመኝ ከዚህ በላይ በቃኝ
ትግራይ ላይ ድጋፍ አለው ምናምን የሚባለው ዱሮ የቀረ ነው አሁን የትግራይ ህዝብን ድጋፍ ያጣው መንግስት እናም የትግራይ ህዝብ እውነቱን አውቆ ከኢትዮጵያዊያን እህት ወንድሞቹ ጋር አብሮ ህመማችን ህመማቸው ሆኖ በመታገል ላይ ናቸው ሟች በየስፍራው በድብቅም በግላጭም ቀጥሏል፡፡
ታዲያ አሁን ደግሞ ስድስት ኪሎ አራት ከሎ ጂማ ወዘተ ግጭት እና ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ በሌሎችም ሊቀጥል ነው እያሉ ከማስተጋባት በላይ አንድ መታሰብ ያለበት በተለይ ለተቃዋሚ አካላት ትግሉ ቀጣይ እንዲሆንንና የማያዳግም እርምጃ በመንግስትና ስርዓቱ ላይ ማምጣት የሚችልየትግል መስመር መዘርጋት አለበት አለያ ይሕ አረመኔ ስርዓትና መንግስት አንድ አንድ እያለ ሁላችን ለመፍጀት ጥይት  አያጣልንም!!
ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ንብረት ከማውደም እና ራሳችንን ከራሳችን ማለትም አንዱን ብሄር ከአንዱ ብሄር ሳንለይ ሁላችንም አማራው ኦሮሞው ትግሬው ሶማሌው ደቡቡ አዲስ አበባው አፋሩ ጉሙዙ ጋንቤላው ሁላችንም በአንድነት የአንዳችን ህመም ለአንዳችን የአንዳችን ቁስል ለአንዳችን ተሰምቶንና አሞን አንድ ላይ በህብረት መንቀሳቀስ አለብን ይሕን ለማድረግ ደግሞ ተቃዋሚ አካላት እና ድርጅቶች የራሳችሁን የሆነ መስመር ዘርግታችሁ ሁሉም ከተሞችና ሃገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ጥርት ያለ ተከታታይኘት ያለው ትል ማድረግ አለብን አለያ እስካሁን እንደቆየነው ለአንድ ቀን ጮኾና ሞቶ ለምንግስት ትልቅ የማምለጫ ቀዳዳ ከምንከፍትለት በስተቀር ምንም አይኘት ለውጥ ማምጣት አንችልም፡፡
ስለዚህ ተቃዋሚዎች እንደ ተቃዋሚ መስራት ያለብንን በእቅድና በመርህ በራዕይ አጅበን ሁሉንም አካላት የሚያሳትፍ ሃገራዊ ስሜትን ለመፍ\ጠር በሚችል የትግል መፈክር እንዲሁም ከሁሉንም ብሄሮች ላይ በአሁኑ ሰዓት እንደ ወረርሽን አለመግባባትን እና ዘረኝነትን እየፈጠሩ ያሉ ቃላትን ሳይቀር ችግሮችን መንጥራችሁ በማውጣት እና በመጣል አንድ እንድንሆን የሚያደርጉንን እውነታዎችና የትግል ስልቶች በመዘየድ ትግላችን ጫፍ አድርሱት እንላለን፡፡
ይሕን ወሳኝና ተቀጣጣይ የሆነ ለውጣዊ አብዮትን መፍጠር የሚችል ትግልን ለማጧጧፍ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ራሱን ከብሄርተኝነት ጠባብ አስተሳሰብ ራሱን ማንፃት የሚያስችለው ተራማጅና የሰለጠነ የአንድነት መንፈስ ውስጥ አስገብቶ የኦሮሞ ጉዳት የሁላችን ጉዳት የአማራ ጉዳት የሁላችን ጉዳት ትግራይ ጉዳት የሁላችን ጉዳት የሶማሌው የአፋሩ የጉሙዙ የጋምቤላውና የደቡቡ ጉዳት የሁላችን ጉዳት መሆኑን ብቻ የሚሰብክልንና የሚቀበልልን ተቃዋሚ ብቻ ነው የምንፈልገውና ሁላችሁም ተቃዋሚዎች ወደዚህ መስመር ለመግባት ቁረጡ፡፡
ትግል አቅጣጫ ከሌለው በስተቀር ለውጤት አይበቃም!!
ሁሉም የተቃዋሚውን ጎራ የተቀላቀላችሁ በሃላፊነት ደረጃ ላይ የምትገኙ አካላትና አንድነቷን የጠበቀችን ኢትዮጵያ ለምትሹ ሁሉ የተላለፈ ጥሪ ነው
1.      ራሳችሁን ከብሄርተኛ ጠባብ አስተሳሰብ አፅድታችሁ ተንቀሳቀሱ ሁላችሁም አንድ በላይ አንድ ጫፍ በታች አንድ ጫፍ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ አንድ ግልፅ ጉዳይ ማወቅ ያለባችሁ ከየትኛውም ብሄር ውስጥ የራሱ ያልሆነውን ብሄር ማንቋሸሽና መዋረድ ስራየ ብሎ የሚይዝ የአዕምሮ በሽተኛ ይጠፋል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ይህ የአዕምሮ በሽተኛነት ነው በስሜትም ቢፈፀም ስዕተት ነው፡፡ ሆኖም የተቃዋሚ አካላትና የተሰዳቢውም ይሑን የተዋራጁ ብሄር አባላት ይሕ የወያኔ ኢህአዴግና ጀሌዎቹ ሴራ ነውና ከመጤፍ ሳትቆጥሩ ስሜት ውስጥ ሳትገቡ እገሌ ዚህ ብሄር አባል እገሌ የተባለውን ብሄር እኮ ዋረደ ተሳደበ እንዲህ አለ ማለቱን ትተን ጉላችንም በአላማና እቅዳችን ብቻ ትግሎች ሁሉ ወደ ላይኛው ጫፋቸው ማምራት አለባቸው፡፡ ይህን የማድረዱና የማስደረጉ የማስፈፀሙ እና የመምራቱ ስራ የእናነተና የሚዲያው ተቋማት ስራ ነው፡፡
2.     ሁላችሁም ትግላችሁ ስርዓቱን ማስቀየር ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም የሚሻው ይህንን ነው በምን ጥናት ላይ ተመርኩዘህ ለምትሉኝ ደግሞ የምናየው ሁሉ ማስረጃም መረጃም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ስርዓትን መቀየር እንጅ የሚፈልገው ትግል ለኢህአዴግ አማራጭ መፍትሄ የሚሰጠውን አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲ የሚሆነውን አደለም፡፡
3.     ሁሉም የተቃዋሚ ድርጅት አካላት የትኛውንም ብሄር ብቻ እወክላለው ብሎ እጁን ለማውጣት ቢሞክር ከሚሊዮን ዓመታት በኋላም ቢሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሳካለት እንደማይችል ማወቅ አለበት፡፡ ይህ ሲባል ግን የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለመንካት ለምን ራሳቸውን በራሳቸው ተመራጮች አይወከክሉም የሚለውን ለመፃረር ሳይሆን ጫፋቸው አንድ ሆኖ ለሃገራችን አንድነት የሚበጅ እንጅ ለመገንጠል የሚሻ ለመበታተን አንዱን ካንዱ በማበላለጥ ላይ የተመሰረተ መርዝን የሚዘራ ርዕዮት መያዝ አይገባቸውም ለማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ብሄርን የሚወክል ፓርቲ ሲመሰረት ተጠሪነቱ ለአንድ ዋና የፖለቲካ ብሄራዊ ተቃዋሚ መሆን አለበት እንጅ ልዩነቶችን አስፍቶ ራሱን አጉል ሸቤ ውስጥ ከትቶ እኛንም የሚከተን መሆን የለበትም፡፡ ይህን ለማቻቻል እኮ ነው አሜሪካን ያህል ሃገር እስካሁን ሁለት ታላላቅ ፖለቲካል ፓርቲዎች ብቻ ያሏት፡፡
4.     የሚቋቋመው የፖለቲካ ብሄራዊ ፖለቲካ ፓርቲ ሁሉንም በምንም ላይ የተመሰረቱ ንዑሳን ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠቀለልልና ገዥ ሆነ መሆን ያለበትና አቅም ያለው መሆን አለበት፡፡ ይህ ፖለቲካ ፓርቲ የሚስማማባቸው ሁሉ ለሁሉም ከታች እስከላይ የሚያስማማ እንዲሆን የየራሱን ሚሰራ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ይህ ጠቅላይ ብሄራዊ ፓርቲ የሚያስተባብረው ሁሉም የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በሚገኙበት ቦታ ሁሉ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት የትግል ትልሞችን መዝራትና ማጨድ አለባቸው፡፡ ያኔ ቀጣይ ይሆናል የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ ስብስብ አድርጎ መግዛትና ማስተባበር ይቻላል፡፡ ያኔ ወደ ድል ጎዳና በቀላሉ ገብቶ ይህንን መሰሪ ስርዓት ድራሹን ማጥፋት ይቻላል፡፡ በመሰረቱ እኮ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ብዛት ያሕል እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነት የለውም፡፡ በእርግጥ ይህ ሁሉ እንደ አሸን የፈላ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ተቃዋሚ ሆኖ ላይሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ይልቅስ እዚህ መብዛትና መራባት ሴራ ውስጥ የኢህዴግ ከፋፍለህ ግዛ እቅድ እንዳለበት አያወላዳም፡፡
…ይቀጥላል!!!

No comments:

Post a Comment