ነፃ ነህ ይሉኛል እዳ በዳ ሆኜ
ሲጫነኝ ሲረግጠኝ
እያዩ ሲደፋኝ
ነፃ ነህ ይሉኛል
ዕዳ በዳ ስሆን
ቀንበሩ ሲከብደኝ…
……..
እህ ልበል እስቲ
እህ ልበል እስቲ
ለጫወታው ሁላ
ለአንዱ አንዱ
ነበር ዱሮማ ከለላ
ዱሮ ብርቅ ነበር
ሰውን ሰው ሲጠላ
አሁንማ ሆነ
አሁንማ ሆነ ሰውን ሰዎ በላ
ችግር ያስተማረው
የችግርን ድግሪ
ከአናቱ የጫነው
ና ውለቅ አልወልቅም
አልወርድልህ ያለው
የጭነቱ ድግሪ
የችግሩ ቆብ ነው
እያሉ መተረክ
እንደአዲስ ሆነና
ከላይ ተቀምጦ
ና በለው ሆነና
በልማ ንገረው
አንተ የማን ልጅ ነህ
ማን ማንንስ
ቢወልድ አንተ ሆንክ ሆነና
ኧረ ከወዴት
ነህ አስቲ በስተየት
የወዳጄ አያት
ብለው ሲጠይቀኝ
ልቤ ዛል ብሎ
ውድቅ ያለ መስሎኝ
ድርጭ ድርጭ
ሲል በላየ ላይ ውሃ ላብ ጥምቅ ሲያደርገኝ
ድንገት አንድ
ወንበዴ በልቤ በር ገብቶ
ይሕን ሽማግሌ
ይህን አንቶ ፎንቶ
በል ያዝ እንዲህ
በለው ሳያርፈው ተኝቶ
ገለባ ተነፍሶ
መች ያውቅና አባባ
እዛው ከዱሩ
እንጅ መች ጎታ ሲገባ
ይሄውለወተኝ
አውነት ታሪክ ሆኖ በብዕር ሲቀባ
ገና ዱሮ ዱሮ
ያኔ ልጅ እያሉ
ዱብ ዱብ ጉም
ጉም ዝልል ዝልል ሲሉ
ምንም ባልወለድ
ምንም ባልታሰብ ከነአካቴው ሁሉ
ያኔ ወጣት ሆነው
ያረጉትን የሰሩትን ሙሉ
አስታውሰዋለው
ገና ሳልወለድ ስዎች ልጅ እያሉ
እርስዎ አባብየ
ሚሉኝን ወሬ የሚተርኩትን
ምንም ባልኖር
ያኜ ባንቀመጥ አብረን
በታሪክ እውነታ
በታሪክ ምስክር
መስታዎት ገዥቼ…መልኬን
ባላየውም ምን ያህል እንዳምር
No comments:
Post a Comment