የትኛውም ክልል
የኢት\ዮጵያ መሬት ለመኖር ኢትዮጵያዊነት በቂ ነው!!! የትኛውም ክልል ውስጥ ለመኖር ኢትዮጵያዊ የሚል መታወቂያ መያዝ በቂ ነው፡፡
ኧረ ተወውውውውውወወውውውውው!!! ስንት አስር ሽህ በኢንቨስትመንት ስም ኢትዮጵያዊያን ያላገኙትን መሬት አሟጠው የያዙ የውጭ ዜጎች
ሞልተው አደለም እንዴ ወገኖቻችን በአረብ ሃገራት ከፎቅ የሚወረውሩ በጩቤ ዘላዝለው የሚገድሉ አረቦች እና የውጭ ሃገር ዜጎች በሞሉበትና
መብታቸው ተከብሮ ተንደላቅቀው የሚኖሩባትን ሃገር እንዴት ንፁህ ኢትዮጵያዊያን እንዳይኖሩበት ይከልከሉ፡፡
ይሕ ያለምንም
ማመንታት የኢህአዴግ ሴራ እንደሆነ ምን የሚያወላዳ አደለም!!!
የሰማያዊ ፓርቲ
ደጋፊና አባላት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የጋራ የሆነው ህዝብ ጋር እንዳይሰለፉ መከልከላቸውን በተመለከተ አቤቱታ ማቅረባቸው ለኢትዮጵያ
ህዝብ የፍረዱኝ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
የገፃችን አስተባባሪም
በሚመለከተው መልክ ለሚመለከተው አካል ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ጥረቱን ሲያደርግ ቢቆይም ባልተጠበቀ መልክ ምንም እንኳን እስካሁን
አንድነት በልሳኑ በኩል ባያወጣም የአንድነት ምላሽ በሚመለስል መልክ የሚከተለወውን ምላሽ ማስተባበያ አቅርበዋል፡
“. . . . . . . . . . . እሁድ ቀን በተከሰተው የአንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጉዳይ ላይ . . . . . . . . . . በቅድሚያ እኔ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለውም። ፖለቲካውን በሚመለከት ግን በግሌ የማምንበትን ሀሳብ በማንኛውም ነገር ላይ እየሰጠው ነው። በጦርነትና በአቢዮትም ስለማላምን በሀገራችን ውስጥ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትንና የሚከተሉትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሙሉ እደግፋቸዋለው። ከእነዚህ ፓርቲዎች ውስጥ ሁለቱ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች ናቸው።
አጥብቀው የሚቃወሙትን የሚያስር፣ በእስር ቤት ቶርች የሚያደርግ፣ የሚያሳድድና ብሎም የሚገድል አምባገነን ፓርቲና መንግስት ባለበት ሀገር አንድነትንና ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሙሉ ሕይወታቸውን፣ ሥራቸውንና ቤተሰባቸውን ለአደጋ አጋልጠው እያደረጉ ያሉትን ሰላማዊና ሕጋዊ የፖለቲካ ትግል አደንቃለው። እደግፋለው። ለሁሉም ትልቅ አክብሮት አለኝ።
ወደ ጉዳዩ ስመጣ ባለፈው እሁድ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ ሄደው “አንድነት ፓርቲ ከለከለን” በሚል የተወሰኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሰጡትን አስተያየትና ቅሬታ ተከትሎ አንዳንዶች አንድነት ፓርቲን ሲወቅሱ አይቻለው። የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም በተደጋጋሚ ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን ፖስት ሲያድርጉ ነበር። በአንዳንዶቹ ፖስት ላይም ነገሩን ከመደጋገም ይልቅ ወደራሳቸው እንዲመለከቱና ነገሩን ትተው ወደፊት እንዲሄዱ የግሌን ሀሳብ ሰጥቻቸዋለው። ነገር ግን አንዳንዶች ሰማያዊዎችን ከመደግፍ አልፈው አንድነት ትልቅ ወንጀል የሰራ አስመስለው ሲጽፉ ስላየው የራሴን አስተያየት መስጠት ፈለኩኝ። በእኔ እምነት ጉዳዩ የዚህን ያህል ቅሬታ የሚፈጥርና የሚጋነን ነገር አልነበረም። የሁለቱን ፓርቲዎች ያለፈ ግንኙነትና አካሄድ የሚያውቅ ሰው አንድነትን ሊወቀሰው አይችልም። ከሚከተሉት ነጥቦችም ተነስቼ አንድነት ፓርቲ ሊወቀስ አይገባም እላለው።
1.አንድን ሰላማዊ ሰልፍ ሁለት ፓርቲዎች በጋራ ለማድረግ ካሰቡ አስቀድመው በጋራ ተስማምተውና ወስነው ማስቀመጥ አለባቸው። በዚህ በኩል በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል በትክክለኛ አካሄድ/formally/ የተደረግ ስምምነት የለም።
2.በሚመለከተው የመንግስት አካልም ሕግን ተከትሎ ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና የተሰጠው ለአንድነት ፓርቲ እንጂ ለሁለቱም ፕርቲዎች አይደለም። ስለሆነም ከሰልፉ ጋር ተያይዞ በሰልፉ ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ተጠያቂነት ቢመጣ የሚጠየቀው አንድነት ፓርቲ ነው።
3. ሰልፉን የጠራው አንድነት ፓርቲ እስከሆነ ድረስ በሰልፉ ላይ የሚሳተፍ ሁሉ ሰልፉን የጠራው አካል በሚለው መልኩ ነው መሳተፍ ያለበት። ለሁሉም ዜጋ ክፍት ነውና በሰልፉ ላይ እኔ እንደፈለኩኝ እሆናለው ብለን ልንቀሳቀስ አንችልም። ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ሥርዓትና አካሄደ አለው።
4. የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ የወሰኑት ሰልፉ እሁድ ሊካሄድ ቅዳሜ ቀን ነው። አንድነት ፓርቲ ግን ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የወሰነውና ያስታወቀው ከአንድ ወር በፊት ነው። በዚህ መሀል ሰማያዊ ፓርቲ እራሱ የጠራውን ሰልፍ አካሂዷል። እናም የአሁኑ ሰልፍ ላይ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ለመሳተፍ የዚህን ይህል ጥብቅ ፋላጎት ከነበራቸው በእኔ እምነት አንድነት ከእነሱ በፊት ሰላማዊ ሰልፍ እንደጠራ ያውቁ ስለነበር እነሱ መሀል ላይ ሌላ ሰልፍ ከመጥራት አብረው ይሄንን ሰልፍ በጋራ ማካሄድ ይችሉ ነበር።
5.ሰልፉን ለመሳተፍ የሄድነው እንደማንኛውም ዜጋ ነው ካሉ ደግሞ ሰልፉን የጠራው አንድነት መሆኑ እየታወቀ ሰማያዊ ፓርቲን የሚወክልና የሚገልጽ ነገር ይዞ ለመሳተፍ ለምን አስፈለገ? በሰልፉ ላይ የተገኙት ሙሉ ለሙሉ በሰልፉ ላይ የተዘጋጀውን አጀንዳ ለማስተጋባት ከሆነ የተወሰኑት የአንድነት አመራር አባላትም ቲ-ሸርቱን አውልቃችሁ ነው መሳትፍ የምትችሉት ሲሏቸው ነገሩን በመቀበል የሰማያዊ ፓርቲን ቲ-ሸርት አውልቆ ለመሳተፍ ለምን ከበዳቸው? ሰልፉ ላይ የተገኙት ሰማያዊ ፓርቲም በሰልፉ ላይ ነበር እንዲባል ካልፈለጉ በቀር ቲ-ሸርቱን አውልቆ መሳተፍ በጣም ቀላል ነበር።
6.ሰልፉ ላይ እንደ ማንኛውም ዜጋ እንዳንሳተፍ ተከለከልን የሚል ቅሬታ ሰልፉ ገና ሳይጠናቀቅ ነበር ፌስ ቡክ ላይ አንድነትን በመኮንን የተጀመረው። እንደ ማንኛውም ዜጋ ከሆነ ለመሳተፍ የፈለጉት ቅዳሜ ቀን እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች መወሰን አያስፈልጋቸውም ነበር። ሲቀጥል እንደ ዜጋ ከተከለከሉ ጉዳዩን የሰማያዊና የአንድነት ለማድረግ ለምን ይፈልጋሉ? የግልህን ጉዳይ በግልህ ትጨርሳልህ እንጂ የፓርቲ ጉዳይ አታደርግም።
7.ጉዳዩ የፓርቲ ከሆነ ደግሞ ሌላ ፓርቲ ላይ ያለህን ቅሬታ የምትገልጽበት ድርጅታዊ አሰራር አለ። እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት በደርጅቱ መዋቅር ውስጥ ያለው የሥራ አስፈጻሚ ወይም የምክር ቤት ወይም ሌላ አይነት አደረጃጀት በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት ተሰብስቦ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን መግለጫ ይሰጣል። ካልሆነ ግን እያንዳንዱ የፓርቲው አመራርም ሆነ አባል ከሌላ ፓርቲ ጋር ቅሬታ ውስጥ በገባ ቁጥር ብድግ እያለ በድርጅት ስም ቅሬታውን የሚያስተጋባ ከሆነ በምንም አይነት ሁኔታ ከሌሎች ፓርቲዎኛ ጋር ጤናማ ግንኙነት ሊኖረው አይችልም። ትክክለኛ አካሄድም አይደለም።
እኔ የሚጽፈው/የምናገረው ነገር እና አንድ የፓርቲ አመራር/አባል ከሚጽፈው ነገር ጋር እኩል ተጽዕኖና ውጤት አይኖረውም። ስለሆነም አንድ በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አመራር/ አባል ሆኖ የሚንቀሳቀስ ሰው ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ነገሮችን አይቶ ከስሜታዊነት በራቀ መልኩ ማስኬድ አለበት። አዎንታዊ ፉክክር ጥሩ ነው። አሉታዊ የሆነ ፉክክር ግን ትግሉን ይጎዳል ሕዝቡን ተስፋ ያስቆርጣል። አሉታዊ የሆነ ፉክክር የፓርቲዎቹን ጉልበት፣ ገንዘብና ጊዜ ያባክናል። ፓርቲዎቹን ደካማ አድርጎ ያስቀምጣቸዋል። በመጨረሻም የኢህአዴግን እድሜ ያራዝማል። ለወደፊቱም ቢሆን አሁን ከተከሰተው ነገር ትምህርት ተወስዶ ተመሳሳይ ነገር እንዳይከሰት ማድረጉ ጥሩ ነው። ሁለቱም ፓርቲዎች ያለፉትን ቅሬታዎች ቁጭ ብሎ በውይይት መፍታትና መዝጋት። የሚከተሉት ፕሮግራም ተመሳሳይነት እስካለው ድረስ ቢቻል በግልጽና በዝርዝር ተወያይቶ በመተማመን መዋሀድ ካልሆነም ተከባብሮ በጋራ መንቀሳቀስና መጏዝ። ከሁሉም በላይ ግን ከግል ስሜት ይልቅ ለጋራ ጉዳይ ቅድሚያ መስጠቱ የተሻለ ይመስለኛል።።”
ነፃ ነህ ይሉኛል እዳ በዳ ሆኜ
ሲጫነኝ ሲረግጠኝ
እያዩ ሲደፋኝ
ነፃ ነህ ይሉኛል
ዕዳ በዳ ስሆን
ቀንበሩ ሲከብደኝ…
No comments:
Post a Comment