ነፃነት ማለት ብቻን መኖር አደለም ነፃነት ማለት ከብዙዎች ጋር
ሆኖ ከአምባገነኖች በላይ መሆን ነው!! ነፃነት የቅኝ ግዛት አፀግብሮት እንደሆነ ብቻ አደልም መወሰድ ያለበት ነገር ግን ነፃነት ሲባል ስዎች መሆን የሚሹትን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሲፈፅሙና
ሲሆኑ ነው፡፡ ነፃነት መላላጥና መጋጋጥ አለው፡፡ ሞትም እስራትም አለው ነፃነት ማለት አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ካለበት ሁናቴ መላቀቅ
ነው፡፡ ነፃነት ማለት ከባርነት መውጣት ብቻ አደለም ያለባርነት ነፃነት ማጣት አለ፡፡ ነፃነት የሰው ልጅ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እንዲሰራ
ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እንዲኖር እንዲሻሻል እና ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ በሙሉ መተማማን እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡
ማንም የምታደርጉትን እደትሰሩ ቢያስገድዳችሁና የመመሪያና መስሪያ
ደንብ ጓጓታ ቢያስቀምጥ አላማው ባይሖንም ቢሆንም ጫፉ ነፃነት ማጣት ነው ስለዚህ ነፃነት ማለት ከእነዚህ ጓጓታዎች ነፃ መሆን ነው፡፡
ነፃነት በሚሊዮኖች መሃል በራስ መስመር መሄድ ራስን ማሰብ የራስን መስራት የራስን መኖር ነው ነገር ግን የሌሎችን ማንነት ለምንነትና
በምንነት በማይነካ ሰንሰለት መታሰር አለበት ይህ ሰንሰለት ደግሞ አርቴፊሻል ዲሞክራሲና ተፈጥሯዊ ዲሞክራሲ ናቸው፡፡
ማንም ሰው ነፃነቱን ማጣቱን ለማወቅ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር
የሚሰማውን ሁሉ ሚያደርገውን እንዲያደርግ ሚፈቀድለትና የሚከለከለውን ሁሉ አስቦ የጎደለውን ማዳመጥ ብቻ በቂ ነው…የሚፈልገውንና
እያገኘ ያለውን ማወዳደር ማገናዘብ ነው፡፡ ከገቢ አንፃር አደለም ነገር ግን ኑሮውን ለማሸነፍም ሊሆን ይችላል፤ አስተሳሰቡን ለመተግበርም
ሊሆን ይችላል አስተሳሰቡን ለማራመድም ይሁን ለማስሮጥ ሊሆን ይችላል፡፡
እነዚህን እሳቤዎቼን ተግባራዊ ለማድረግ የሚገታኝ አለ ወይ ብሎ
ጠይቆ ካሉ ነፃነት የለውም፡፡ ነፃነት ፍፁም ነው አደለም ለሚለው መልስ ለመሻት ነፃነት ተፈፅሯዊ ሲሆን ፍፁም ነው ካልሆነ አደለም፡፡
የሰው ልጅ ፍፁም አያደርገውም ተፈፅሮ ግን ፍፁም ታደርገዋለች፡፡ በእኔ እምነትም ተፈጥሯዊ ዲሞክራሲ እንደሚሻል መፃፌ ትክክል ይመስለኛል
ነገር ግን የኣለም መንግስታት አንድም ሳይቀር ይህንን ዲሞክራሲያዊ እሳቤ ተግባራዊ ማድረግ አይፈልጉም ምክንያቱም የትኛውም መንግስት
ዓለም ላይ ያለ አርቴፊሻሊ እንጅ በስምምነት እንጅ ዲሞክራሲያዊ አደለም፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት በህይወት ኖረው ስልጣናቸውን በምንም መልኩ
ለህዝብ ለማስረከብ ፈቃደኛ ከማይሆኑበት ምክንያት ውስጥ ወደ ስልጣን የሚመጣው አካል አንዱ ወደ ዘብጥያ ሊያወርዳቸው ወይም የሞት
ፍርድን ሊያከናንባቸው እንደሚችል ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ምክንያቱም ህዝብና ሃገር ላይ የሰሩትን ግፍ እነርሱ የሰሩትን ያህል ህዝብ
የሚያውቅባቸው ስለሚመስላቸው ነው፡፡
በመሆኑም ባለስልጣናቱ አንድም እድሜያቸውን ሙሉ በፌደራል ፖሊስ
ጫንቃና ጭካኔ፤ በወታደሩ ሚናና በልዩና አጋዚ እንዲሁም አጠቃላይ የፀጥታና ጦር ሃይሉ ህዝብ ጋር መበላላትና መፋጀት እንዲሁም አንዱን
ብሄር ከአንዱ ብሄር ጋር በማባላት አንድም የስልጣን እድሜያቸውን እና ሃብት ማሸሻቸውን ጊዜ ሲያራዝሙ ሁለትም የህዝብን ቅጣት አይናቸው
እያየ ከመቀበልና ከመታሰር ከመሞት ስንጋተት ዕድሜያችን ነውና በፈጣሪ እንሞታለን መለስ ወደፍዳ ዘምን አለመቅረቡን ምን ያህል እንደታደለ
እያሰቡ ነው፡፡
ካልሆነም እነርሱ ህዝቡን እንደጠላት በማየታቸው ስልጣናቸውን በሰላም
ማስረከብ ለጠላት እጅን የምስጠት ያህል እንኳን አቅልለው አያዩትም ህዝብ በእነርሱ ቤት ከጠላታቸው በላይ ነው ውስጣቸው በስጋት
የተሞላና እጃቸው ላይ የጠፉ ነፍሳት ደመከልብ ስላደረጋቸው ስለዚህ በሰላም ከሚለቁ ራሳቸውን ቢሚያጠፉ ምንኛ ደስ እንደሚላቸው መገመት
አያዳግትም!!!
የፍርድ ቀን ግን መድረሷ አይቀርም እኛም እጃችን በካቴና እስኪታሰር
ድረስ መጮሃችን አናቆምም!! አንድ የድረገፅ አክቲቪስት ቢያንስ ለተከታታይ አራትና አምስት ቀናት ኦንላይን መሆን ካቆመ…ወይም ፅሁፎችን
ከመፃፍና ከመለጠፍ ከተለየ አንድም ተገድሏል አለያም ታስሯል፡፡ በመሆኑም ሁላችንም ፎሎው የምናደርጋቸው ወይም የምንከተላቸው ገፆች
ለምሳሌ፡ እንደ minilik salsawi, Ethiopian
politicshttps://www.facebook.com/pages/Ethiopian-Politics/623214127716880?hc_location=timeline, https://www.facebook.com/gezahegn.abebe.33?fref=nf, https://www.facebook.com/Zehabesha?fref=nf,Abrha desta, https://www.facebook.com/hune.abyssiniawi, https://www.facebook.com/ethiopia.mitmita?fref=nf, https://www.facebook.com/samsson.dechassa,
ሌሎችም የነፃነት ታጋዮቻችን ቢበዛ ከሶስት ቀናት በላይ ኦንላይን
ሆነው ፅሁፎችን ማውጣት ካልቻሉ
1.
ከሃገር ወጥተዋል
2.
ታስረዋል
3.
ተገድለዋል
ስለዚህ ሁሉም እነዚህና ሌሎችም የት እንደገቡ ጥያቄውን መቀጠል
አለበት፡፡ ይህ ዘግናኝና ግፈኛ ገንጣይ አስገንጣይ ስርዓት መፈናፈኛ ማጣት ዜጎችን ማሰር መግደል ማሰደድ ማቆም አለበት፡፡
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር
በአብቢን ተፃፈ
No comments:
Post a Comment