Monday, June 16, 2014

መልካም የእርቅና ይቅርታ የአንድነትና መተባባር ዘመን ከዚች ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ ያድርግልን!!! ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር



አዎ እናውቃለን ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊያን አማርኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ብቻ በተወሰኑ የኦሮሚያ ክልል ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እየሞቱ እየተገደሉ ነው፡፡ አዎ ንብረታቸው እየተዘረፈ እየተቃጠለ እየነደደ ነው፡፡ አዎ በቆንጨራና በገጀራ እንዲሁም እነ ሙሃመድ ጅዋር በሰበኩትና ባስተማሩት እንዲሁም ወያኜ ኢህአዴግ ባስያዘው ሜንጫ አማራዎች እየተጨፈጨፉ ነው፡፡
አዎ አማርኛ ተናጋሪ ወያኜ ፅንስስ እቅድ ነበርና በየቦታው እየተገፋ ነው አሁን ግን ቆርጦ መብቱን ለማስከበር ተነስቷልና አትስጉ ነገር ግን ቆርጦ ሊታገል የተነሳው በተሳሳተ የሴረኞች እቅድና ሴራ አማራ እንደ ጅብ እንደሚባላ አድርገው የሰበኩትን እንደ እነጃዋርና ጥገኞቻቸው እንዲሁም ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር በመሆን አምባገነኑን እና አሳሪ ገራፊ አገር ገንጣይ አስገንጣይ የሆነውን የአማራን መውደም የሚፈልገውን እንዲሁም የሚገድል ዳር ድንበርን ቆርሶ ለባዕድ የሚሸጠውን ገድሎ አፋልጉኝ የሚለውን ደሃውን እያፈናቀለ መሬቱን ለባለሃብት እየቸበቸበ የየራሱን የሚያጋብሰውን ኢህአዴግና ጀሌ የብሄር ድርጅቶችን እንጅ እኛ የአማራ ህዝቦች ያላወቁትን የተሳሳቱትን የኦሮሚያ ህዝብ አባላት መክረን ዘክረን እናስረዳቸዋለን እንወያያለን ኢህአዴግን እንዴት እንደምንገረስሰው እንነጋገራለን እንጅ በወያኜና ካድሬዎቹ የስልጣን እድሜ ማቆያ ሴራማ አንፋጅም፡፡
ለውድ የኦሮሚያ ክልል አንዳንድ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ታሪኩ ሆነም አልሆነ ከስንት መቶ አመታት በፊት የሆነን ጉዳይ በማንሳት ለዛሬና ለወደፊት እንደማይጠቅመን እንደማይበጀን ብቀላም ሆነ ምን ለሃገራችንም ሆነ ለህዝባችን እንደማይበጀን እያወቃችሁ ስህተቱን ለምትሰሩ ሁሉ እግዚያብሄር እና የሁላችንም አምላክ አላህም ብንለው ከስተታችሁ ተምራችሁ በአንድ ላይ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶቻችን ጋር በመሆን የጋራ ጠላታችን ለዚህ የዳረገንን ወያኔ ኢህአዴግን ለማስወገድ ቆርጠን መነሳት አለብን፡፡
ይህን የማያደርግና የዘርና ሃይማኖት ግጭትን የሚሰብክ ሁሉ ግን ከወያኔ ካድሬነትና ከሰልጣን እድሜ ማራዘም ጥማት ከተጠናዎቸው እና ከነጃዋር ተከታዮችና የሰፈር ፖለቲካ አራማጆች እና ስሜታዊ የፖለቲካ እና ታሪክ ፍንዳታዎች ውጭ ማንም ስለማያደርግ ከእናንተ እራስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይወርድ ልናስረዳችሁ ይገባል፡፡
ጭንቅን ያልቀመሰ በሜዳ ሲፈረጥጥን የማየት ያሕል የሚያዝናና የለም፡፡ የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ እና ሌሎች ወንድሞቹ ጋር አንድ ላይ በመሆን በፍቅርና መተሳሰብ የኢትዮጵያን መከፋፈል ህዝቦቿ መጨራረስን የሚናፍቁትን አፈር ዱሜ ለማብላት ከሁልጊዜውም በላይ ዝግጁ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹን ግን በዘር በቀለም በሃይማኖት ገለመሌ ለማጥፋት አይታትርም፡፡ መቼም በአማራነት ታሪክ አስቦ አያውቅም አማራ ሁልጊዜም ሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ ላይ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ተከብሮና ተከብራ እንድትኖር ብቻ ደሙን ያፈሰሰ አጥንቱን የከሰከሰ ህዝብ እንጅ ሌሎችን በዘር በቀለም በቋንቋ በሃይማኖት ምናምን እየሰነጠቀ የራሱን እየበላ የሌሎችን ስቃይ እንደ ኮንሰርት ማለትም አሁን የወያኔ ባለስልጣናት እንደሚያደርጉት የሚያይ ህዝብ አደልም፡፡
ስለዚህ አሁንም አማራ ለኦሮሞ ወንድሞቹ እባካችሁን የወያኔን ሴራ ንቁበትና አንድ ላይ ሆነን ይህንን ድራሻችን ያጠፋውን ሃይል እናጥፋ አንድነታችን የሚበታትኑትን እንበትናቸው፡፡ ኑና ታግለን እናታግል ሲል ለሁሉም ኢትዮጵያዊያኝ አሁን ከወያኔ ኢህአዴግ ውጭ ማንም ጠላት እንደሌለው በመግለፅ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
አንድነቷ የጠጠበቀችና ዳር ድንበሯ የተጠበቀች ኢትዮጵያን ለማየት ያብቃን
መልካም የእርቅና ይቅርታ የአንድነትና መተባባር ዘመን ከዚች ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ ያድርግልን!!!
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር
በአብቢን

No comments:

Post a Comment