Monday, June 16, 2014

ያልተሳካውና መቸም ቢሆን የማይሳካው የጃዋርና አብዲ ፈቲ የፀረ-ሌሎች ብሄሮችና ፀረ ክርስትና እንቅስቃሴዎች…



ያልተሳካውና መቸም ቢሆን የማይሳካው የጃዋርና አብዲ ፈቲ የፀረ-ሌሎች ብሄሮችና ፀረ ክርስትና እንቅስቃሴዎች…
ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሁሉ ኢትዮጵየዊ ነው ነገር ግን ደማቸው አንድ የሆነውን ግንዳቸው አንድ የሆነውን ኢትዮጵያዊያን በመከፋፈል ስራ ላይ የሚሳተፉ ሶስት አካላት አሉ ምን ጥቅም እንደሚያገኙበት ባይገባና ምንም  እርባና ባይኖረውም፡፡ እነዚህ ሶስት የፀረ-የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞችና የተከፋፈለች የተበታተነች ኢትዮጵያን ከሚፈልጉት መካከል
1.      ህወሃት ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ሙሉ አባላትን ማለት ግን አይቻልም ለእንጄራ ብለው የገቡት ስለሚበልጡ
2.     ጃዋርና አብዲፈቲ እንዲሁም የቴሌቪዥን ጣቢያቸው ኦሮሞ ፈርስት  እንዲሁም ተገንጣይና አስገንጣይ አመለካከት ያላቸው ኦነግ አካላትና ሌሎችም የመገንጠል አላማ ያላቸው ሁሉ
3.     የወያኔ ሴራ ተጠቂ የሆነው ያላወቀው ዘረኛ እና ጎጠኛ ጥቂት ኢትዮጵያዊ ብሄርን መሰረት በማድረግ መጀመሪያ ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ባለማለት ይጀምሩና ሌሎች ከራሳቸው ብሄር ውጭ የሆኑትን ደግሞ እንደ ኢትዮጵያዊ በመቁጠር ማግለል የጀመሩና ይህንንም በማሰብ ላይ ያሉ፡፡ ብሄርን መሰረት ሃይማኖትን ቋንቋን መሰረት ባደረገ መልክ ከእምነታቸው ከብሄራቸው እንዲሁም እነርሱ ከሚናገሩት ቋንቋ ውጭ የሚናገሩት ሁሉ ጠላቶቻቸው እንደሆኑ የሚሰብኩ፡፡
ለእነዚህ ሴራ ሁሉ ማክሸፊያው  ሁለት ነው
1.      ወያኔን እና ስርዓቱን እስከመርዙ እንደእባብ ቀጥቅጦ ከስልጣኑ ብቻ ሳይሆን እስከ ገተቱ ድራሹን አጥፍቶ ዲሞክራሲያዊ ከህዝብና ለህዝብ በህዝብ የሆነ ስርዓትን ማቋቋም ለዚህ ደግሞ ከሰላማዊ ሰልፍ እስከ ህዝባዊ አመፅ እንዲሁም ከከተማ ትግል እስከ ትጥቅ ትግል ድረስ እንደ ትግል መስመር ማስመር
2.     የወያኔ ሴራ ተጠቂ ሆነው ይህ የወያኔ ቫይረስ ልባቸውን ደፍኖ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ያስጠላቻቸውን እንደ ሙሃመድ ጃዋርና አብዲ ፈቲ እንዲሁም ኮተቶቻቸው ኦሮሞ ፈርስትና የመገናኛ ጣቢያ ግንኙነቶችን ማቋረጥና ድራሻቸውን ማጥፋት!! ይህ ማሰሪያው የትኛውም ብሄር የትኛው ብሄር ላይ የሚያደርሰውን በደልና ግፍ የወያኔ ከፋፋይና አፋጅ ሴራ መሆኑን በመገንዘብ በትዕግስትና ብልጠት በተሞላበት ፍቅር አሰጣጥ ለአንዲት ሃጋራችን ኢትዮጵያና አንድነታችን ስንል ሴራዎቹን ሁሉ በፍቅር መሸኘትና…ልክ የሚይዙበትን ዘላቂ መፍትሄ መሻት ናቸው፡፡

የ ኦሮሞ ህዝብ ማንም እንደሚለው ክፋት ያለበት ህዝብ አደለም ይልቁንስ የኦሮሞ ህዝብ አብሮ መኖርን ልክ እንደሌሎች ህዝቦች ሁሉ ማስተማርና አብሮ መኖር የሚችል ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ችግር ያለባቸው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ትንሽ የነሙሃመድ ጃዋርና ወያኔ ኢህአዴግና የታሪክ ምሁር ነን ባዮቻቸው የፃፏቸውን መፅኃፍት በማንበብ የሚዘባጥሩ የኦሮሞ ህዝብ ስንት ምርጥ እና አንቱ የተባሉ ምሁራን እንደሌሉት ሁሉ አፋቸውን በየወረቀቱና በየቦታው የሚከፍቱ የወያኔ ተላላኪ ታሪከኞች በሚዘሩት መርዝና ቫይረስ የተለከፉና ሰፊና የተከበረውን ህዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ጋር ለማጋጨት የሚጥሩና አንድም ጥቅም ለሚሉት ዓላማ እንኳን ላያተርፉ የሚታትሩትን የሚሰሙ የኦሮሞ ብሄር አባላት መኖራቸው ሊገርም አይገባም፡፡
ሁሉም ብሄር ላይ ጎጠኛና ዘረኛ የሆነ አመለካከት ያላቸው በአንዲት ኢትዮጵያ የማያምኑ ግለሰቦች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም አሉ፡፡ ነገር ግን ትኩረት ሳንሰጣቸውና አላማችን ሳንዘነጋ አሁን ወደ ጋራ ጠላታችን ወያኔ ኢህአዴግን ወደ ማስወገድ ማተኮር አለብን፡፡ የድል ጊዜው ቀርቧል፡፡
ራሳችን እናዘጋጅ
ማንኛውም ትግል መስመር ተቀባይነት አለው መደራጀት ግን ግዴታ ነው በአንዲት ኢትዮጵያ ስም እና ጥላ ስር!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

No comments:

Post a Comment