Monday, June 16, 2014

ኢተዮጵያን ከወያኔ መንጋጋ ፈልቅቀን እናውጣ



ወንድሜ ጃዋር ሙሃመድ አንተ መስሎህ ከነበረው ስህተትህ ራስህን አርመህ ኢትዮጵያ ያውም የነፃነት ናፋቂዎች ባንዲራ ስር አንተን በማየቴ እጅግ ተደስቻለው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ የራስን ስዕተት አርሞ ወደ ብዙሃኑ መስመር ማዝገምን ያህል የሚያስደስት የለም፡፡ የተከበርከው ጃዋር ሙሃመድ አሁንም ቢሆን አስበሃቸው ከነበሩት ስታስባቸው ከነበሩት አሁንም ልታስባቸው ከነበሩት የመፈረካከስና ለአንድ ወገን ብቻ የሆነ አስተሳሰብህን እንጦረጦስ ከተህ ና ናልን ና እያልንህ ነውና የመፈረካከስ የመበታተን ለማንም ቢሆን አንዳችም ጥቅም የለውምና አብረን የጋራ ጠላታችን ወያኔ ኢህአዴግን እናጥፋ፡፡
በመሰረቱ እኛ ይሕንን መንግስታችን ሳናደርገው መንግስታችሁ ነን ያለንንን ወያኔን ባልተላፋነው ባልታገልነው ነበር ግን ህዝባችንና ሃገራችን ላይ እኔና አንተም ላይ ግፉ በዛና ህዝቡ የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰው የሚኖርበት አጣ ሰፊ ሃገር ኖሮት እያለ ሃገር እንደሌለው ምድር ላይ ሊኖር እንዳልተፈቀደለት ፍጡር በዱር በገደሉ የሚረግፈው ህዝብ የኔም ያኝተም የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ደም ነውና የሁላችን ወንድምና እህት ናቸውና ይህንን ለማስቆም ግዴታ ይህ አረመኔና የግፍ አገዛዝ ግብአከመሬቱ መፋጠን አለበት፡፡
ስለዚህ የሰፊውን የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ  ህዝብ ኢትዮጵያዊ ነውና ድምፅ ተቀላቅለህ የፈረካካሽ ውጥንክን አምክነህ በጣጥሰህ ላንተና ለቤተሰቦችህ መኖሪያ የመጨረሻ ማረፊያህ ለሆነቸው ምድር እንተባበርና ከጥፋትና ኪሳራ እናድናት፡፡ እመነኝ ጃዋር ሙሃመድ ታሪክን እያኘሱ ራስን የበለጠ ወደከፋ ጥፋት ከመውሰድና ሌሎችም እዲጠፉ ከማድረግ ያለፈውን መጥፎና ቆሻሻ ታሪክ እዳለ ተቀብሎ ከስዕተቱ ተምሮ ጠንካራ ጎኑን ወስዶ ለዚህ ህዝብ የሚበጀውን ማድረግ ይሻላል፡፡
ሴራና ተንኮል ለማሰብ ጭንቅላት ስለማይጠይቁ ቀላል ናቸው፡፡ የሚከብዱት የሚያደርሱት ኪሳራ ላይ ነው፡፡ ቂም በቀልን እንደመዝራት ቀላል የለም ምርቱ ግን ከባድ ነው፡፡ መከራና ስቃዩ ዋይታና ጩኸቱ እጅግ ይዘገንናል፡፡ ነገር ግን ይቅር ተባብሎ ቢያጠፉም ባያጠፉም ይቅር ተባብሎ ለዘመናት የኘበረ ክብርና ፍቅርን መልሶ በአንድነት ለመኖር የሚዘራውን መዝራት ልክ አሁን የነፃነት ታጋዮች እደሚፈትናቸው ቢፈትንም እንኳን ቂምና ጥላቻን ዘርቶ ምርቱን እደመሰብሰብ አይከብድም እንዲያውም ምርቱ እጅግ አትራፊና አስደሳች ነው እንጅ፡፡ ስለዚህ አሁን የጋራ ኢትዮጵያዊ ነፃነት ጥያቄና ትግል ዘሩን በመዝራት ቢከብድም እንኳን አንድነት ካለ አይከብድምና ትርፋማና የተሳካ በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ በፍቅርና አብሮነት ላይ የተመሰረተ ነፃነታችን እናውጅ፡፡
እርግጠኛ ነኝ ጃዋር ሙሃመድ በቅርብ ጊዜ ይሕንን ህዝብ አንድ ለማድረግና በአንድነት በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ተሰባስበው ለነፃነታቸው ከሚታገሉት መሃል አንዱ ሆነህ ኢህአዴግ ወያኜን ስታስጨንቁና አንድ ላይ ዘምራችሁ ስታስዘምሩ ይሰማኛል፡፡ ውድ ጃዋር አሁን እየሰራህ ባለኸው ወያኜ ተመችቶለታል ጥንት ጀምሮ የሚያስበው ዓላማው ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንድትኖር አይፈልግም፡፡ ጠንካራዋና ሃያሏ ኢትዮጵያ ራሷን ችላ እንድትኖር አይፈልግም፡፡
የዚህን እውነታ መንገር ደግሞ ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው
እዝነ ልቡናህን ይክፈትልህ ወዳጄ
ኢተዮጵያን ከወያኔ መንጋጋ ፈልቅቀን እናውጣ

No comments:

Post a Comment