Monday, June 16, 2014

ለማንኛውም በያላችሁበት የሚመለከታችሁም ሆነ አላፊ አግዳሚው ይህንን ማውገዝ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አደለም፡፡ ለዚህም መግለጫ ማውጣት ያሻችኋል፡፡



አሁን በዛ በዛ በዛ…የለቅሶ ሴቃ መስማት ሰለቸኝ አቦ…ለሁለት አካላት የመጨረሻ ጥሪ ለማሰማት ወስኛለው ይላል አማራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ለተሳሳተው ለወያኔ ላደረው ከላይ ከታች ማገናዘብ ላቃተው በጣት ለሚቆጠረው የወለጋ በተለይም ደምቢደሎ…ጊምቢ አካባቢ ለሚገኘው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ አክራሪ አላዋቂዎች ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ከአማራው ጋር ተጋብቶ ተዋልዶ ባለበት እውነት… እናንተ ለኢትዮጵያ ከምንጊዜም ጠላቷ ለኢትዮጵያ ህዝብ የምጊዜም ጠላት ለሆነው ወያኔ የመላላክ ያህልና እንዲሁም በባሰ የአማራ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ በደል እያደረሳችሁ እየገደላችሁ እየቆረጣችሁ ነው፡፡
ስለዚህ ስለዚህ!!! ጠላታችን የየትኛውም ኢትዮጵያዊ ጠላት አማራ ሳይሆን ትግሬ ሳይሆን ደቡብ ሶማሌ አፋር ጉሙዝ ጋምቤላ ወይም ማንም ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ወያኔ ነው እንጅ ማንም አደለም፡፡ ስለዚህ
1.      ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ይህን ለማውገዝና ጥፋተኛና የወያኔ ተላላኪዎችን እጅ ውስጥ አድርገህ ከጥፋታቸው እንዲታቀቡ ካልሆነም እርምጃ እንድትወስድ ስንል በሰፊው የአማራ ህዝብ ስም እንጠይቃለን
2.     ለጊዜውም ቢሆን በትረስልጣኑን ተቆናጥጠህ ያለኸው ወያኜ ኢህአዴግ ይሕ ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ ግዴታህ ብቻ ሳይሖን ባታደርግና የየትኛውም ብሄር ተወላጅ በፈለገው ቦታ ተንቀሳቅሶ ኢትዮጵያ ውስጥ የመስራት ንብረት የማፍራት መብት ስላለው መብትን ማስከበር ግዴታህን ባትወጣ ለእያንዳንዱ አማራ ሞት ምላሹን ከየትም ቦታ ቢሆን የፈጀውን ፈጅቶ እንደምትቀበል አትጠራጠር፡፡ የሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ከልጆቹን እንዲያርም እስከማስገደድ መሄድ አለብህ ኢህአዴግየ አለበለዚያ…የሚወርደውን መሸከም ያቅትሃል፡፡
3.     የአማራ የንቅናቄ ድርጅት ነኝ የምትለው ብአዴን እኛ አማራ ክልል የምንኖረውን ተወን ራሳችን ራሳችንን እየመራን እንጅ በአንተ ጥረትና ትጋት እዚህ አልደረስንም /ማለቴ እዚች ዕለት አልደረስንም ለማለት ነው እንጅ እዚህ ስልጣኔ ወይም እድገት ለማለት አደለም/ ስለዚህ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎችና ክልሎች የሚገኙ ወገኖቻችን የሚደርስባቸውን ግፍና በደል የማስቆም ግዴታ አለብህ፡፡ ይህንን ግፋቸውን https://www.youtube.com/watch?v=lUotPfYA76Y&feature=youtu.be እንዲሁም እኛ የማናውቀውንም ሆነ የምናውቀውን የአማራ ዚትዮጵያዊያን ስቃይና ግፍ አይተህ ወደ ክልላችሁ ኑና ስፈሩ እንድትላቸው አንፈልግም ጠልተናቸው ሳይሆን እንኳን ለእነርሱ ለሱዳን ያተረፋችሁት ለጠላታችን የሆነ መሬት አለን እንኳንስ የማይቸግረንን…ግን ኢትዮጵያዊ እስከሆኑ ድረስ ጥፋተኛውን ከሚመለከተው ጋር ተናባችሁ እርምጃ በመውሰድና የዜጎችን ድህንነት ባትጠብቅ አማራ ክልል ውስጥ ካለነው ኢትዮጵያዊያኝ አካባቢ ዝር እስከምትል አንጠብቅህም…ውሳኔው የራስህ ነው ብአዴን!!
4.     ኢህዴድ አንተም ልክ እንደ አማራው ብአዴን በኦሮሞ ህዝብ ስም እየነገድህና የግለሰባዊ ድርጅትና የህወአት ተቀፅላ ሆነህ በየመድረኩ አፍህን ከምትከፍት ይልቅ ይህንን ባዶ ሬሳ ጭንቅላትህን የጥላቻ መርዙን አስፈንጥረህ ጣልለትና ከውዱ የአማራ ህዝብ ጋር ውዱ እና ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ተሳስቦ ተፋቅሮ እንዲኖር የበኩልህን አስተዋፅኦ አድርግ ይህ ግዴታህ ነው፡፡ ብቀላ ለማንም አልበጄ ወዳጄ ኦህዴድ ህወአት ይህንን ሴራ ቢያሴር ወዶ አይምሰልህ…ራስህ ስለምታውቀው እንደቁራ አልጮህም…ይሕንን ባታደርግ ሰፊው የኦሮረሞ ህዝብና ሌላው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ራሳችሁ ላይ አስከፊ እርምጃውን ይቀጥላል፡፡ ደግሞ እልህ እንዳይይዛችሁ…ይህንን የፃፍኩት እኔ አንድ ግለሰብ አቢ ቢን ነኝ ሆኖም የአማራው ብቻ ሳይሆን የየትኛውም ቋንቋ ተናገሪ እምነት ተከታይ ሲገፋ ሳይ ደሜ ይፈላል…በስሜት አደለም ይህንንን የምለው እጅግ አስቤበት ነው፡፡ ይህም የኔ ስሜት ብቻ እንዳልሆነ አምናለው…!!!
5.     ለህወአት ትግራይ ውስጥ ብቻ ነው እንዴ የትግራይ ህዝብ የሚኖረው…አማራ ክልል ውስጥ በተለይ በባህርዳር በወሎ በተለይ በተለይ ደግሞ በጎንደር ከተማ እኮ ግማሽ በግማሽ በዚህ አስር አመት ውስጥ መጥተው ሚሊየነር ሆነው ከአማራው ህዝብ ጋር ልክ ኦሮሞውም አማራ ክልል ውስጥ መጥቶ ሀብታም እንደሆነው ሁሉ…በሰላም ሰርተው እየገቡ ማህበራዊ ነሯቸውን እያጧጧፉ ነው፡፡ ታዲያ የአማራው ህዝብ ሄዶ ያውም ሰፈራ በምትሉት ኮተታም ፖሊሲ መስፈሩ ምንድን ነው ሃጢያቱ …ምን አጠፋና ነው በናንተ ሰብባና በናንተ አስተምህሮ በናንተ ሴራ እና ወጥመድ አጥማጁን ኦሮሞ ተጠማጁ አውሬ ደግሞ አማራ እንዲሆን አድርጋችሁ የተዋችሁት ኧረ ምንድን ነው አለማችሁ…ዋናውን አላማችሁንስ እናውቀዋለን…ወይም ካጠፋችሁ ኑና አማራውን ያውም ከቻላችሁ በመትረየስ ለመፍጄት ሞክሩ እንጅ ለምን ወንድማማች ህዝብን ተጋብቶ ተዋልዶ ደሙ አንድ የሆነን የጋራ ህዝብ ኢትዮጵያዊ እንዴት አእንዲሞት ፈረዳችሁ እንዴት ዝምስ አላችሁ እንዴት ዝምምምምምም አላችሁ!!!! መልሱልኝ!!! ስለዚህ አሁንም ለዚህ አፋጣኝ የሆነ ምላሽና ማንም አማራ ማንም ኦሮሞ ማንም ትገሬ ማንም ደቡብ ማንም ጉሙዝ ማንም ሶማሌ ማንም ጋምቤላ ሌላው ክልል ውስጥ ስለኖረ ብቻ ሲገደል አደለም ሲሰደብ ዝም ብላችሁ ማየታችሁ ከታሪካዊ ስዕተትና ፍርድ አያስመልጣችሁም!!! ይሄው ተናገርኩ…ይህ የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃና ሴቃ እናንተ ላይ ባላሰባችሁት አግባብ እንደሚደገም አትጠራጠሩ…ይህ እንዳይሆን አሁኑኑ መቆሙን ግፉ ግድያው ንብረት መውደሙ እንዲቆም አድርጉ…በየትኛውም አማራጭ፡፡
6.     ኢተዮጵያ ውስጥ ያላችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች የሲቪል ተቋማት እንዲሁም የእምነት ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰብ አቀፍም ይሑን በጎ አድራጊ ድርጅቶች እና ተቋማት ይህንን የተሳሳተ እርምጃና ንፁህ ኢትዮጵያዊ መግደል መደብደብ መዝረፍን በገሃድና በይፋ መቃወማችሁን አሁኑኑ መስማትና ማወቅ እንፈልጋለን እኛ ኢትዮጵያዊያን፡፡ ይህ አለመሆኑ የሚጎዳህ የሚጎዳሽ የሚጎዳን እኛኑ ኢተዮጵያዊያንንን ነው፡፡ ንብረት ሃብት ያላችሁም ይህንን ጉዳይኛ ዘር ማጥፋት ለማስቆም ማንኛውንም ድጋፍ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ሰላም ከሌለ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡
7.     ለኦሮሞ ህዝብ የተከበርከው የሰፊውና የምርጥ ኢትዮጵያዊው ቤተሰብ እባካችሁን ይህ እኩይ ተግባር ማለትም በኦሮሚያ ክልል በወያኜ ሴራ እና ጥንሰሳ እንዲሁም በአንዳንድ ግልፍተኛ ታሪክን ለመማሪያ ሳይሖን ለመበቀያ በሚወስዱ ወጣቶችና ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት የተከበረውና የኢትዮጵያዊ ወንድማችሁን የአማራውን ደም ያለአግባብ እጅግ በ21ኛው ክፍለዘምን ሊታሰብ በማይችል መልክ እያፈሰሱት ሃብት ንብረቶቻቸውን እየዘረፉ እያወደሙ ይገኛሉ በመሆኑም እነዚህ አካላት ከጉያችሁ ያሉ አብረዋችሁ የሚኖሩ ልጆቻችሁ ወንድሞቻችሁ እህቶቻችሁ ናቸውና ምንም እንኳን እንደ አንድ ፀሃፊ አይቸው እንደወያኜ ልውረድ ብየ እንጅ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወንድምና እህቶቻችን ሳያውቁም ሆነ እያወቁ በቂም በቀል ታሪክን ድጋሚ ለጥፋት ለመጠቀም ወያኜ በሸረበው ሴራ ገብተዋልና…
"…ልጆቻችን ወንድሞቻችን እህቶቻችን ተውውውው!! እነዚህ አማርኛ ተናጋሪም ይሑኑ ሌላ ተናጋሪ ስዎች እኮ ጥሎባቸው ከሚወዱት ቀየ በችግር ሰርቶ ለመብላት የመጡ ወንድሞቻችን እህቶቻችን እንጅ…ጠላቶቻችን አደለሉም!! ስለዚህ የአማራው መኖር የትግሬው መኖር የሶማሌው ደቡቡና ጉሙዙ እነድሁም ጋምቤላው መኖር ለዚች ቅድስት ሃገር ቢጠቅም እንጅ አይጎዳትም…እኛ ያኘሌሎች ሌሎችም ያለእኛ ኢትዮጵያን ማቆም ማሳደግ ማልማት የጋራ ጠላታችን ወያኔን ማውደም አንችልምና እነርሱ የኛ ናቸው…ይህ የኢህአዴግ ወያኜ ሴራ ነው…ከአማራው ጋር በመሆን እጅና ጓንት በመጣመር ልናጠፋው ስላወቀ ብቻ ወያኜ የሸረበው ሴራ ነው…ተዋቸው ይልቅስ ወያኜ ኢህአዴግን እናጥፋ አማራዎችማ ታገብተን ተዋልደን አንድ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ህፃን ልጅ በመካከላችን እያለን…ከእነርሱ ጋርማ አንጋጭም…ራሱን ወያኜን ግን ከገባበት ገብተን ብቻ እናጥፋው…የእኛም ወገኖች እኮ አማራ ክልል ውስጥ አሉ በመቶ ሽህዎች…እናንተ እዚህ ሲጨፈጨፉ አማራ ክልል ውስጥ ያሉት ኦሮሞዎችስ ምን ይሁኑ…!!!?"
ወዘተ ብላችሁ ይሕን የአማራ አማርኛ ተናጋሪ ላይ የሚደረግ ሸፍጥ አንዲቆም የምትችለውን ማየት አለብህ፡፡  አዎ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ይህን አሳፋሪ ድርጊት መቃወምና መታገል መጨረሻውንም ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን አፋጥን፡፡ ይህ ጥሪ እዚህ ላይ ስማችሁ ያልተጠቀሳችሁ ድርጅቶች ሁሉ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡
አማራ ለኦሮሞ  ወንድሙ ነው፡፡ ፍቅርን የተማማሩበት የበርካታ ዘመናት መድረኮች አሏቸው!!! ታዲያ ይህ ብቻ የጠላትን ወሬ ባዶ ሊያደርገው አይገባም ነበር? ለምን የወለጋ ጊምቢ እና የሌሎችም ኦሮሚያ አካባቢዎች ሌሎችም ለምን ሌላ ስዕተትን እንዲደገም ፈቀዱ፡፡፡
ለማንኛውም በያላችሁበት የሚመለከታችሁም ሆነ አላፊ አግዳሚው ይህንን ማውገዝ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አደለም፡፡ ለዚህም መግለጫ ማውጣት ያሻችኋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትሁር
ኦሮሞና አማራ አንዲሁም ሌሎች ሁሉ አንድ ናቸው!!! ይሕ ህዝብን ከህዝብ የሚያፋጅ ታሪከ እያስፃፈ በዘመዶቻቸው አማራው የኦሮሞውን ማህበረሰብ እነደበደለ ምናምን አድርጎ በማቅረብ አንባንድ በማስተማርም ጭምር ግፍ ሰርቷል ዘላለማዊ ስልጣን አደረገው እኮ…
ቸር ሰንብቱ መልዕክቱን ለሁሉም ሰው አድርሰ!!

No comments:

Post a Comment