Monday, June 16, 2014

አምባገነኖች መንግስትና ፍትሃዊ በሆኑበት ሃገር ህዝብ የራሱን ውሳኔ ይወስናል ገዥ ባለበትም የራሱን ስርዓትና አገዛዝ ይመሰርታል፡፡



አምባገነኖች መንግስትና ፍትሃዊ በሆኑበት ሃገር ህዝብ የራሱን ውሳኔ ይወስናል ገዥ ባለበትም የራሱን ስርዓትና አገዛዝ ይመሰርታል፡፡ በመሆኑም መንግስታችን ሳናደርገው መንግስታችሁ ነኝ ብሎ ያስገደደንን አምባገነናዊ ስርዓት ከስሩ ፈንቅለን ለመጣል ለሚያወጣቸው ህጎችና መመሪያዎች በምንም መልኩ ተገዥና አጎብዳጅ ልንሆን አይገባም፡፡
ስለዚህ የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ይህን አምባገነናዊ ስርዓት ሃገራችን ላይ በራሱ አፋኝ እና ማፊያ ቡድኖች አማካኝነት ሃገራችን ወደ ስርዓት አልበኝነትና መንግስት አልባነት እየቀየራት ለመሆኑ ቀን ከሌሊት የምናየው እውነት መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡
ይህ ስርዓት ምናልባትም ሙሉ የኢትዮጵያን ህዝብ በበርካታ ማጎሪያ ዞኖቹ አስሮ ለመጨረስ መቸም ያላሳደገው እውነተኛ የፋይናንስ አቅም አስሮ ይዞት እንጅ በሃሳብ ደረጃ ሁላችንም እስር ቤት ውስጥ አስሮናል ሁላችንም ገድሎናል ደጋፊዎቹና አጫፋሪ አባላቶቹ ብቻ ኢትዮጵያ ውድ እናታችን ላይ እንዲጨፍሩባት ታሪካዊ ህልሙን እዲያሳኩባት ብቻ ነው የሚሻው፡፡
በመሆኑም ውድ ኢትዮጵያዊያን ውድ ሃገር ወዳድና አንድነት ናፋቂ ህዝቦች ሆይ የአንዱ ብሄር ጥያቄ አይመለከተኝም ያንዱ ግለሰብ የመብት ጥያቄ አይመለከተኝም አያገባኝም ሳንል እርስ በራሳችን ተፋቅረን እርስ በራሳችን ተዛዝነን ተሳስበን ይህንን ምስኪን ሃገር ከአዘቅት ለማውጣት መረባረብ አለብን፡፡ ይህን ለማድረግ በምንችለው ሁሉ መስመር ሄደን አንድ ቦታ ላይ በስተመጨረሻ ብቻ መገናኘቱ ከጥቅሙ ይልቅ የመበታተንና ክፍተት የመፍጠር አጋጣሚዎችን ስለሚፈጥር መስመራችን አንድ አድርገን ትግላችን ከማጠናከርና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ጥያቄያችን ከማቅረብ በላይ ለየትኛውም ለመንግስት ህጎች ተገዥ ባለመሆንም ተቃውሟችን ማሰማት ማሳየት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስደመጥ አለብን፡፡
አለማቀፉን ማህበረሰብ የምናሰማበት ምክንያጥ ነፃ ያወጣናል በማለት ሳይሆን አለማቀፋዊ ህጎችን ለማክበር ነው፡፡ መንግስት በየትኛውም አጋጣሚ ስርዓቱን በምንም ያህል መጠን ሲቃወም ቢያገኝ ማንንም ቢሆን አንድም ወደ እስርቤት ሁለትም ወደ ግርፋትና ስቃይ ቦታዎች አለያም ቀለል ሊያደርገው ከፈለገ ከመግደል ወደኋላ እንደማይል ሁላችንም ጠንቅቀን አውቀን ትግላችን ማጧጧፍ ይጠበቅብናል፡፡
ለዚህ ሁሉ ትግላችን ስኬት ዋናው መሰረት ግን አንድነታችንና ውህደታችን ለአንድ ዓላማ መቆማችን ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ እና ጀሌዎቹ ማለት ምንም ማለት አደሉም በመካከላቸው ምንም አይነት መተማመን እንደሌለና እርስ በእርስ በጥርጣሬ አይን በመተያየት የሚገፋቸው ካገኙ ማንም ሳይነካቸው ተበላልተው የሚያልቁ እፉኝቶች ናቸው፡፡
በላስልጣናቶቹ መላቀቂያና መሹለኪያ መስመራቸውን ስለዘጋባቸው ብቻ እንጅ አንድም ባለስልጣን መንግስታችን ያልሆነው መንግስትን አክ እንትፍ ብለው ተፍተውታል፡፡
ከዚች ቅፅበት ጀምሮ የትኛውም ብሄር ላይ ይሑን የትኛው ብሄርን መሰረት ያደረገ ከአንዲት ኢትዮጵያ ምስረታና ይሕንን አላማ አድርጎ የማይንቀሳቀስ ፖለቲካ ፓርቲም ይሑን ግለሰብ እምነት ተቋምም ይሁን ምን በለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያንንና  ደጋፊዎች ዘንድ በምንም መንገድ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡
በዛም አለ በዚህ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን የምንሻው ኢትዮጵያ ሃገራችን አንድነቷ ተከብሮ የበለፀገችና የህዝቦቿ የኑሮ ሁኔታ አሁን ካሉበት የዘቀጠና የሚዘገንን የድህነት አሮንቃ ተላቀው የሃገራችን ህልውና ላይ ብቻ የሚያተኩር መዘመን እና ዓለም ላይ ተወዳዳሪ ሆነ ትውልድን የያዘች ሃገርን ነው፡፡
ሁልጊዜ ስለመብት ለስለመረገጥ ስለሞት ስለረሃብ ስለድርቅ ስለአምባገነናዊ ስርዓት ወዘተ የምናስብበት ጊዜ አብቅቶ ከእኛም ተርፈን ስለሌሎች ማሰብ የምንጀምርበት ሰኣትና ወቅት የሚሆንበት እውነት ስላልሆነና ማንኛውም ዜጋ የራሱን ሃገራዊም ይሑን ግለሰባዊ አስተዋኦ ያለምንም ገደብ እስከጠቀመ ድረስ እንዲያበረክት የሚያስችለው ስርዓት እስኪፈጠር ድረስ ከየትኛውም ብሄርተኛ አስተሳሰብና ጥበት ወጥተን እንደ አንድ ኢትዮጵያ ብቻ እንጅ እንደ አንድ አማራ እንደ አንድ ኦሮሞ ትግሬ ሶማሌ አፋር ደቡብ ጉሙዝ ጋምቤላ በአጠቃላይ እንደ አንድ ጠባብ ብሄርተኛ ስለብሄሩ ደህንነት ብቻ ከማሰብ ተላቅቀን ይሕችን ሃገር በአንድ ህዝብ በአንድ ባንዲራ በአንድ የለውጥ መስመር በአንድ ሃገራዊ ስንቅ ነገር ግን በበርካታ ድንቅ ቋንቋዎቻችን ታጅበንና ተያይዘን ህች ሃገር መጀመሪያ ከዚህ ውስጣዊ ቅኝ ግዛት ራሳችን አላቅቀንና ነፃነታችን ያሳጣንን የሚያስርና የሚገድል የሚገርፈንን ስርዓት መብቶቻችን የነፈገንን ስርዓት ነፃ እምነቶቻችን የበከለብንን ስርዓት ድራሹን ካጠፋን በኋላ እኔ እብስ አንተአንች ትብስ ተባብለን ተፈቃቅረን ተከባብረን ወደ ህልማችን ደረጃ ማድረስ ዜግነት ግዴታችን ነው፡፡
በመሰረቱ አንድ የዚህ መንግስታችን ሳናደርገው እየገዘዛን ያለው ስርዓት ሁልጊዜም ሊቀበለው የማይፈልገውና እንደራሱ እየመሰለው የማያምነው ነገር ቢኖር እኛ ለውጥ ፈላጊ አንድነታችንን የምንሻውና ልዩነታችን አክብረን ተቀብለንም ዘረኛ እና ብሄርተኛ መደባዊ ስርዓቶችንም ሆነ ግለሰቦችን የምንታገል ኢትዮጵያዊያን ስልጣናቸውን ለህዝብ ብቻ ሊያስረክቡ እንደሚገባ እና በሰላም ሃገራቸው ውሰጥ በሰላም ሊኖሩ እንደሚችሉ ብንነግራቸውም አይቀበሉም፡፡ ከየት ያመጡትና ታማኝን ማመኑን፡፡ ግን እኛ እንላችኋለን ወደሃይል እርምጃ ብንሄድ እንኳን በምንም መልኩ ከግለሰቦች ጋር ፀብ እንደሌለን ነገር ግን ከአምባገነናዊ ስርዓቱ ጋር ብቻ እንደሆነ ፀባችን ሊያውቁት ይገባል፡፡
ይህ ስርዓት እኮ…የምንፈልገውን ለውጥ ሁሉ እስከመብቶቻችን መከበር እና ሉዓላዊነታችን አለማስደፈር ይቅርና ዳርድንበራችን መሸጥ መለወጥ ድረስ እንደምንፈልገው ቢሆንልን ሴረኛና ከፋፋይ ባይሐን አድሏዊና አሳሪ ገዳይ ገራፊ ባይሆን "ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን" ተከታይ  ቢሆን ዲሞክራሲን ተከታይ የሚለው ካሉት መልካም መርሆች አንግል እንጅ የራሱን ፍልስፍናም ቢከተል ለህዝባችን አንድነት ለሃገራችን ሉዓላዊነት የሚጠቅም በህዝባችንና በሃገራችን መካከል ያለውን መጣመሪያ መገናኛ ድልድይ የሚያጠናክር ቢሆን ሚሊዮን ዓመትም በገዛን ነበር፡፡
ነገር ግን እንደ ስራውና ግፉ አንድም ቀን ማሳደር አንፈልግ፡፡ በቃን በቃን በቃን የሚል ድምፅ ሙሉ ሃገሪቱ አፈር ላይ የትም ቦታና ሰዓት ላይ እንቁራ ሲቃልት ሲጮህ እየተሰማ ለምን ለዚህ ጩኸት ምላሽ አንስጥ ለምን በጣጥሰን አንጣል ይህንን የሸረሪት ድር የሆነ ስርዓት፡፡ ለምን አንታገለው ለምን አንሰባብረው፡፡ እኛ እርቦናል ተቸግረናል እነርሱ ስርዓቱና ባለስልጣናቱ ቢሊየነሮች ይሆናሉ፡፡ እንዲያው ሲፈርዱብን ስናብድ ስንጮህ ሲፈርዱብን ትንሽ ብሎ እንኳን አይሰማቸውም፡፡ ምን ነካቸው አሁን አሁንስ በሰው ስለመመራታችንና በሰው ዘሮች በሆኑ ባለስልጣኖቻችን ሃገራችን ስለመንቀሳቀሷ እጠራጠራለው፡፡
አስቡት እስቲ እንዲህ በደል ደርሶብናል ተቸግረናል ኑሮ ከብዶናል በግፍ እየተገደልን ነው በግፍ እየታሰርን ነው መላ በሉን ባልን እነርሱ ሌላ መላ በቅርብ መልለው እኛን ሸቤ ያስገቡናል ለእኛ አስከሬን መጣየያ ቦታ እየፈለጉ በዱር በገደሉ ይወረውሩናል፡፡ ዛሬ በየቦታው ስንት ጊዜ ነው ሰው እንደ ዶሮ ቤቦታው ሞቶ የምናገኘው ማን እንደገደለው ሳይታወቅ ማን እንዳረደው ሳይታቅ የሰውን ልጅ ያህል ክቡር ንቡህ ነገር በየቦታው ተቆራርጦ የሚገኘው በማን ነው፡፡ ኧረ ተውውውውው… ኧረ ተውውውውውው…
ይህም ቀን ያልፍና አምና ይባልና…መባሉ ተረሳ እንዴ ኧረ ተውውው…ይህ ህዝብ የሚበላው አጥቷል፡፡ ይህ ህዝብ የሚጠጣው አጥቷል፡፡ እውነት ነው ፈጣሪና ተፈጥሮማ እንደእናንተ ስላልሆኑ በየወንዙ የሚጠጣ ሞልቷል በየዱሩ ሚበላ ሞልቷል እኛ አፈር ምሰን ጤዛ ልሰን የአቧራ በሶ ጠጥተን ነው የኖርነው ለምን እንደእኛ አትሆኑም ካላችሁ…መልሳችን ዝቅዝቅ በሉ ነው!!! አዎ ዝቅዝቅ በሉ ነው፡፡ እናንተ ነፃ ልታወጡን ከነበረው ስርዓት ልታላቅቁን ሳይሆን ልትላቀቁ በመፈለጋችሁ ብቻ ነው እንደዛ የሆናችሁት ግን አንላችሁም እኛ የምንላችሁ…
…አሁን አለም አለምን ጨብጧል እኛ ግን ተመጧች መሆን አንሻም አሁን የዓለም ህዝብ ስለመብቱ ከመታገል አልፎ ስለ ቅንጦት የኑሮ ምቾቱ እያሰበና እያማረጠ በርካታ የኑሮ ምቹ አማራጮች አሉት እኛ ግን እኳን ምቹ አማራጮች ሊኖሩን በናንተ ግፍና ስንፈት በናንተ ታሪካዊ ስዕተት ምክንያት ያለንን ያልሞላ አንድ አማራጭም እንኳን በሰበብ አስባቡ እየነሳችሁን ስንቶቻችን በረሃብ አልቀና ስንቶቻችን በየቀኑ እንታሰራለን ስንቶቻችን በየቀኑ ሃብቶቻችን በማፊያ የመንግስት አደረጃጀቶች እየተዘረፍንና እየተዋከብን እንውል እናድራለን፡፡ ስንቶቻችን በየቀኑ እንሞታለን ስንቶቻችን በየቀኑና ደቂቃው እንገረፋለን ኧረ ምኑ ቅጡ…
ሆሆሆሆሆሆሆ…ድድድድድድድ ይፍጀው!!!
ነው ያም ሆነ ይሕ ምንም ከናንተ አንልግም የያዛችሁትን ይዛችሁ ልቀቁን ለናንተ አንገዛም ነው የእኛ ጥያቄ የማትጨርሱትን አትጀምሩ፡፡ እኛ አንለያይም እኛ አንበታተንም እኛ ከታሪካዊ እኛነታችንና አንድነታችን አንወጣም አሁን በመካከላችን የዘራችኋቸው ልዩነቶችና ቁርሾዎች ሁሉ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቀዳዳ ይሞላሉ ብቻ እናንተ ልቀቁን ልቀቁን…ልቀቁን!!!
አንድ ነገርም እናረጋግጡላችሁ የናንተው ሴረኞች በህዝቡ መሃል እየተሸለከለኩ ቀዳዳዎችን ለማስፋት ቢጥሩም የኢትዮጵያዊያን ግድግዳ ማስቲካ ነው ሙጫ ነው ይጠራራል ይሳሳባል ቀዳችሁት በሄዳችሁ ቅፅበት አንድ ሆኖ ደግማች ብትሄዱ ቀዳዳ የለም ስለዚህ አጉል ልዩነት ላትፈጥሩብን አአጉል አንድነታችን ላትንዱት አትድከሙ የኛ አንድነት ከፈጣሪ ነው የሙስሊሙና ክርስትያኑ አንድነት ከፈጣሪ ነው፡፡ አንድነታችን በልዩነታችን ከፈጣሪ ነው ከማንም አደለም የፈጣሪን ስራ እናነተ ልትንዱት አይቻላችሁም፡፡ አትድከሙ፡፡ ወይ ደግሞ ዝም ብላችሁ በመካከላችን ገብታችሁ እኛን መጨረስ ከሆነ ሃሳባችሁ ንገሩን እንደማትችሉ ግን እንላችኋለን፡፡
መሮናል ተውውውንንንንን ልቀቁን ልቀቁን…ይህንን እናሳውቃችሁ ዘንድም አንድነት የእሪታ ቀን ላይ እናሳያችኋለን፡፡
አደራ አደራ አደራ
ለኢትዮጵያ ህዝብ…
መጀመሪያ ምንም አይነት ክፍተት አንፍጠርላቸው፡፡ የትኛውም ግለሰብ የትኛውም ቡድን ከየትም ይምጣ የየትኛውም እምነት ይሁን ፖለቲካዊ ተቋም ይምጣ አንድነታችን የሚነካ ልዩነታችን  በታሪካዊ ስዕተቶችም ይሁን በምን መንገድ ሊበታትነን የሚፈልግን አካል በፅኑ በመታገል ሃላፊነታችን እንወጣ!!!
አንድነታችን በልዩነታችን ውስጥ ልዩ ሃብታችንና ህብረ ብሄራዊ ክብራችን አንድነታችን መሆኑን ጠንቅቀን አውቀን አማራውን ከኦሮሞው አማራውን ከትግሬው ትግሬውን ከኦሮሞው ኦሮሞውን ከሶማሌው አፋሩን ከሶማሌው ደቡቡን ከጉጅው አንዱን ከአንዱ ለማጣላት ላማፋጀት ለማጋደል የሚጥረው ሁሉ በግለሰብ ደረጃም በቤተሰብ አባል ደረጃም ይሁን በየትኛው ደረጃ አንዳች ሳይጣናዊ አንዳች ኢህአዴጋዊ ተልዕኮ እንዳለው አውቀንና ነቅተን ጥንቃቄ የተሞላበት ምላሽ መስጠት እስከ እርምጃ መወውሰድ ድረስ መቀጠል አለብን፡፡
በአንድነታችን የሚመጣ ቢሆን ልዩነታችን ለማስፋት የሚመጣ ቢሆን ታሪካዊ ስዕተቶችን ለመበቀያ የሚነግረኝ ቢሆን እናቴንም አባቴንም አልምርም!!...የሚል ስነልቦና ሊኖረን ይገባል አንድ ብርቅየ እናታችን ኢትዮጵያን የምንፈልግ ከሆነ አለበለዚያ ይህን በታታኝ አላማ የሚደግፍ ሁሉ ገዥው አምባገነን እና ስርዓት አልባ መንግስት ደጋፊ የአንድነታችን ጠላትና በብሄራዊ ክብራችን የሚመጣ ሉዓላዊነታችን እንዳስደፈረ…መሬታችን እንደሸጠ ጀግኖቻችን ከመታሰራቸው እጁ እና እጇ እንዳለበት…ከሞቱትና ዞትር ከሚገደሉት የነፃነት ታጋዮቻችን ደም እጁ እንዳለበት የምንወስድና በታሪክም የምንጠይቅ መሆናችን ማንም ሊያውቀው ይገባል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሰፊው ለውጥ ናፋቂ
አንድነታችንንን አትንፈጉን የዘር ጥላቻን አትዝሩብን
ቆርጠን ተነስተናል
ሰማያዊ ርቲ እናመሰግናለን!!

No comments:

Post a Comment