Monday, June 16, 2014

ለኢትዮጵያ ትልቅ ካንሰር ማለት ኢህአዴግና ጀሌ መደብተኞቹ ናቸው!!



ለኢትዮጵያ ትልቅ ካንሰር ማለት ኢህአዴግና ጀሌ መደብተኞቹ ናቸው!! ምድሃኒት ያለው ካንሰር!! #‎Blueparty መብትን መጠየቅ ወንጀል አይደለም ወንጀል መብትን መቀማት ነው ወያኔ ኢህአዴግ የህዝብን መብት የነጠቀው እራሱ ሆኖ ሳለ ንጹሃንን ወንጀለኛ አድርጎ እያሰረ ነው የሃገሪቱን ሃብት ከህዝብ እየቀማ ያለበት ወቅት ነው
መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም መብራት የለም ውሃ የለም ነትዎርክ የለም

ሚያዚያ 15/8/2006 ላይ የጭልጋ አካባቢ ገበሬዎችና ማለትም ህዝብና የመንግስት ታማኞች ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በርካቶች እጅግ በርካቶች ከሁለቱም ወገኖች መሞታቸው የታወቀ ሲሆን…በተለይ ከመንግስት ወታደሮችና ፌደራል ፖሊሶች በኩል በርካታዎች ሞተው በርካታዎች መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡ የሚገርመው ግን ህዝቡ በርካታ ወታደሮችን ማርኮ መውሰዱ መሰማቱ ነው፡፡ እስቲ እዛ አካባቢ ያላችሁ ወገኖች አረጋግጡልን፡፡

የትውልድ ገመና ከታች
የትውልድ መማሪያ ከሳች
ታሪክ መስታወቱ
ብቸኛ ቀዳዳ የእይታ መስኮቱ
ሲውል ሲተረጎም ለፍጅት ለከንቱ
ምንኛ ይጎዳል ያቆስላል በእውነቱ
ቅድመ አያቶቻችን ሰው አደሉም አንዴ
ስተት ሰሩ ተብሎ ለዚኛው ዘራቸው መበተኑ ባንዴ
ከዚህ ይልቅማ
ያኔ ሳንነቃ ርቃናችን ሳለን
ልብስ ያለበሱን ገመና መክተቻ ታሪክ የሰሩልን
ታሪክ ድንበራችን ከልለው ያቆዩን
በአጥንት በደማቸው አንድም ያደረጉን
የአለማችን ቁንጮ ያኔ ያደረጉንን
ምነው ብናነሳው ምነው ብንፅፈው
ምነው ብንቀርፀው
ምነው ብናቆመው
ምንም አይካድም ለማንም ግልፅ አደል
ሰው ሆነው እያለ መች ሰሩና ስተት ፍፁም ናቸው መባል
ከውሸትም ውሸት በራስ ላይ መቀለድ ራስን መደለል
ሆኖ ሳለ እውነት ሰው ልጅ መሳሳቱ
ለአላማ ማሳኪያ ለአጀንዳ ማድለቢያ አድርጎ ማጉላቱ
እድገት ብልፅግና ስኬትን መርሳቱ…

No comments:

Post a Comment