Monday, June 16, 2014

እኛ የምንፈልገው ነፃነት ሁሉ አቀፍ ነፃነት ሆኖ እያለ እናንተ ይህን ሰርተንላችሁ ይህንን እያደረግን ገለመሌ ትሉናላችሁ ለምን ጥንቅር ብሎ አይቀርም ያለነፃነት ሃብትና ንብረት…



እንዴ የኢህአዴግ ደጋፊና አባላትና ባለስልጣናት ጥያቄያችን አሁንም አልገባንም ሊሉ ነው መሰለኝ አንዱ ካድሬ ምን አደረገ መሰላችሁ… አንድ ዘመናዊ መንገድ የሚያሳይ እና ባቡር መንገድ ዲዛይን የሚያሳይ አንድ ንድፍ ለጠፈና ጠላቶች እርር ድብን በሉ ይላል ከላይ…
ታዲያ ምን ገረመህ አትሉኝም…
1.      በቃ ተቃዋሚ ሲባል ተቀናቃኝ መሆኑን ለሃገር ለውጥ መሰረት የሚጥል ወሳኝ ሃይል መሆኑ ቀረና ጠላት ተባለ
2.     እንዴ የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ ኢህአዴግ ተብየው ስርዓት አልባ መንግስት ሳናደርገው የነገሰብን ሃይል መልካም ስራዎቹ እንዳሉ ሆነው የኛ ጥያቄ እኮ  ነፃነታችን ነፈገን፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስታዊ መብቶቻችንን ገስሶብናል፣ ቀን በቀን በቁጥራችን ልክ ህግና መመሪያ እያወጣ ነፃነታችንን ነፍጎናል፣ ህገመንገስታዊ አንቀፆችን ይጥሳል፣ ዜጎችን በእኩልነት አይን አያስተናግድም፣ ዜጎችን ይከፋፍላል በዘር በቀለም በቋንቋ በምናምን ድራሻችን ሊያተፋን ነው፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን አንድነትን አይፈልግም ለምን ኢትዮጵያዊነታችን ቢያንሰ እንኳን ሃገራችን ውስጥ አያከብርልንም፣ ለምን ተከብሮ የኖረውን ሉዓላዊነታችንን አይመልስልንም፣ ለምን ለረሃብና ለችግር አሳልፎ ይሰጠናል፣ ለምን ሳንጠግብ ጠግበዋል ብሎ እንደ ክፉ እንጄራ እናት ይሳለቅብናል ምን አደረግነው፣ ለምን በልዩነቶቻችን ጣልቃ እየገባ ለስንት ሽህ ዓመታት ተከባብረን የኖርንን ዜጎች ለምን ያበጣብጠናል፣ ለምን ተወዳዳሪ የሆነ የትምህርት ፖሊቼ ቀርፆና ተወዳዳሪ የሆነ ተማሪን መፍጠር የሚችል ተማሪ የነገ ተስፋ እንዲፈጠር ማድረግ የሚችል ካሪኩለም አያዘጋጅም እስካሁን የምንማረው እኮ ኢቭን በ18ኛውና በ19ኛው እንዲሁም በ20ኛው ክ/ዘምን በተፃፉ ዋቢ መፅሃፍት ነው ለምን፣ ለምን የምንፈልገውን ወደ ስልጣን ልናወጣ ዘለትፍቅድሊንም፣ ለምን የፈለግነውን ሳንሳቀቅና ሳንደበቅ እንድንፅፍ እንድንናገር እንድንመሰክር ዲሞክራሲያዊ መብታችን አይከበርም፣ ለምን ዳር ድንበራችን ይሸጣል ለምን ለታሪካዊ ጠላቶቻችንና ሌሎች እየኮረመመ ያስረክብብናል ስንት ስራ አጥ ወጣችን አሰልጥኖ ይህንን ለተላት ሰጠውን ቦታ ማስረከብ እየቻለ፣ ለምን የተማረውን ማህበረሰብ መሸከም የሚችል ኢኮኖሚ መገንባት አልቻለም ስቲል አንድ ስራ ለመወዳደር ለአንድ መደብ እስከ 10 ሽህ ተወዳዳሪ መመዝገብ የተለመሰ ነው እንዲሁም እስከ 50000 ምሩቅም…ያውም አዲስ ምሩቅ አንድ አማካይ ህዝብ ብዛት ካለው ከተማ ላይ…ለምን፣ ለምን ብምንፈልገው መልክ ለእኛ ለምስኪን ኢትዮጵያዊያን ጀሮውን አይሰጥም፣ ወዘተ እነዚህና ሌሎች ሆነው እያለ ጥያቄዎቻችን አነርሱ ልማቶችን በጭፍን የምነቃወም ይመስላቸዋል…ኢህአዴግ ይህን ያህል ሰላም ሰፈነበት ሃገር ይዞ ከሰራው እኮ ደርግና ቀ/ኃ/ስላሴ ያን ያህል በውስጥና በውጭ ተወጥረው የሰሩት እኮ ይበልጣል፡፡
3.      እኛ እኮ የምንለው በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የምታገኙትን ሃብት አትዝረፉት ከፎቅ ላይ ፎቅ እየዘረፋችሁ ብትሰሩ ምንድን ነው ትርፉ…ለኢኮኖሚው የኑሮ ውድነትን ከማምጣት ውጭ ሌላ ምን አድቫንቴጅ አለው…እናንተ እኮ ለብዙ የቀን ሰራተኛ እና ግምበኛ የስራ እድል ይፈጥራል ህንፃው እስከሚያልቅ ብሎ አስተያየት የሰጠ ትልቅ መሳይ ትንሽ ካድሬስ አላችሁ አደል…አይ ጥርሶቼ ይላል ባበይ…ኪኪኪኪኪኪ…
4.     እኛ የምንፈልገው ነፃነት ሁሉ አቀፍ ነፃነት ሆኖ እያለ እናንተ ይህን ሰርተንላችሁ ይህንን እያደረግን ገለመሌ ትሉናላችሁ ለምን ጥንቅር ብሎ አይቀርም ያለነፃነት ሃብትና ንብረት…
5.      እኛ ስለመታሰራችን ስለመገረፋችን ስለ መሞታችን ስንጮህ ይህንን ያህል መንገድ ይህንን ያህል የሌሌ ኔትውርክ ዘርግተን ይህን ያህል ውሃ ልማት ሰርተን ይህንን ያህል ግድብ /ባያምርበትም እንኳን መቃወሜ ደግሞ አደልም ግድቡ መሰራቱ ለኔም ስለሆነ አልቃወምም ግድቡ በቻይናዊያን ጣልቃ ገብነት ስለሚሰራ…በአህያ ቁርበት የተሰራ ቤት…ፍርስርስ ይላል ጅብ የጮኸ ዕለት…ስለሆነ ብየ/ ሰራን ገለመሌ ትሉናላችሁ…ይሰራ ያው ለኛው ነው…ልማት ያለህዝብ ተጠቃሚነት ምን ይሰራል…ልማት ህዝቡን ያላማከለ ከሆነ ምን ይጠቅማል ከጉዳቱ ውጭ;
6.     አውራ ፓርቲ ተብሎ የመንግስት ማፈኛ መዋቅር መቋቋሙን እኛ ኢትዮጵያዊያን ከተቃወምን ለምን እንደ አውራ ዶሮ ትቃልቱብናላችሁ…እኛ ከዚህ ሁሉ በፊት መች በላን መች ለበስን መች ቤት ኖረን መች እንደ ልባችን ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን በነፃነትና በፍቅር መንቀሳቀስ ቻልንና…እስቲ ኦሮሚያ ክልል ሂዱ አማራው እየተሳደደ ነው እስቲ አዲስ አበባ አካባቢ ሂዱ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወንድምና እህቶቻችን ደካማ እናትና አባቶቻችን እየተሰደዱ አደለም…የነገ ህልውናቸው ምን ይሁን…
7.     አሸባሪ እየተባሉ የታሰሩት እነማን ናቸው? ልባችሁ እኮ ያውቀዋል…እንዲሁ ከረጢታችሁን ሞልታችሁ ለማደር ስትሉ ቅራሪያችሁን ማፈስና መንዘላዘል ጭፈራ በጭፈራ ቤት ለመከራተት እንዲያመቻችሁ…ማለትም ነፃ የሆናችሁ መስሎ ስለታያችሁ እንጅ… ጊዜውን ጠብቆ ፍርዳችሁን የምታገኙ ቢሆንም
8.     እኛ አባይ አይገደብ ተከዜ አይገደብ ባሮ ጊቤ ገለመሌ አይገደብ መች አልን እናንተ አደረግን ከምትሉት በላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ የምንጮኸው እኛ አደለን ነገር ግን መጀመሪያ ነፃ ህዝብ መፈጠር አንድ የሆነ ህዝብና ሃገር አንድ የሆነ ብሄራዊ ስሜት ይቀድማል ነው፡፡ እንዴ…ይህ  እውነት ጠፍቷችሁ ነው…ለነገሩ ባዶ ጭንቅላት ነው ያላችሁ
9.     የኢትዮጵያ ህዝብ በመሪዎቹ ተከብሮ የኖረ ህዝብ እንጅ በአፈሙዝ ስለመጣችሁ ራሳችሁን የጀግና ጫፍ ህዝቡን ፈሪ አድርጋሁ ከመቁጠርና አምባገነናዊ የወረደ አስተዳደራችሁን ወዲያ ብለናችሁ እምብኝ ስላላችሁ እንጅ የምንቃወማችሁ ምንም እንኳን እንደ እናንተ አባባል ጠላት እንደሆንን ባናውቅም መፈረጃችን ባንቀበልም፤
10.    ስንቶችን ነው በግፍና ስለተናገሩ ስለፃፉ ስላነበበቡም ጭምር ስንቶችን ነው ወህሊ ወርውራችሁ ከአዕምሮ በሽተኞች ክፍል ውስጥ ቴነኛዎችን በማስገባት በስነልቡናናና በአካል እንዲጎኡ አድርጋችሁ ስቶች አበዱ ስንቶች ሞቱ ስንቶች ጠየና አጡ…ለዚህ ደግሞ የኦሮሞኛ ቋንቋ እና አማርኛ ተናጋሪው እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬድዋ እንዲሁም ጋዜጠኞች ትልቅ ምሳሌዎችና ብዙ እጁን የሚይዙ ናቸው፣
11.     ስንቶች ተሰደዱ እንዳይሰደዱ ምንግስት የእግድ አዋጅ ብቻ ነበርን መፍትሄው…ይሕም ይሁን ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ዜጎቻችን ለምን የህግ ከለላ አግንተው አይዟችሁ የሚላቸው ያጣሉ… ለዚህም ደግሞ ኢትዮ ሱዳናዊቷ ነፍሰጡር ዶ/ረ ማርያሞ ሞት ሲፈረድባት ያውም ክርስትያን ስለሆነች ብቻ ምን አላችሁ… ምን ብላችሁ የሱዳንን አሸርቋጫችሁን ጠየቃችሁት… ለምን ትገድሏታላችሁ ክርስትያን መሆኗ የፈለገችውን እምነት በመከተሏ ለምን ትገድሉዋታላችሁ…አላችሁ…ብለናል ትሉ ይሖናል እኮ ከናንተ /የኛ ገዥዎች ሳናደርጋቸው የሆኑት/ ውሸት እኮ እውነት ናት እውነት ደግሞ ውሸት…ይህንን በተለያ መረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል…
12.    ለምድን ነው ልዩነታችን አክብራችሁ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያና አንድ ኢትዮጵያዊነት እንዲኖር ለምን አትጥሩም…በመሰረቱ ይህንን እናንተ ባታደርጉት እንኳን ራሳችህ በራሳችም እናመጠዋለን››
13.    ለምን ዜጎቻችን በፈለጉት የኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ እስካሉ ድረስ ለምን እንዲኖሩ አይፈቀድም፡፡ ለምን ይፈናቀላሉ…ለምን ይተሰራሉ ለምን ይገደላሉ አንድም በአባራሪው ሁለትም በዚሁ አርቲስት መሳይ ስርዓት አልባ ስርዓት…
ለእነዚህና ሌሎች በርካታ  ምክንያቶች ስላሉን እንጅ እኛማ የምታገላችሁ /…እስክንጥላችሁ/ እንጅ ለምን በበጎ ስራችሁማ እንጠላችኋለን፡፡ ለምንስ ይህ ጠላትነት ከየት መጣ
ኧረ ስንቱ ለማንኛውም ይቀጥላል…
አብቢን ነኝ


ዳንኤል ተፈራ ቁርጡን አውቀን እንቀመጥ…
ብሏል፡፡
እኔ አብቢን ግን የማስበው ቁርጡን አውቀን እንቀመጥ ሳይሖን ቁርጡን አውቀን እኛም የራሳችን ምርጫ እንከተልም ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግ ከሁለቱ ተቃርኖዎች የትኛውንም መረጠ የትኛውን እኛ በማንኛውም ሰዓት ህዝቡ የሚፈልገውን ስርዓት ኢትዮፕያ ውስጥ ተመስርቶ እሰክናይ ድረስ ትግላችን ከየትኛውም የኢህአዴግ ምርጫ ጫፍ ጋር ቦሆን እየተላጋን ይጥላል፡፡ በሚል ይስተካከል፡፡ ዳንኤልም በእርግጠኝነት ቁርጣችን ካወቅን አርፈን እንረገጣለን ለማለት ሳይሆን ቁርጣችን ካወቅን "ቁጭ" ብለን እናስብና አማራጫችን ኢህአዴግን አስወግደን ህዝብ የሚፈልገው ስርዓት እስኪፈጠር እንታገላለን ለማለት እንደሆነ ተስፋ አደርጋለው…ለማንኛውም አብቢን እንዲህ እንቀሆነ ሃሳቤ ላካፍላችሁ እወዳለው፡፡


ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ለማጥፋትና ለማስነሳት በሚሹ ሁሉ የተፈጠረች ስመ፣ ቅርፀ፣ ስዕለ፣ ምዕናበ፣ ታሪከ እና ምኞተ ብዙዋ ኢትዮጵያ…
አለም ላይ በርካታ ኢትዮጵያዎች እንዳሉ ለመናገር ምንም አይነት መረጃ ማሳደደድ አያስፈልግም
1.      ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ነፃነት ናፋቂ ጭቁን ህዝብ የሚያውቃት እውነተኛዋ ኢትዮጵያ
2.     ዲያስፖራው ነፃነት ናፋቂ  የጭቁኑ ሎካል ህዝብ አካል የሆነው የተጨቋኝ መከታ ህዝብ ኢትዮጵያ
3.     ኢህአዴግ የሚያውቃት ኢትዮጵያ
4.     ሌላው ክ/ዓለም የሚያውቃት ኢትዮጵያ
5.     ታሪክ ያጎሳቆላት ኢትዮጵያ
6.     ተገንጣይና ገንጣዮች የሚያውቋት ኢትዮጵያ
7.     ኢጣሊያና እንግሊዝ ፓኪስታንና ኤርትራዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ
8.     ግራ የተጋባው ሁሉ የሚያውቃት ኢትዮጵያ
9.     ሆዳሙ ካድሬ የሳላትና የጨነቆራት የጎረጎራት ኢትዮጵያ
10.    ታሪካዊ ሥዕተቶችና እውነቶች የሚገልጧት ኢትዮጵያ
11.     ተጀምረው ያልተቋጩ እውነቶች እና ሳይጀመሩ የተቋጩ ታሪካዊ እውነታዎች የሚገልጧት ኢትዮጵያ
12.    በልዩነቶች መካከል ያለች ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ውስጥ ያለች ኢትዮጵያ
13.    በሚላክላቸው ቁልል መረጃ ላይ በመነሳት አንድም የሃገራችን ባለስልጣናት የሚያውቋ ት ኢትዮጵያና የውጭ ረጅ ድርጅቶች የሚያውቋት ኢትዮጵያ
14.    "እኛ" የምናውቃት ኢትዮጵያ
15.    የምንፈልጋት ኢትዮጵያ
16.   ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለያዩባት ኢትዮጵያ /ፖለቲካ ፓርቲዎች በመካከላቸው ያለው ልዪነት የፈጠራት ኢትዮጵያ/
17.    የአስተሳሰብ ስፋትና ጥበታችን የፈጠራት ኢትዮጵያ
18.    ተማርኩ የሚለው ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ የሚላት ኢትዮጵያ
19.   ያልተማረውና በተለይም ያለፉት ስርዓቶች የተዋትን ሃገር የሚያውቃት እና እንዲህ ናት የሚሏት ኢትዮጵያ
20.   ቅኝ ገዥዎች የሚያውቋት ኢትዮጵያ
21.    ስለፖለቲካ አይመለከተኝም የሚሉ አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ
22.   በኢትዮጵያዊያን መካከል ግጭት እንዲኖር የሚፈልጉ አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ
23.   መከላከያ ሰራዊቱና ፀጥታ ሃይሉ የሚያውቋት ኢትዮጵያ
24.   ጎረቤት ሃገራት የሚያውቋት ኢትዮጵያ
25.   የታሪክ ምሁራን የሚያውቋት ኢትዮጵያ
26.  ያለመረጃ ኢትዮጵያ እንዲህ ናት ኢትጵያ ይች ናት ብሎ የሚያውቃት ኢትዮጵያ
27.   የኣለም ሚዲያዎች በየራሳቸው አመለካከትና ባላቸው መረጃ የሚያውቋት ኢትዮጵያ
28.   ኢቲቪ የሚላት ኢትዮጵያ
29.  ሃይማኖቶች የሚሏት ኢትዮጵያ
30.   ኢንቨስተሩና ባለሃብቱ የሚያውቃት ኢትዮጵያ
31.    ዘረኛ አመለካከት ያላቸው አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ
32.   ዶ/ር መራራና መሰሎቹ የሚያውቋት ኢትዮጵያ እና አጼ ቴወድሮስ የሚያውቋት ኢትዮጵያ እስካሁን ቁጭተን አዝሎ
33.   ጠላትና ወዳጆቿ የሚያውቋት ኢትዮጵያ
34.   ኢትዮጵያዊነት የሚያንገበግባቸው አካላት የሚያውቋት ኢትዮጵያ
35.   ኢትዮጵያዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ
36.  አማጺ ቡድኖች ካሉበት ሆነው የሚያውቋትና ተገድደውም ሆነ ለስትራቴጅ የሚያውቋትና የሚቀበሏት ኢትዮጵያ
37.   ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን፣ ሶማሊያዊያን፣ ጅቡቲያዊያን እንዲሁም ኬንያዊያን የሚያውቋት ኢትዮጵያ እንዲያውም ግብፅ፣ ምዕራባዊያን እና የአረቡ ባህረሰላጤ የሚመኛትና የሚያውቃት ኢትዮጵያ
38.   ባለሃብቱ ቨርሰስ ድሃው ብለቶ የሚያድረው ያጣ የሚያውቋት ኢትዮጵያ
39.  ብሄሮች ተብለው የኢህአዴግ ፌደራሊዝም /ፌዝራሊዝም/ የፈጠራቸው /ያስፈነጠራቸው/ ልጆቹ የሚያውቋት ኢትዮጵያ
40.   ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ባለስልጣናት፣ ሃይማኖት ተቋማት፣ ታሪካዊ አባቶችና እናቶች፣ ዕድሜ ባለፀጎች ገለመሌ የሚያውቋት ኢትዮጵያ ከራሳቸው ደካማ አስተሳሰብ ከራሳቸው እውነተኛ መረጃ ከራሳቸው ጥቅም ከራሳቸው አቅም በመነሳት የሚመኗትና የሚያውቋት ኢትዮጵያ
41.    የማናውቃት ኢትዮጵያ…
42.   ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ስለመኖሯ የማያውቅ ህዝብ የሚስላት አፈታሪካዊ እና መፅሃፍ ቅዱሳዊ ምናባዊ ኢትዮጵያ
43.   ደራሲውና ታሪክ ፀሃፊው ጦማሪውና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌላው የሚያውቃት ኢትዮጵያ ወዘተ…

ለማንኛውም ኢትዮጵያዊያን እና ዓለም የሚያውቃት ኢትዮጵያ በትንሹ ይህን ትመስላለች፡፡ እስቲ በናታችሁ ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን  ለምሳሌ የቋንቋ፣ ዘር፣ ቀለም፣ የትውልድ ቦታ፣ ቢሎንጊንግነስ፣ ወዘተ…ፍጹም ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን ጠብቀን እና ተንከባክበን ከተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችን ውጭ ያሉትን "መጤ ሰው ፈጥሮሽ" ልዩነቶቻችን ለምሳሌ ታሪክ ያበላሻቸውና ድጋሚ ሊደገሙ የማይገባቸውን ልዩነቶቻችንን፣ ተፈጥሯዊ ልዩነቶቻችንን መርጠን ፈልገን ቢሎንግ እንዳደረግንበት በመቁጠር በተሳሳተ መልክ የሚፈጠሩ ዘረኛ አመለካከቶችን፣ በስዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ልዩነቶቻችንን፣ ስልጣን ላይ ባለው አካል እና በስልጣን ጥመኞች የተፈጠሩና የሚቆሰቆሱ ልዩነቶቻችንን፣ ኢትዮጵያ ተበታትና እንደ ደሃ ቁምጣ ሽርጥ መስላ ማየት የሚፈልጉ አካላት የፈጥሯቸው ልዩነቶቻችንን፣ በአጠቃላይ በመቻቻልና በመፋቀር በመተሳሰብና በአንድነት የምናውቃት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የበኩላችን እናበርክት፡፡ እኔ አብቢንም እስካሁንም ሳደርግ እንደነበረው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን እኔንም ጭምር የምችለውን ያህል የሚከፈለውን መስዋዕትነት ከፍየ ለማዳን  በማደርገው ትግል ትንሽ እጣቴን ከትንሽ እጣቴ በማቆላለፍ ቃል ገብቻለው፡፡
ትግሉ የትኛውንም ያህል መስዋዕትነት ሊጠይቅ ቢችልም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ከአንድነታቸውና ከፍቅራቸው ሊበታትናቸው የሚፈልግን ሁሉ ድራሹን እስከማጥፋት ድረስ ለመሄድ ዝግጁ ነኝ፡፡ ይህንን የሚቃወሙ መብታቸው ነው ብየ ማለፍ አልሻም ምክንያቱም ሰው የሚፈልገውን መግለፅ መብቱ ቢሆንም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን አንድ አድርጎ ጠንካራዋን ማለትም በአንድነቷ በኩል የማይደራደሩ አባቶቻችን ያስረከቡንን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረግን ግብ ግብ በተፃራሪው የሚቆምና ፀረ-ኢትዮጵያን፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን እና ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚዘባበት ዝተት አልሻም፡፡
አሁን ኢትዮጵያዊያን ራሳቸውን የሚመረምሩበትና ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን የሚያድኑበት ብቸኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ ትንሽ ብንዘገይ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊያን የለንም፡፡ አትጠራጠሩ የለንም፡፡ ምክንያቱም ጠላት እየቀደመን ነው፡፡ ዳቧችን ሳይበላ እንጅ ከተበላ በኋላማ የኛ ማደንፈቅ የኛ መወራጨት ምን ጥቅም አለው ከመላላጥኛ ከመጋጋጥ ራስን ከመጉዳት ውጭ፡፡ ይህ ነው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ማዳኛ ትክክለኛ ጊዜው፡፡
ይህን ጊዜ ተገንጣይ አስገኝጣዮች ዘረኛ እና በጥቅም ልክፍት የታመሙ ሁሉ መቃብራቸውን እየማሱ ይላፉናል፡፡ የሚምሱት መቃብር ለራሳቸው ብለው ሳይሖን የሚያቅዱት ለኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊያን ነው ነገር ግን ከቀድምናቸው ራሳቸው ሳንገፋቸው ከማሱት ጉድጓድ ውስጥ ይገባሉ ፡፡
ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ህልም ያላደረገ ወደ መቃብር ይገባል፡፡
እኔ አብቢን ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን መቃብር ውስጥ ለማስገባት ጉድጓድ የሚምሱትን በየትኛውም የትግል አቅጣጫ ለመደገፍ ታግሎ ለማታገል ዝግጁ ነኝ፡፡
ይህ ፅሁፍ ለማንም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊያንን ለሚሻ ሁሉ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ የሚነቅፍ ያለምክንያት የሚዘበዝብ ሁሉ ግን ጠላቴ ነው እርም ብያለው ጠላቴ ነው፡፡
በኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነቴና እና ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚመጣብኝ እንትፍ ብያለው ጠላቴ ነው!!!
#አብቢን ንኝ

No comments:

Post a Comment