Monday, June 16, 2014

አማራ ላይ ያለምርጫ ኢህዴግ ተሸንፏል፡፡




ኧረ ስዎች ድፍረት ነው አበ!! የተሰደበን ህዝብ ይቅርታ ሳይጠይቁ ክብርና ቅብጠት ያሰኘዋል እንዴ!! ኢህዴግስ አንድያው ብሽቅ ሆነ፡፡ ገና ሳምንት ሳይሞላው የአማራ ህዝብ ከተሰደበ ትላንት የኢትዮጵያ ስፖርቶች ፌስቲቫል መክፈቻ ፕሮግራም ላይ አስተዋዋቂው
እንዲህ አለች
"እባካችሁን ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፀጥታ ስዎች እየመጡ ስለሆነ ከመቀመጫችን ተነስተን እንቀበላቸው !!"
ብላ በማይክራፎኑ ድብልቅልቅ አድርጋ ስታዲየሙን አናወጠችው
የባህርዳር ህዝብ ግን ሁሉም ባለበት መነሳት ሳይሆን ምላሹ ሁሉም ባለበት እንደተቀመጠ የጠቃውሞ ድምፁን አሰማ፡፡ አስተዋዋቂዋ አሁንም ደግማ እባካችሁን ስትል ለመነች የበለጠ ጩኸትና ተቃውሞ
ስታዲየሙ ድብልቅልቅ አለ
ሁሉም ተቃውሞ ያሰማ የነበረው ታዳሚ የአሰልጣኝ ሰውነት ብሻውን ምስል የያዙ ባነሮችንና መፈክሮችን ብቻ እየጮኹ ይጨፍራሉ፡፡
አሁንም
"በቅርቡ በሞት የተነጠቅናቸውን የኦሮሚያውን ፕሬዚዳንት ለአቶ አለማየው አቶምሳ ለማሰብ ለህሊና ፀሎት አንድ ጊዜ ለአንድ ደቂቃ እናስበው"
አለች ደግማ
ሁሉም በጩኸት አደባለቀው እንደተቀመጠ እንኳንስ በህሊና ፀሎት ሊያስበው፡፡ ለማንኛውም የአማራ ህዝብ አሁንም ኢህዴግ ላይ ያለውን ተቃውሞ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየገለፀ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የአማራ ክልል ህዝብ አንድነት ሁለተኛው ዙር ዪሊዮኖች ድምፅ ላይ ለምን ሰልፍ ከሚደረግበቸው ከተሞች ውስጥ ለምን ባህርዳር አልተካተተችም፡፡ በማለት ሲያጉረመርሙም በአጋጣሚዎች ሁሉና በተገኘው መረጃ መሰረት ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለማንኛውም ኢህዴግ አፍሮ እና የአማራ ህዝብ ምን ያህል  የአገዛዙ እና የኑሮው ጉዳይ እዳንገሸገሸው ገልጧል፡፡ ይህንን ኢህዴግ ልብ የለውም እንጅ ገብቶታል

አማራ ላይ ያለምርጫ ኢህዴግ ተሸንፏል፡፡


በነገራችን ላይ ታማኝ በየነና ንፁህ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን ተለያይተው ያውቃሉን
ምንድን ነው የሁለቱ ሚስጥር በእውኑ ይህን ያህል መታደል አልን!! እስቲ ለማንኛውም ይህን ፍቅር እርሱ ያድለን!!


አንድነት በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ በሚጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሁሉም መስክ የከፋው ህዝብ በርከት በርከትከት ብሎ እንደሚወጣ መረጃዎችና ምንጮች ይጠቁማሉ!! ባለፈው የካቲት ስድስት ላይ ባህርዳር ላይ የተደረገውን ከምርጫ 97 በኋላ በታሪክ የመጀመሪያውና እጅግ በርካታ ህዝብ የወጣበትን ሰላማዊ ሰልፍ ለመብለጥም ከተሞች ውድድር ውስጥ መግባታቸው እንደማይቀርና ይሕም ህዝቡን ከማነሳሳት አንግል እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ እዳለው ምንጮቻችን ገለፁ፡፡
ባህርዳሩ ሰልፍ ላይ ያውም በርካታው ህዝብ የኡራ ኪዳነምህረትን ክብረበዓል ለማክበር ወደ ጣና ገዳማት በሄደበት ሰዓት ቁጥሩ ከ80 እስከ መቶ ሽህ ህዝብ ከጊወርጊስ እስከ ፖሊ ድረስ ያልንም ክፍተት ሲያጥለቀልቀው ያየው የወያኔ ጁንታ ሁሉ በቀጣይ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ብርክ እንደሚይዛቸው ምንም አያጠራጥርም፡፡
ለዚህም ተከታታይ የሆኑ የማጥመድ ዘመቻዎችን መንግስት ሊወስድ እንደሚችል ምንም አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ሰልፈኞችና ህዝቡ ምንም ይሁን ምን እስከፈለገው ድረስ መስዋዕትነቱ ይቀጥል እንጅ ለሃገራችንና ለህዝባችን ለራሴም ስል ለጎረቤቴም ሆነ ለወገኔ በደል ስል መገፋት መራች መቸገር ስል ለዳር ድንበራችን መደፈር ስል መብቴን እና መብታቸውን ለማስከበር ስል ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ባዶ እጄን ያለምንም ጦር መሳሪያ ህሊናየንና አላማየን ታጥቄ እወጣለው እያለ መወያያ ርዕሱ አድርጎታል፡
በመሰረቱ የባህርዳር ህዝ ግን አሁንም ቢሆን ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ በውርቡ እየናፈቀ በመሆኑ አንድነቶች ለዚህ ተገቢውን ምላሽ እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ፡፡
በተሳካ መልኩ የሄደውን የየካቲት ስድስቱን ሰልፍ የማጨናገፍ ያህል ዓላማውን ያለማሳካት ያህል እንደሆነ ይህም ደግሞ እንዲያው ጉዳዮች ተድበስብሰው የህዝቡ ጩኸት የቁራ ጩኸት ብቻ እንዲሆን እንደሚፈልገው ኢህአዴግ/ብአዴን የመሆን ያህል በመሆኑ በቅርቡ ባህርዳር ላይ ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ ያለፉ ጥያቄዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እስኪሆኑ ማለትም ለህዝቡ የሚስማማ ምላሽ አስኪሰጥባቸው ድረስ መቀጠል አለበት፡፡
ነገር ግን ይህ እዲሆን ሌላው ቢቀር እንኳን ለሁለተኛው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ሰላማዊ ሰልፍ መጥሪያ ከተማዎች እቅድ ውስጥ ባህርዳር አለመካተቷ ነዋሪዎችን እያስከፋ ነው የሚገኘው፡፡
ስለዚህ ሌላ አስቸኳይ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራት አለበት ምንም አይነት የሰላማዊ ሰልፉ አለመሳካት የሚያጥራጥር እውነት የለም፡፡ 100 ሽህ የነበረው በእጥፍ ይገኛል፡፡
የባህርዳር ህዝብ ለዓመታት ሰላማዊ ሰልፍ ያንገሸግሸው የነበረው ህዝብ እንዲያ ወጥቶ መታየት በራሱ የሚያመላክተው አንድ እውነት ምንድን ነው፡፡ ህዝቡ መሮታል ብአዴን እና እናት ፓርቲው ኢህዴግን አንቅሮ ተፍቷቸዋል፡፡
ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ተፈቀደም አልተፈቀደ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎችን እዛው ላይ መጥራት ነው፡፡ እናም ባህርዳር ትካተት ነው የህዝቡ ጥያቄ፡፡
ቸር እንሰንብት
ቻው
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

የባህርዳር ህዝብ ጥያቄዎቼ ሳይመለሱ ክበራችን ያጎደፉ የሰደቡን ዳር ድንበራችን አሳልፈው የሰጡ ግለሰቦች ህዝብ ፊት ወይም ፍትህ ፊት ውሳኔ ሳያገኙ አሁነንም ራሳችን ላይ ሲሸኑብን ማየት አንፈቅድም ይላል፡፡
የባህርዳር ህዝብም በእጥፍ ሆኖ እንደሚወጣ እየገለፀ ነው፡፡ ተስፋ አድሮበታል ነገር ግን አንድነቶችን በመውቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ለምንድን ነው ሁለተኛ ሰላማዊ ሰልፍ የማይጠራው
እሽ የተሳደበው ሰውየ አቶ አለምነው መኮንንጉዳይ ምን ላይ ደረሰ በምንም መንገድ ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም!! ያለያም በግልፅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ያን ቀን ሁሉም ለማየት ፈቅዶ/ በአማራ ቴሌቪዥን በፋና ብሮድካስትና ሌሎች በተመረጡ ሚዲያ ተቋማት ብያለው ለዚህም የተከበረው የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያኝ ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለው ማለት አለበት፡፡
ታዲያ ያኝ ያል ድካም ምን አስፈለገ የዝምታ ዝምታማ፡፡
ዳር ድንበራችን አሳልፈው ለሱዳን የሰጡ ስዎች ይጠየቁ ከላይ እስከታች ዳር ድንበራችን ይመለስ መመለሱንም በይፋ ህዝቡ ይወቅ፡፡ በቅርቡ ዶክሜንትሪ ፊልም ለማቅረብ በርካታ የአማራ ክልል ባለስልጣናት እንዲሁም በተዋረድ ያሉ አካላት እና ከሃዲዎች በግዳጅ እና ደጋፊዎችን በማሰባሰብ ምንም ዓይነት መሬት አልተሰጠብም እኛ ድሮም ከያዝነው እርሻ ቦታዎቻችን ላይ ነው ያለን እንዲሉ ለማስገደድና ይህንንም ቀርፆ ለህዝብ እንደተለመደው የውሸት ዶክመንትሪ ፊልም ለመስራት ሄደዋል ፊልሙም እየተሰራ ነው፡፡
ስለዚህ የሚከተሉት ጥያቄዎች እስካልተመለሱና ለመመለሳቸው ለሁሉም የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች ግልባጭ እስካልደረሳቸው ድረስ እንዲሁም በአካል መታየት በሚችል አግባብ ጥያቄዎቹ መመለሳቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ሰላማዊ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም በከፋ መልክ ትግሉ እንደሚቀጥል ነው ህዝቡ እየጠቆመ ያለው፡፡
የህዝብ ጥያቄ አንድ
·         አቶ አለምነው መኮንን ሁለት አማራጭ አለው፡፡ አንድ የሰፊውን አማራን ህዝብና የኢትዮጵያን ህዝብ መበንግስት ሚዲያዎች ኢቲቪን ጨምሮ በይፋ ህዝቡን አጥፍቻለው ለዚህም ይቅርታ ብሎ ማጎንበስ አለበት፡፡ ሁለተኛ እና አንደኛው ካልሆነ ሰውየው ለፍርድ ይቅረብ ውሳኔውም ቢያንስ ቢያንስ ከስልጣኑ ተባርሮ ክምንመ አይነት ሃላፊነቶች እገዳ እንዲጣልበት
·         ለሱዳን የተሰጠው መሬታችን አንድም ካልተሰጠ አለመሰጠቱን በዶክመንትሪ ፊልም ጋጋታ ሳይሆን ከተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች እናንተ ተቃዋሚ ከምትሏቸው ማለት ነው ሁሉ ተመልምሎና ባለሞያዎች ባሉበት ታይቶ ተገምግሞ አዎ መሬታችን ለሱዳን አልተሰጠም የሚል ምላሽ እንዲሰጡን ይደረግ፡፡ መሬቱን ደርግ ወይም ጃንሆይ ናቸው ሊሰጡ የተስማሙ ወይም የተፈራረሙ የምትሉ ከሆነ ደግሞ አንድም እነርሱ ስዕተቱን መስራታቸውን በተጨባጭ ማስረጃ የስምምነት ሰነዶችን በማጋለጥ ህዝቡ ጠላቱን ይወቅ ያለያም ደግሞ የሱዳን መንግስት ከደር መንግስት ጋር ወይም ከጃንሆይ ጋር ተስማምቻለው ሲል የሚያቀርበውን መረጃና ማስረጃ ያቅርብ፡፡ ይህም ሆኖ ግን በምንም መልኩ ሃገር ማለት በስምምነት የምትቆራረጥ የምትበጣጠስ ነዳቦ ስላልሆነች ስምምነት ቢኖርም እንኳን ያለ ኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ ብቻ በመሆኑ ሳይሆን በምንም መንገስ ተቀባይነት ባለመኖሩ ስምምነቱ ተሰርዞ መሬታችን ወደ እኛ መመሆን አለበት፡፡ አስፈላጊ ከሆነም እና የሱዳን መንግስት ወዲህ ዘረጥ ወዲያ ዘረጥ እላለው ኢትዮጵያኝ እወጋለው ካለ የእምየ ኢትዮጵያ ልጆች አለን ለዚህማ፡፡ መከላከያ ሰራዊታችንና ታጣቂ ታጋዮቻችን በዚህ ሰዓት አንድ እደሚሆኑ አያጠራጥም የታሪከ አውነት ስላለው ብቻ ሳይሆን ይህ ከአለም ህዝብ የሚለየን እውነት ነው፡፡ በመሰረቱ መንግስት እንደጭቃ እሾህ የሚፈራቸውን ታጣቂ የኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ አራማጆችን በእጁ ማድረግ ቢፈልግ ይህንን ድንበር ከሱዳን ጋር በመመሳጠር ከመስጠት ይልቅ …አይይይይይይይ ሱዳን!! በዳር ድንበሬ አትምጭብኝ!!!... ገና ለገና ስርዓት ለውጥ ናፋቂ ተቃዋሚ የኢትዮጵያ በረሃ ቤታቸው የሆኑ ውድ ልጆችን እወጋለው አጠፋለው ብየ ዳር ድነበራችን ከምንሰጥማ አንች ጋር ጦርነት ብገጥም ይሻለኛል፡፡ የትም አትደርሽም…
ቢል ጦርነት ካስፈለገም ጦርነት ቢገጠም እነዚህ የስርዓት ለውጥ ናፋቂ ተቃዋሚዎች ታጋዮቻችን ለምሳሌ እንደ አበባ እየጎመራ ያለው ከውድቀት ተነስቶ በርካታ ሽህ ምርጥ ምንም የማይበግረው ጦር ያለው አርበኞች ግንባር ከ80 ሽህ በላይ ነቅነቅ የማይል ጦር ያለው ደምሂት እንዲሁም ለፍትህና እኩልነት፤ በርካታ ጦር ያለው አማራ ፎርስ እንዲሁም የጋምቤላ እና የጉሙዝ ነፃ አውጭ ጦሮች ግልብጥ ብለው ሃገራቸው ገብተው ሱዳንን አሳሯን እንደሚያሳዩዋት አያጠራጥርም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር የጋራ ጦር ድንበር ላይ ለማስቀመጥ ያውም እርሱ ማለትም የኛው ጅል መንግስት በበርካታ መቶ ሽህ ዶላር እየከፈለ ለሚያስተዳድረው የጋራ ጦር ሃይል ደፋ ቀና ማለቱ ሱዳንን እንጅ ኢትዮጵያ ላይ እንደብሄራዊ ጥቅም ሲሰላ ጉዳት አለው ይህ ነው ተብሎ በቀላሉ ሊገለፅ የማይችል የብሄራዊ ጥቅም ኪሳራ አለው፡፡
በመሆኑም መንግስት ይህንን መሬታችን መመለሱን አንድ ኮሚቴ ወይም ሸንጎ በሉት ተቋቁሞ አንድ ሚሊሜትርም እዳልተሰጠ ካላረጋገጠልነ ትላችን ምናልባትም በከፋ መልክ ይቀጥላል፡፡ ይህንን ውሳኔ የትኛውም ተቃዋሚ መደገፍ አለበት፡፡ በምንም ዓይነት ታሪካዊ ወይም የዘመን አመጣሽ ስዕተት ሃገራችን ተቆርሳ ለታሪካዊ ከሃዲ ጠላታችን ሱዳን መሰጠት የለበትም፡፡ በመሰረቱ ይህ መሬት ለሱዳን እንዲሰጥ የሆነባቸው በርካታ ሚስጥራዊ ምክንያቶች ሲኖሩ የተወሰኑትን እንይ
ü  የሱዳን መንግስት የደቡብ ሱዳንን መገንጠል አይፈልግም በተፈጥሮ ጋዝና በተለያዩ ማዕድናት የበለፀገ አካባቢ በመሆኑ ስለዚህም ነው ሰሜን ሱዳን ወይም ሱዳን የደቡብ ሱዳን የታጠቁ የሳልቫኪር ተቃዋሚዎችን የመተረተችው ከሳልቫኪር መንግስት ጋር በተራ የግለሰቦች እልህ እና የብሄራዊ ጥቅም ግጭትን ምክንያት በማድረግ፡፡
ይህኔ ታዲያ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ታጣቂዎችን ሱዳን ጋር በመሆን ጥግም ሰጥታ የምትረዳ የኛይቱ መንግስት ናት፡፡ አስባበት ሳይሆን በስሜት እንዲያው አስቲ እንደአሜሪካ እኔም በሌሎች እጄን ልስደድደ ብላ በማሰብ እንጅ አሁን ራሷን ሳትችል ምን ጥልቅስ አደረጋት አንዱ ይህ ነው
ü  የኛው ጅል መንግስት በመለስ መቀመቅነት እና ሴረኛነት የተጀመረውን የውስጥ ለውስጥ ማለትም ገሃድ ያልወጣ ከኤርትራ ጋር ስምምነት ለመፍጠር መጣር ማስቀጠል የምትችል ሱዳን ብቻ እንደሀኖነች ኢህዴግ ያውቃል፡፡ ስለዚህም የሱዳን ፍላጎት ቢሟላ ኤርትራ ጋር ታደራድረኛለች ቦሎ አሰበ በቀንዱ በአዕምሮው ሳይሆን፡፡ ይህንን ስራ ለመስራትም ሱዳን ሃላፊነቱ ተሰጣት እየጣረችም ነው፡፡ ይህ የኤርትራ ፍላጎት ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አድርጎ አሰብን በእጅ ለማድረግ ከሚል ብልጥ እሳቤ ሳይሆን ኤርትራ የኢህዴግን እንጅ የኢትዮጵያ ጠላት ያልሆኑትን ውድና ብርቅየ ታጋይ ልጆችዋን እንደ ደምሂት አርበኞችና ሌሎችንም በበተለይ ደግሞ እነዚህን አንድ በማድረግ ስራ ላይ እና የጋራ የሰለጠነ ጦር በመገንባት ላይ ያለውን ግንቦት ሰባትን ኤርትራ እንድትበታትንለት ከመሻት ነው፡፡
ü  እኔ እኮ የሚገርመኝ ሱዳን እነዚህን ተቃዋሚዎች እንደምትረዳ እንኳን ጠንቅቆ አያውቅም መንግስት፡፡ ሱዳን ለግብፅ ኢትዮፕያኝ መውጊያ ቦታ በምንም መንገድ እንደምትሰጣት ምንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አደለም፡፡ ሚዲያ ማለት አስበህ ብልጥ ሆነህ ጅሎችን እንደእኛው መሪዎች አይነቶችን የምትሳድበት ቦታ ነው፡፡ አሁን ሱዳን ግብፅ የያዘችውን አቋም ባለመደገፍ ላይ ናት ግን በታሪካዊ እውነታ ሱዳን አባይ እንዲገደብ ትፈልጋለች፡፡ አትፈልግም ለዚህም ታሪካዊ እውነታዎችን ማየት በቂ ነው ለምሳሌ የ1929ኙንና የ1959ኙን ስምምነት እንደስምምነት ብቻ ሳይሆን ማየት በቂ የሚሆነው የስምምነቶቻቸው ጭብጦችና ፎርማልም ሆነ ፎርማል ያልሆነው ምክንያቶቻቸው ምንድን ናቸው የሚለውን ስናይ…በትልቁና በትልቁ የሚሰመርበት ጉዳይ የአረቡ ዓለም ጠንካራና በራሷ ምሰሶ የምትንቀሳቀስ ኢትዮጵያ አንድነቷ የጠነከረ ኢትዮጵያን ማየት አይፈልጉም…ሱዳን እና ግብፅ ማለት ደግሞ የአፍሪካዊ አረብ ክንፍ ቁልፍ ሃገራት ናቸው፡፡
ü  ከዚህ በተጨማሪ ሱዳን የግድቡአስመሳይ ደጋፊ ግን እውነተኛ ሰላይ ናት፡፡ ይህንን ሰለለችውን እውነታ መጨረሻ ማሰብ በቂ ነው፡፡ አሁን ከላይኛውም ይሁን ከታችኛው ናይል ተፋሰስ ሃገራት መካከል በብልጠት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ግብፅና ሱዳን ብቻ ናቸው ሌላው እንኩቶ ነው፡፡ ሱዳን ቂጥዋን ገጥማ ሁኔታዎችን ስትከታተል ግብፅ ደግሞ ጦሯን የሰበቀች አሁን መጣሑ አሁን ፈጨኋችሁ እያለች ሌላኛውን ግን ለሱዳንና ለራሷ የሚሆናትን ስትራቴጅ ታመቻቻለች፡፡ ይህንን የኛው ጅል መንግስት ያቃል ብንል አልባነነም ነው መልሱ፡፡ ሱዳን ልትክደው እንደምትችል ብቻ ግን ገምቷል የኛው ማለቴ ነው፡፡ ግን ቢባንንም መሬታችን ለበርካታ መቶ ዓመታት ሳይሆን ሽህ ዓመታት አስከብረን የኖርነውን ዳርድንበራችን አሳልፎ በመስጠት መሸንገል ፈለገ፡፡ አይ ሱዳን መታደሏ ሁለቴ ባላሰበችው ባልጠበቀችው መልክ ተጠቃሚ ሆነች፡፡ በለስ ቀናት ሎቶሪ ነው አቦ ለሱዳን፡፡  እንጅ የተንሰፈሰፍንለትን ደማችን ልንገብር የተነሳንለትን የአባይ ግድባችን ሱዳን እስከመጨረሻዋ ደም ጠብታ ድረስ ይቅርና እስከመጨረሻዋ መለያያ ቀን እንኳን አብራን ትዘልቃለች ማለት ዘበት ነው፡፡ እንዴ እንዴት ብሎ አቦ፡፡ የግብፅን ያህል ባይሆንም እኮ አባይ ማለት ለሱዳኖችም የሂወትና ስልጣኔ መሰረታቸው ነው መቸስ ነዳጅ ጠጥተው አያድሩ፡፡
ü  ለሱዳን ሎቶሪ የሆነውን መሬታችንን ደማችንን አጥንታችንን ታሪካችንን ከሰጠን በኋላ ለማልቀስ ካልሆነ ሱዳን እንደምትክደንማ ምን አያተራጥርም፡፡ ሱዳን ማን ከአረቡ ዓለም ውጭ ያለንን ሃገር ነው ታምና ስትኖር የምናውቃት፡፡ በባህሪያቸው ሱዳናዊ ግለሰብን እንኳን ብናው ከአረቡ ዓለም ለኢትዮጵያ ቅድሚያ ይሰጣል ማለት ዘበት ነው፡፡ ለምን ፍግም አንልም፡፡ የማውቃቸውን ያል ነው የምነግራችሁ፡፡ በደንብ አውቃቸዋለው፡፡ ሱዳኖች ከሃዲዎች ሃበሻ ሲያዩ አይናቸው ደም የሚለብስ መሰሪ ደደቦች ናቸው፡፡ እባክህን ብዙ አታስለፍልፈኝ ኢህአዴግ ስማኝ ነው የምለው፡፡ እባክህን አንድ ለማይጠቅሙን መጥቀሙም ይቅርና ለሳምንት እንኳን ለማይታመኑ ባዕዳን የቴወድሮስን ትውልድ ስፍራ የዮሃንስን ቀብር ቦታ አባቶቻችን አጥንት እና ደም አትሽጥብን ልለምንህ ኢህዴግ እባክህን እያነባው ልለምንህ እባክህን ኧረ አንድ ያደረጉን ኧረ ኢትዮጵያን የፈጠሩት እናት አባቶቻችን ምን ይሉ ቢያዩን፡፡  ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ!!
ü  እንዴ ሱዳን እኮ ግብፅ ጋር ከኢትዮጵያ በላይ ታሪካዊውም ይሁን እስካሁኗ እለት ድረስ እጅግ ምዕራባዊያን እንኳን የማይበጥሱት የፖለቲካዊ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊውም ይሁን ባህላዊ ቁርኝት ያላት ከኢትዮጵያ በላይ በሰፊ መሬት ጎረቤት የሆነች ሃገር ናት፡፡ ይህን ማለትም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዝምድና እውነተኛ ሆኖ ቢቀጥል ግብፅ በርካታ ከኢትዮጵያ ከምታገኘው የመሬት ብቻ ጥቅም በብዙ ሚሊዮን እጥፍ ከግብፅ ብቻ እንደምታጣ ታውቃለች፡፡ ግብፅ የአረቡ ባህረሰላጠየ አድራጊ ፈጣሪ ናት እንደምናውቃት ታዲያ ሱዳንን ከገባችበት ገብታ ቢያኝስ ቢያኝስ ከ15 ፐርሰንት በላይ የሱዳንን ኢኮኖሚ የሚያሽመደምድ ስራ መስራት እንደማያቅታት እኛ አውቀን የተውነውን ሱዳን ግን ጠንቅቃ ታውቃለች፡
ü  ይህ ለሱዳን የተሰጠ መሬት ሱዳን ጦሯን ካሰፈረች በኋላ ለማባረር የኢትዮጵያ መንግስት ቢፈልግ እና ሱዳን የኢትዮጵያን ጦር መመከት ቢያቅታት እንኳን ስትራቴጅካሊ ኢትዮጵያን ማስመታት የሚያስችል በመሆኑ ቀጣይ የግብፅ ጦር እንደሚረከበው አያጠራጥርም፡፡ የግብፅ ጦር ቢይዘውስ ምን ያመጣል የምትሉ ከሆነ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን መከላከያና ህዝባችን እህቶቻችንና ወንድሞቻችንስ በጅሉ መንግስታችን ስሕተት ለምን ታሪካዊ ግፍ ይፈፀምባቸዋል ነው ለምን እንደባድመ ያውም በከፋ መልክ ያለምንም ጥቅም ሂወታቸው ታልፋለች ለምን ሂወታችን ያልፋል ነው እንጅ የሚያሸንፈውንማ ታሪካችን ምስክር ነው፡፡ ሱዳን ለግብፅ እንጅ ለሃበሻ ሆና አታውቅም መቸም ልትሆንም አትችልም፡፡ ስለዚህ የኛው ጅል እባክህን መሬታችን ሰጥተህ ለነገ ሞታችን ድግስ አታስደግስብን፡፡ ይህን የኛው ጅል መንግስት ማለትም ስዕተቱን ቢፈፅም የቀረው ይቀራል እንጅ የመጀመሪያዋን ፅዋ የምናጠጣው ወደ ጠላት ከመሄዳችን በፊት እኛው ኢትዮጵያዊያኝ መከላከያ ወታደሮች ነን እያሉ ነው የሚገኙ ሰራዊቱም በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በፊት ለአንድ ጉዳይ ወደ ቴወድሮስ ክፍለ ጦር ጎራ ብየ ነበርና ይህንኑ ነው የሚያረጋግጡት፡፡ ይገርማችኋል መከላከያ ሰራዊታችን አሁን ነገሮች ገብተውት በጣት ከሚቆጠሩት አክራሪ ኢህዴጎች በስተቀር መሬታችን ለምን ለሱዳን ይሰጣል ለምንድን ነው ሱዳንን የምናምን ታሪካዊ ስእተት ቢኖር አፈሙዛችንን ወደ መንግስትና ስልጣን ላይ ወዳሉ ኢትዮፕያዊያን ላይ እናዞራለን ነው የሚሉት፡፡ ይህ ደግሞ አሪፍ ጅምር ነው፡፡ መሪዎቻችን ያላወቁትን እኛ እናውቃለንና ለምን ስልጣንና ሙያ አንቀያየርም ሃይለማርያምና ጀሌዎቹ ይምጡና ይዋጉ እኛ እንሂድና እንምራ እያሉም ይቀልዱ ነበር፡፡
ü  ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ያለው መሬት አካባቢ ስርዓት ለውጥን በሃይል የሚደግፉ ምርጥና የትግል መንገዱ የገባቸው ሃይሎች ጦር አንስተው መንግስትን እየተፈታተኑትና በየቀኑም ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ በማድረስ ላይ ያሉ ሃይሎች ማለትም ታጋዮችን ለማጥፋት የተደረገም ሴራ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በምንም መልኩ ቢሆን ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም መሬቱ ለሱዳን መሰጠቱ ምንድን ነው ተቃዋሚዎች ላይ የሚፈጥረው ጫና ነው የአኔ ጥያቄ ምንም አደለም እኮ፡፡ በቃ ከመተማና ሁመራ ትንሽ ራቅ ብለው በረሃ ውስጥ ነበሩ አሁን ያኛው ወደ ውጭ ሱዳን ሲሄድ እነርሱ ተመቻቸው ወደ ውስጥ ጠጋ አሉ ማለት ነው እንዲያውም የበለጠ ጥቅም፡፡ እሽ በረሃውን ዱሩን ጫካውን ለማቃጠልና ለማጥፋት ከሆነ ይሑን ግን ወዳጄ እነዚህ ታጋዮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ዱሩ ጫካው ጠፋም አልጠፋ ለመንግስት ስልጣን ላይ እስካለ ድረስና ህዝብን መበደሉን እስካላቆመ ድረስ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እስካልመጣ ድረስ የእግር እሳት መሆናቸው በተጠናከረ መልክ ይቀጥላል እንጅ አይገታውም፡፡ ያውም ይብሳል ሆድ የባሰው ይበዛል፡፡ እንዴ ከሶስት ወራት በፊት ጎንደርና ባህርዳር አካባቢ እንዲሁም ወደ ጃዊ አካባቢ አርበኞች ግንባር በርካታ መቶ ወጣቶችን መልምሎ ቤሰፈሩ እየገባ በፈቃዳቸው ሲወስዱ አልሰማሁም ሊል ነው እንዴ ታዲያ ይህ ወጣት ባይከፋው ባይርበው ለምን ሞትን ተሸክሞ ጦርነትን ይመርጣል፡፡ አዎ አንድ ግልፅ ጉዳይ አለ አሁን ተጠቃሚ የሆነ ስርዓቱን ይደግፋል ህሊና ከሌለው ሆዳምም ከሆነ ግን ህሊና ያላቸውማ ቢኖራቸውም ቢደላቸውም ተው ማለታቸውን አያቆሙም፡፡ እናም መንግስት እነዚህን ትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ሃይሎች ለማዳከም ፈልጎ ከሆነ ይህንን ታሪካዊ ስዕተት የፈፀመው ተሳስቷል ይታረም መሬታችን አይስጥብን ትግሉን የበለጠ ያባብሰዋል እንጅ ምንም አይፈይድም፡፡ ይህ ለግብፅ ግን ለጋራ ጠላታችን ምቾት ነው፡፡
·         ሶስተኛው መመለስ የሚገባው ጥያቄያችን ደግሞ አባይ የሁላችንም ነው ይገደብ እንደግፍማለን ግን በአባይ ስም እና ሽፋን ሰባዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከመጣስ ይቁሙ፤
·         አራትኛ የፀረ ሽብር ህጉ ይሰረዝልን ፀረ ሽብር ህጉ የህግ እና ህዝብ ማሸበሪያ እንጅ በትክክል የአሸባሪነት መከላከያ አሸባሪነትን ለማጥፋት ወጣ ህግ አደለም፡፡ በዚህ ህግ ስም ጠቅላላ የኢትዮጵያ መብት ተሟጋቾች ወህኒ ናቸው፡፡ በመሰረቱ ለኢህአዴግ አሸባሪ ማለት ለምብቱና መብታቸው ለሌሎችም ምብት የሚታገል ማንኛውም ለህግ የበላይነት የሚታገል ነው፡፡
ለነገሩ አሁን እኛ ሃገር ላይ ህጎች በራሳቸው ልክ እንደፀረ ሽብር ህጎች አይነት ስለሆኑና ሆን ተብሎ ህዝቡን ቀጥቅጦ አስፈራርቶና በሃይል ለመግዛት የሚወጡ የሚረቀቁ ያለምንም ተቃዋሚ የተቆጣጠረው የጉማሬዎች ስብስብ የሞላውን ፓርላማ ህግ አውጭ በመጠቀም ብቻ አንድ አምባገነን ግለሰብ ያወጣውን ያወረደውን የስልጣን ዕድሜውን የሚያራዝምለትን ስልት ብቻ ህግ እያሉ የሚያወጡና እንተግብር የሚሉ ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ መንግስት በተለይ ህጎቼ ናቸው ይህንን አክብሩ የሚላቸው ሁሉ ምንም አይነት ጥያቄ  እንዳየኘሳ ለምብቱ እንዳይቆም የሚያደርጉ ስለሆኑ ህጎቹ በራሳቸው ህጎች አደሉም፡፡ እደግመዋለው ህጎች አደሉም!!! ህጎች ያልሆኑን ደግሞ የአምባገነኖች ፍላጎት ማስፈፀሚያ የሆኑ የታንክ አፈሙዞች እንጅ ወረቀት ላይ ያሉ መተዳደሪያዎች እንደሆኑ አድርገን አንቀበልም፡፡ ስለዚህ ለታንክ አፈሙዝ ደግሞ ፊቱ ላይ ሆኖ መሞት አለያም ታንኩን ማጋየት ብቻ ነው ያለው አማራጭ ነው የህዝቡ መልስ ደግሞ፡፡
በእምነቶቻችን ጣልቃ አትግቡብን ይህንንም በተግባር በፈለጋችሁት መንገድ አረጋግጡልን እናንተ የ666 ተከታዮች መሆናችሁ ለእኛ ጉዳያችን አደልም፡፡ እኛን ግን ተውውውውውውውውን ነው!!!
ይቀጥላል…

No comments:

Post a Comment