Monday, June 16, 2014

ሰላም በዓለም ሁሉ ይኝገስ ለወገኖቼም ይድረስ…



ሰላም በዓለም ሁሉ ይኝገስ ለወገኖቼም ይድረስ…እኛ ሰላም ወዳድ ህዝቦች ነን…እኛ የፍቅር ስዎች ነን…በጭንቅ ጊዜ የምንገኝ…በክፉ ጊዜ በጎን ቁመን…ክፉን የምናሳልፍ ለወዳጆቻችን ፍፁም የሆንን ለሳውዲአረቢያ ለኩዌትም ህዝብ ለመላው አረብ በጭንቅ ቀን በክፉ ቀን የቆምን…ህዝቦች ነበርን…!!! ነበርን…!!! ነበርን!!!
ሳውዲ አረቢያ የመጀመሪያውን ኢምባሲ ሲመሰርት ነፃነቱን ሲያገኝ የመጀመሪያው ሰው ኢትዮጵያ ነበረች…ዜሮ ዜሮ አንድ የሆነ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ነው ማንም አልነበረም!!!
የወገኖቼን ግፍና በደል ዕድሜ ልኬን ብፅፍ ልገልፀው አልችልም!!!
…እግዜያብሄር መልካም እስኪያመጣልን ድረስ እንትጋ…
አንድ እንሁን ህብረት ይኑረን!!!!! ሰላም ይኑረን ፍቅር ይኑረን!!!
አየህ ወይ እግዜያብሄር አየህልን አላህ!!!!
በመላው ሳውዲ በመላው ኩዌት በአረቦቹ ሃገር!!!
መካ ጅዳ መዲና ኩዌት በያሉበት ሃገር
በያሉበት ምድር በያሉበት ሰፈር
የሃገሬ ልጆች የኢትዮጵያ ልጆች
ታስረው በእግር ብረት በባርነት ቀንበር
ሲሰቃይ ህዝባችን አይተሃል ወይ አላህ
አይተሃል እግዜያብሄር…!!!!;
ቃጠሎውን ችለው
ያለእረፍት ሰርተው
ለሚኖሩት ኑሮ ተዋርደው
ደም ተፍተው…!!!!!
እንዲህ ተሰቃይተው ለበሉት እንጄራ
 ምን በበደሉ ነው ይህ ሁሉ መከራ?!!!!
ህፃን ልጆችና ነፍሰጡር እናቶች
በስቃይ ላይ ያሉ ወንድሞች
እህቶች
ምን ስላረጉ ነው አስቲ ተናገሩ
ኧረ እናነተ ስዎች እስቲ አላህን ፍሩ
እንጄራ ነው እንጅ ካገር ያወጣቸው
ምንም ይሁን ምንም አገር እኮ አላቸው!!!!!!!!!!!!!!!...
ወገን እኮ አላቸው!!!...
በሰላም መጥተዋል በሰላም ሸኟቸው
አገር እንደሌለው ወገን እንደሌለው
አታንገላቷቸው…
የደከሙበትን ንብረት ቀምታችሁ
በረሃብ ውሃ ጥም እያሰቃያችሁ
የህፃናት ለቅሶ የእናቶች ዋይታ
ምንም ሳይመስላችሁ
ስንቱን ኢትዮጵያዊ
ስንቷን ኢትዮጵያዊ
በአጭር አስቀራችሁ
እናንተ ኢትዮጵያዊ ሳውዲ እና ኩዌትም ያላችሁ
በደረሰባችሁ መከራና ችግር
መታሰር  መገደል መገፋት መደፈር
መላው ወገናችሁ ከአንጄት አልቅሰናል
ከአይናችን ደም ዘንቧል
ነደን ተቃጥለናል
በቁጭት ግለናል
አበሻን አትንኩት
ነብያችን ያሉት
ዘመን አለፈና ልጆቻቸው ናዱት
የሆነውን ሁሉ ለማመን ይከብዳል
ለካስ የአባቱን ቃል አደራ ይጠላል
እንግዳ ተቀባይ ነበር ያገሬ ሰው
ግን ማንም …ፈጥኖ ያልደረሰው
የክፉ ቀን ደራሽ አይዞህ ባይ ወዳጅ
እንዴት ይዋረዳል ይከበራል እንጅ
የኢትዮጵያ ልጆች እርቀው መጡ እንጅ እንጀራ ፍለጋ
የሃገሬ ልጆች ርቀው መጡ እጅ እንጄራ ፍለጋ
ያውም ላብ ጠብ አድርገው
ከፍለው ብዙ ዋጋ
ሰላሙን ሃገር ሰላም ለማደፍረስ
ለዘረፋ አልመጡ ወይ ሃገር ለማፍረስ
ስለዚህ አሁንም/2/
የሳውዲ መንግስት የኩዌትም መንግስት
የሳውዲ ስዎች የኩዌትም ስዎች
የለፉበትን ሃብት የወገኖቼን ደም
ከምትቀሟቸው
ለእስር እንግልት ከምትዳርጓቸው
በሰላም መጥተዋል በሰላም ሸኟቸው
ደግሞም እንዳትረሱ እዲህ ተቆርቋሪ ወገን እኮ አላቸው
ደም መላሽ አላቸው
ወገኖች ደም መላሽ አሏቸው!!!!!
አገር እኮ አላቸው
ነግ በኔ ነው አታንገላቷቸው!!!
የሳውዲ ስዎች ጥቂት እስቲ አስቡ
የኩዌትም ስዎች ጥቂት እስቲ አስቡ
እግዜያብሄርን ፍሩ አላህን አክብሩ
ይዘገያል እንጅ በሰፈሩት ቁና አይቀር መሰፈሩ
ለትውልድ የሚቆይ የማይሽር ጠባሳ
በደል አታኑሩ
እንዳያይ ፈጣሪ /3/
በሰው ግፍ አትስሩ!!!!!!!/3/
አባት እኮ አላቸው!!
እናት እኮ አላቸው!!!
ወንድም እኮ አላቸው
እህት እኮ አላቸው
ወገን እኮ አላቸው
በሰላም መጥዋል
በሰላም ሸኟቸው!!!!!!!

No comments:

Post a Comment