Monday, June 16, 2014

ኢህአዴግ ይህ ጉዳይ ጫፍ ላይ አድርስ!!! ያለዚያ የሃገር ልማት ነው የሚቀረው፡፡ ትዕግስታችን ነው የሚቀረው!!




አይ ኢትዮጵያ አይ አንች ሃገር ልጆችሽ በየቦታው እየተበተኑ የማንም ንፍጣም መጫዎቻ ይሑኑ፡፡ ዛሬ አንድ ደምን ትክ አድርጎ ጎናችን የሚገኝ አረብ ሁሉ በሜንጫም በሉት በጎራዴ የሚያስቆርጥ ጉድ አየው፡፡
ጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ዘገባ ቀጣይ የማቀርብ ቢሆንም አንዲት እህታችን ኩየት ውስጥ ለጊዜው ማንነቷን መንገር አያስፈልግም በአረቦች አስገድደው እያስጮኹ እንደ እንሰሳ እንደመሬት እየተጫወቱባት የሚያሣይ ቪዲዮ በጥንቃቄ በምንም መልኩ እንዲሰራጭ ስለማይፈገለግ ለልጅቷ ክብር ሲባል የተሰጠኝን ቪዲዮ አየሁት ይህን አይቶ መንግስት የኩየት መንግስትን ካልጠየቀ ጥያቄያችን በከፋ መልክ ይቀጥላል፡፡
ወገኖቻችን በየቦታው እየታረዱ እየተደፈሩ ተቆራርጠው እየወደቁ ነው፡፡ ባለፈው አንዲት የሲንጋፖር ዜጋ ሳውዲ ውስጥ ብትታሰር የሳውዲ ምንግስት ከገቡበት ገብቶ አሳሪዎቹንና የታሰረችበትን ምክንያት እንዲያቀርብ የሲንጋፖር መንግስት ለዜጎቹ የሚጨነቀው መንግስትማ አስፈታት አስገድዶ፡፡
ኧረ እኛ ለማን አቤት እንበል!!
ይህ ጉዳይ ከሰብአዊ መብት ጥሰት በላይ ነው፡፡ አስገድደው በሚችሉት ቦታ ሁሉ እባካችሁን እያለች እያለቀሰች እየጮኸች ደፈሯት፡፡ ይህን ጉዳይ መንግስት ጫፉን ካላሳየን በተግባር የኩየት መንግስትን ጠይቆ ካላስገደደና ደፋሪዎቹ እርምጃ ካልተወሰደባቸው ህዝቡ የራሱን ውሳኔ የሚወስድ ይመስለኛል እኔም ራሴ ብሆን የራሴን የብቀላ እርምጃ እወስዳለው፡፡
በስሜት አደለም የፃስኩት አስቤበት ነው፡፡
ኢህአዴግ ይህ ጉዳይ ጫፍ ላይ አድርስ!!! ያለዚያ የሃገር ልማት ነው የሚቀረው፡፡ ትዕግስታችን ነው የሚቀረው!!

No comments:

Post a Comment