ይህ ሃውልት በምንም መልኩ ከታሪካዊ
ጠቀሜታው ጉዳቱና ለአንድነታችንም ሆነ ለክብራችን ለአብሮነታችን እጅግ ዘግናኝ የሆነ አደጋ ስላለው መፍረስ አለበት፡፡ ይህን ለመደገፍ
የምንም ብሄር አባል መሆን አያስፈልግም፡፡ አንድነታችን ኢትዮጵያችን ይዘን በፍቅርና በሰላም መኖር ካለብን የጋራ ጠላታችን ወያኔን
አንድ ሆነን በሰከነ መንፈስ መጣል ከፈለግን ይህ ሃውልት መፍረሱ የትግላችን አንዱ አካል ነው፡፡
ይህ ሃውልት የተሰራበት እና
20 ሚሊዮኝ ብር የወጣለት ምክንያት ምንም ሳይሖን መንግስት እያሰጋ ያለው የአማራው እና ኦሮሞው መነጋገር አይዞህ መባባል ከሌሎችም
ክልል ነዋሪዎች ጋር በመሆኑ ይህን ለመበታተን እነዚህን የበርካታ ህዝብ እናት የሆኑትን ሁለቱን ብሄሮች ታሪካዊ ክስተት ስህተትም
ይሁን ትክክል በማንሳት እና በማናቆር ነው፡፡
ስለዚህ ይህንን ወያኔያዊ ሴራ
ማክሸፍ የትግላችን እና አንድነትና ሃገራዊ ፍቅራችን መገለጫ ነው፡፡ አስቡት እስቲ ይህን መስራት ምንድን ነው ጥቅሙ እሽ አማራውና
ኦሮሞው ተናኮሩ እንበል ለአንድ አንዲትን ሃገር አንድነቷ ተጠብቃ መምራት ሚፈልግ መንግስት ምንድን ነው ጥቅሙ?
እርግጥ ነው ምንም አይነት አንድነቷና
ጥንካሬዋ ተጠብቆ በፖለቲካ ነቃ ህብረተሰብ በጤናውና ስነልቦናዊ አቋሙ ጠንካራ የሆነ ማህበረሰብ እንደማይፈልግ መንግስት ስናስበው
የሚያሸልመው ስራ ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያዊያን የሃገራችን
አንድነት ብሄራዊ ጥቅምና የህዝባችን በሰላም ውሎ ማደር የምንናፍቅ ሰላምና ፍቅርን በህዝቦቻችንና ግለሰቦቻችን መካከል የምንናፍቅ
ሁሉ ይህንን ሴራቸውን በትግላችን ካስፈለገም በደምና በአጥንታችን ታግለን ማክሸፍ አለብን፡፡
ስለዚህ ቀጣይ ዘመቻችን መሆን
ያለበት ይሕ ሃውልት ብሄራዊ አንድነታችን ብሎም ሁሉንም ጥቅማችን ይነካልና ያፈርሳልና ሳያፈርሰን መፍረስ አለበት፡፡
በእውን ቀጣይ ትውልድ መልካም
ታሪኮቻችንን ብናወርሰው አይሻልም እንዲህ ርካሽ የሆነ አንድም ጥቅም የሌለው ስራ ሰርቶ ለሚመሩት ህዝብ ከማቅረብ፡፡ ለልዩነታችን
መስፋት መስዋዕ ማቅረብ ማለት ነው ሃሃሃ…
አይ ኢህአዴግየ ይህን በትግላችን
ከጥቅም ውጭ ሲሆን ምን ትሉ ደግሞ፡፡ ለነገሩ እንደነ ገ/ክርስቶስ ደስታ አይነት ውሸታምና ቅሌታም ዘረኛና ከሃዲ ታሪክ ፀሃፊ ነን
ባይ ዜጎች አሏችሁ ታስነግረላችሁ ቀጣይ ምናልባትም የፈጃችኋቸውን ኢህአፓን ምርጥ ልጆች ሃውልት ታሰሩ ይሆን?¡
ይህን ከማድረግ ይልቅ ታሪካዊ
ጠላቶቻችን ደርቡሾች ምርጡን መሪያችን አፄ ዮሃንስን ጭንቅላቱን ቆርጠው የጣሉትን ሃውልት አድርጋችሁ
ለምን ያወጣውን ያህል አውጥታችሁ ለምን አትሰሩትም!
እንደዚህ በተቆረጠ እጅ ያለ ጭንቅላት ሳይሆን የንጉሳችን ጭንቅላት
/ራስ / የያዘ የደርቡሽ ወታደር በቀኝ እጁ የንጉሳችን ማረጃ ቢላ ወይም ጩቤ የያዘ ሱዳናዊ ወታደር ያውም ጀኔራል!!
እባካችሁ ይህን ስሩልን እና ጀግና እንበላችሁ
የአፄ ዮሃንስን ጭንቅላት ቆርጦ የገንዛ ሃገራችን
መሬት ላይ ይዞ የሄደውን ታሪካዊ ጠላታችን ጭንቅላቱን በግራ እጁ በቀኝ እጁ ጩቤ የያዘ ይህንን የሱዳንን ታሪካዊ ስዕተት የሚያሳይ
ሃውልት ሰርታችሁ የኛውን በፍቅራችን ስለምንሰራው… እባካችሁን የአኖሌው ማፋጃችሁ ግን በአስቸኳይ አፍርሱልንና ጀግና እንበላችሁ!!
No comments:
Post a Comment