Monday, June 16, 2014

ጎረምሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳዋ ወያኔ የምትሰራውን ጨርሳችሁ አንብቡና ታዘቡ!




ጎረምሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳሳዋ ወያኔ የምትሰራውን ጨርሳችሁ አንብቡና ታዘቡ!
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ….!!!
አስታውሳለው በ1998 ዓ.ም እ.ኢ.አ መንግስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ አባላትን ለማፍራት ሲሞክር አንድ ጥያቄ ጠይቄ ነበር፡፡ ይሄውም "ለምን መንግስት የግል ባለሃብቱ እጁን ሊሰድባቸው በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈራቸውን የልማት ዘርፎች አይገባባቸውም? ለምን እጁን አጣጥፎ የግሉን ሴክተር ብቻ ይጠብቃል…" ስል
የተሰጠኝ መልስ
"መንግስት የግሉን ዘርፍ ለማበረታት ሲል እጁን መስደድና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ማኮሰስ አይሻም፡፡ ይህማ ከዕዝ ኢኮኖሚ ምኑን ተለየና? መንግስት ምንም አይነት የዕዝ ኢኮኖሚ ስርዓትና ተግባራትን መፈፀም አይፈልግም የምንከተለው ነፃ ኢኮኖሚ ስርዓት ነውና በምንም መልኩ እጁን መስደድ አይፈልግም፡፡ አሁን በመንግስት እጅ ስር ሚገኙ ህዝባዊ ድረጅቶችንም በቅርቡ ፕራይቬታይዝ ያደርጋል ኢቭን ቴሌና መብራት ሃይልን ጨምሮ…ወዘተ"
ነበር ያሉት፡፡ ከዛስ ምን እንደሆነ እራሳችሁ ታውቃላችሁ፡፡
መንግስት ተብየዋ ጎረምሳዋ ኢህአዴግ ቀድሞ የሚያውቀውን የምርጫ ውጤት ምንም አይነት ምርጫ ሳይካሄድ ብቻ ሳይሖን ምንም የምርጫ ዳና ሳይሰማ ቢያውቀውም ተጭበርብሮ ነው የሚለውን ከቀምቶና ያለምርጫ ነው ከሚለው ይመርጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ አምባገነን ስርዓቶች መለያ ባህሪ ነው፡፡ ቢያጭበረብረውም ውስጡ በሚያውቀው መልክ በምርጫ አጭበርብሮም ሆነ ቀምቶ ስልጣኑ የኔ ታግየ አፈር በጥብጬ በበረሃ ተቃጥየ፤ ልሞት ቆርጬ ማንም በከተማ እያውደለደለ እኔ በበረሃ ስጋይ አይዞህ ላላለኝ አላማየን ላልደገፈ፤ ለኢህአፓ ምናምን ርዝራዦችማ እጄን አልሰጥም!! ኤርትራን ለዚህ ያበቃሁበት ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የመገነጣጠል መብት የሰጠሁት እኔ እያለው፤ ህዝብን አይቶት በማያውቀው መልክ አንዱን ካንዱ በማጣመርና በብረት በመበየድና አንዱ አንዱን እንዳያምን የሚያደርግ አንድ ለአንድ ሂሳባዊ ስሌትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለተወዳጁ ህዝባችን በማስተዋወቅ አንዱን ካንዱ አስተሳስረን ማንም ጠላት /ተቃዋሚ ወይም ተቀናቃኝ ፖለቲካል ፓርተዎችን ለማለት ነው/ ዝር እንዳይል በማድረግና ትውልድ ሁሉ የማይረሳው ታሪክን እየሰራሁ እያለው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ መጨረሻውን እያወቅኩት ምርጫ እንዲካሄድ በማድረግ ታሪካዊ ፈጠራን አስተምሬማ… ስንቶችን ለሃገራችን ደህንነት ሲባል በጀግንነት እስር ቤቶቼ ላይ አጉሬ አንዱን ወነድ ተባለ የተወለደበትን ቀን እያስቆተርኩ እያስለቀስኩ ገልብጬ አሳሩን እያሳየው ባለውበትና ማንም ከኔ በላይ ወንድ ባልተወለደበት ሁኔታ ይህችን ሃገር ወደ መካከለኛ ገቢ ሃገራት ተር ለማሰለፍ እየጣርኩ እያለው… ህዝቡን ጫፍ እስከጫፍ አንቀሳቅሼና አዝምቼ ታላቁ ተሃድሶ ግድብን በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥንቃቄ በአንዱና ውዱ መሪ እቅድና ዲዛይን እንዲሁም መሪነት ወደ ተግባር ቀይሬ እያለው፤ የአባይ ግድብን ለማስተዳደርም ራሱን የቻለ ገንዘብ ኖት በማሳተም ይህች ሃገር ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ የተመሳሳይ ኖት መጠን ገላጭ የተለያዩ ገንዘቦችን በማሳተም በታሪክ የመጀመሪያው ሆኜ እያለ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብፅ የተባለችውን ራሷን እንደ አፍሪካ ንጉስ አድርጋና የጥቁር ምድር ዘሮች ሳንሆን እኛ ንፁህ አረቦች ነን እያሉ ጥቁርን እንደሰው የማይቆጥሩ ነጫጭቦችን በመድፈር እና  አቅማቸውን በማየት በኢትዮጵያ ታሪክ የትኛውም መንግስት ያልሞከረውን ድፍረት በማሳየት የዚችን ሃገር ህዝብ ያኮራሁ ሆኜ እያለ…፤ ኧረረረረረረ ስንቱን ልበለው…. ተቃዋሚ ፖለቲካል ፓርቲዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በማስበርከክ እና ወደ እስር ቤት በማጎርና ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ በማስገደድ እና በማስፈረም  በሃገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው መንግስት ሆኘየ እያለ…፤ ደርግና ጃንሆይ ሚኒሊክና ቴወድሮስ ያልሰሩትን አስፋልት ያላመጡትን እስከ ሞባይል ቴክኖሎጅ ድረስ የዘመነውን ቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያቤት እየፈጠርኩ እያለ ፈጥሬም ሳለ፤ እስቲ ማን የቀድሞ መንግስት ይህን ሰራ አጼ ዮሃንስ፣ ቴወድሮስ ሚኒሊክ ሃይለስላሴ ወይስ ደርግ? ታዲያ ልምንድን ነው ምንም አልሰራህም የሚለኝ ህዝቡ?
ሲል ኢህአዴግ ለሕዥቡ ጥያቄ አቀረበ፡፡
ስንት እና ስንት ያየሁበትን ከአፈር ብጥብጦ መጠጣት እስከ አፈር ተቃዋሚዎች ላይ መድፋት የሰራሁበትን፤ ከባዶ ኪስ እስከ ጥቅጥቅ ካዝና ድረስ የሞላሁበትን፤ ወዳጅና ጠላቴን የለየሁበትን፤ ደሃና ሃብታሙ ላይ ያለውን ፍፁም ልዩነት በማየት ስዝናናበት የኖርኩበትን፤ የድሃው ለቅሶ እንደ ሙዚቃ በየጭፈራ ቤቱና እንደሸራተን ባሉ ትልቅ ወጭ በማይጠይቁ ሆቴሎች ላይ እየተዝናናው ለቅሶና ዋይታ የሰማሁበትን፤ ዳቦ ዳቦ ሚል ህዝብ የናፈቀኝን ያህል ናፍቆቴን የተወጣሁበትን፤ በብሄር ልዩነት በዘር በቋንቋወዘተ መለያየት ምክንያት ስዎች ሲፋጁ ሲፎጋገሩ ሲገዳደሉ ሲናከሱ እንደ እንሰሳና ከብት አንዳንድ ጊዜም እንደ ከብት ሲሆኑ በማየት የተዝናናሁበትን መድረክ ጥየማ ወይ ፍንክች…እንዴ ይህ ስልጣን ዘመኔ እኮ ሰንት እና ስንት ሬሳዎች ላይ ተረማምጄ የመጣሁ መሆኔን ቢያውቁ አንድም ፈርተው ቀጣይ አስከሬን እኔ እሆናለው በማለት ያለያም ደግሞ ኢህአዴግ ሊምራቸው እንደማይችል በመገመት ቀጣይ ሬሳቸው የእነርሱ እንደሚሆን በማሰላሰል መቅረት ሲገባቸው የትኛውንም የስልጣን ጥያቄም ይሁን የመብት ጥያቄ ሲያነሱ አለማፈራቸው ትንሽ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ድፍረት ሆኖ እያለ ሙከራ ማድረጋቸውን በእስርና ግርፋት ብቻ እንደተውኳቸው እንኳን መርሳታቸው ተቃዋሚዎች ም ያህል ሞኞች እንደሆኑ መገመት ስላላቃተኝ ስልጣኔን አሁንም ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ… እንዴ ለነሱ ሰጥቼ ይህን ህዝብ ላስቸርሰው አይ ሰው ስልጣን ላይ ወጥቶ ሳያይ ምላሱን ያውለበልባል!!...
እናማ ኢህአዴግየ እንዲህ ገለመሌ እያለች በርካታ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄዎች ስታፍን ስትጎረምስ ቆይታ አሁንም ቢሆን እዚህ ጉርምስናዋ አልወጣችም ገና ምራቋን አልዋጠችም፡፡ ምራቅ መዋጥ መቸም አታውቅም ሁሌም ጎረምሳ ዝም ብላ ትጎረምሳለች ህዝብ ላይ አቦ!!
ለማንኛውም አንድ ትምህርትስ እንኳን ካለት ስርዓቶች ይቅርና እጅግ በጣም ከሚያስፈራወ ስታሊን ጦርና ከጀርመን በርካታ ሃይል ጠንካራ ጦር መፍረስ እንኳን አንድም አልተማረም፡፡ ለማንኛውም ይህች ኢህአዴግ ሚሏት ሰውናት አውሬ ከጉርመምስናዋ ካልታቀበች አንዳች መብረቅ ይውረድብሽ ከማለት ውጭ ምንም አልልልም፡፡
ኢህአዴግ አይን አውጥታ ከምትጎረምስባቸው መስመሮችና አካላት መካከል
1.      የግሉ ፕሬስ ላይ
2.     የከተማው ነዋሪ ላይ
3.     ጦር ሃይሉ ላይ
4.     ህዝቡ ላይ አንድም ድሃው አሁን አሁን ደግሞ ሃብታሞች ላይም
5.     ባለስልጣናት ላይ
6.     መንግስት ሰራተኛው ላይ
7.     የግሉ ባለሃብቶች ላይ ወዘተ…
8.     ሙስሊሙ ማሂብርስበ ላይ
9.     አማራውና ኦሮሞው ላይ ቢያይልም ደቡብና ሶማሌም አልቀረላቸው በቅርብ ጊዜም ለይታ ትኩረት ያደረገችባቸው ብሄሮች አሉ
10.    ተቃዋሚዎች ላይ
11.     ማህበረቅዱሳን እና ቤተእምነቶች ላይ
12.    ጀኔራሎችና ወታደሩ እንዲሁም የፀጥታ አካላት ሁሉም ላይ
ወዘተ…እንዲያው እርሷ የማትጎረምስባቸው ደግሞ ምን ነፃነቱን የሚያውቅ አለና፡፡
የምትጎረምስባቸው መስመሮች ደግሞ
1.      ግብር ቀረጥ ቫት አገልግሎት ክፍያ ወዘተ…
2.     እስር ግርፋት ከአገር ማስወጣት
3.     ማስፈራራት ማሰለል ከስራ ማባረር ሃብትና መሬትን መቀማት ማማረር
4.     ነፃነትን በግለሰብም ይሁን በቡድን መንሳት
5.     የገንዘብ ዋጋ በተለያየ መልኩ እንዲቸምር ማድረግ ሳይሆን ብዙውን ሳያውቁ 49 ፐርሰንቱን ደግሞ እያወቁ የሞኔታሪ ፖሊሲው ላይ አደጋ መፍጠር
6.     የበጀት ፖሊሲውን ማዛባትና የበጀት ጉድለትና የበጀት ትረፈትን ለይቶ ባለማወቅም ይሁን ሆን ብሎ በመስራት ጉድለቱ ወይም ትርፉ ችግር እንዲፈጥር ሳይሆን በሙስና ባላንስ እንዲፈጠር ሲሯሯጡ መኖር
7.     ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እንዲሁም ዘራዊ እና ባህላዊ ሙስናዎችን መስራት
8.     ማግለል
9.     ጭንቅላትን ማለት
10.    ዘር ማፅዳት
11.     ታሪካዊ ስህተቶችን መድገም ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ
12.    የኢትዮጵያ ትክክለኛ ታሪኮችን የሚገልፁ መፅሃፍትን በማጥፋት ለዚህ ትውልድ በሱስ ተጠምዶ ለሃገሩ እንዳያስብ ማድረግ ሳያንሳት በእርሷ ማለትም በኢህአዴግ ዘምን ብቻ የተፃፉ መፅሃፍትን በመጠቀም በተለይ የአማራው ብሄር ላይ ያተኮረ ጥላቻን በሌሎች ወንድምና እህቶቻችን ላይ መዝራትና ማፋጀት ማሰብ…/ማሰብ ነው ግን መቸም አይሳካም/
13.    የትምህርት ፖሊሲውን ማጃጃልና ሞተ ዜጋ እንዲፈራ ማድረግ
14.    በመለሲዝም ርዕዮታለም ብቻ የከሰለና የተከነ ምስጠ-ድባ ትውልድ እዲፈጠር በማድረግ
15.    የህዝብን አቅጣጫ የህዝቡን ልብትርታ በማዳመጥና ህዝቡ የሚነሳባቸውን ለራሷ ማይጎዷትን የአትኩሮት ማስቀየሻ ምክንያቶችን በመመንዘር ህዝቡ ትኩረቱ እንዲበታተን ማድረግ፤
16.   ህገወጥ ግንባታ ህገወጥ ቢዝነስ ገለመሌ በማለት ጠንካራ ደጋፊዎቻቸው ያለሆኑትን ወይም ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ለህዝብና ሃገር ይጠቕማሉ አይጠቅሙም ሳትል ከገበያ ውጭ ማድረግና ወደ እስር ቤቷ ማጋ፤
17.    የተማረውን በማሳመን ሳይሆን ያልተማረውን ወንድምና እህቶቻችን እናትና አባቶቻችን መሸወድና ማንገላታት በቅርቡ አቶ በረከት ስምኦን እንዳሉት ማለት ነው "…ገበሬው በእጃችን ነው…" አደል ያሉት
18.    ጥቁር ዱላ አስለቃሽ ጭስና ና ክላሽንኮቭ በነገራችን ላይ ኢህአዴግየ እኛ ላይ የማትጎረምስበት መንገድ እና ምክንያት መስመር ምንም የለም በጎ እና ምናምን ስሪ አይበሏት እንጅ ለተንኮልማ…
19.    
ለማንኛውም እስቲ የጥረት ቅርንጫፍ መስሪያቤቶችና ህውአቶች ተሰባስበው በቢሊዮኖች ዶላር በማፍሰስ አንድ የኤሌክትሪክ ሃይል ግንባታ ማለትም 371 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ በባሮ ወንዝ ላይ ሊገነቡ ነው አሉ፡፡ ይህ በባሮ ወንዝ ላይ የሚገነባው ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ በአጠቃላይ ወደ 13 ቢሊዮን ብር አካባቢ ሚፈጅ ግድብ ነው አሉ፡፡
ተቋራጮችም የጥረት አጋርና ቅርንጫፍ ድርጅቶች ሲሆኑ ምርቱንም ለውጭ ሃገራት ለመሸጥ አስበዋል፡፡ ትርፉስ?
ለማንኛውም እንግዲህ መንግስታችን ሲለን እንደነበረው የተሃድሶ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ ግድብ ሲሆን በዓለምም መሪ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው በዚህ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ ወጭውም በሃገራችን ደረጃ እጅግ ከፍተኛ የሚባልና ምናልባትም እጅግ የሚገርም መጠን ነው፡፡ በቦንድ መልክ ከህዝቡ መንግስት ከሁለት ዓመታት በኋላ እንዴት ሊመልስ እንደሚችል ማለትም መሰረቱ ሲደመር ወለድ እንዴት ከፍሎ ከየትስ አግንቶ ሊከፍል እንደሚችል ብዙም አያባብልም በገባበት ራሱ ቢወጣ ይሻላል፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን የኔ ጉዳይ ይህ አዲሱ ግድብ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ግድብ ማለትም የባሮ ወንዝ ግድም ወይም ጥረት ግድብ ብንለው ይሻላል 13 ቢሊዮን ብር አካባቢ እንደሚፈጅ ከታወቀ ወጭውን ከተሃድሶ ግድብ ጋር ማወዳደርና ምን ያህ ፌር ነው አደለም የሚለውን መገመት እንችላልን፡፡
አስቡ ምንም ያህል ውስብስብ የሆኑ ቴክኖሎጅዎችን ቢተቀም ውስብስብ ዲዛይን ቢሆን ምንም ያህል የተራቀቀ ቁጥጥር ስርዓት ቢኖረው እና ቢተገበርበት ምንም ያህል ዘመናዊ ቢሆን ቢበዛ 86 ቢሊዮን ቢያንስ ደግሞ ከ65 እስከ 75 ቢሊዮን ብር ይፈጃል፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ምናልባት የፈጀበት ምክንያት ከሶስት ምክንያቶች ነው ብለን ልናተቃልለው እንችላልን፡፡
1.      ከቶፖግራፊው እና ጅኦግራፊካዊ አቀማመጡ አንፃር አስቸጋሪ በመሆኑ
2.     ዘመናዊ እን ውስብስብ የሆኑ ለግድቡ ደህንነት ሲባል ከተጨማመሩ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች አንፃር
3.     የድንገተኛ በጀት ተብሎ 2 ፐርሰንት መያዝ ስላለበት ብለን በርካታ ምክንያቶችን በዚህ አቁማዳ ምክንያቶች  መቋ ጠር እንችላልን፤
ኤኒወይስ ወደ ስሌታችን እንግባ አስቲ የጥረት ባሮ ግድብ ወደ ግል ሙሉ በሙሉ መዞር አለመዞሩን ምንም የተባለ የለም ያም ሆነ ይህ ግን 13 ቢሊዮን ወጭ ይጠይቃል ተብሏል፡፡ ታዲያ ይህ ግድብ ምንም ያህል ውስብስብና ዘመናዊ ቢሆን ቢሆን ከተሃድሶ /ህዳሴ ግድብ ሊበልጥና ሊውሰበሰብ/ አይችልም፡፡
ቶፖግራፊውም ቢሆን የአባይን ያህል ሸለቋማ እና ወጣ ገባ የበዛበት በተራራራ ያበደ አካባቢ አደለም፡፡ ዘመናዊነቱን ብናይም ይህን ያሕል የአባይን ግድብ ሊወዳደር የሚችል አደለም፡፡ የተሃድሶው ግድብ እጅግ ዘመናዊ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ዲዛይኑን የዴዘኑት በ1946 ዓ.ም የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ይገልፃሉ ራሳቸው የቀድሞው እና አሁን ደግሞ ምስላቸው የሚመራው ተቅላያችን አረጋግጠዋል፡፡ በርካቶችም ብለዋል መስክረዋልም፡፡
ከአዋጭነት አንግልም ቢሆን የህዳሴው ግድብ እንደተባለው ከሆነ ወጣለትን ወጭ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስመልሶ ዓለማቀፋዊ ገበያን የማካለሉ አቅም ከፍተኛ እና ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከድህነት ወለል ወ…ለ…ል አድርጎ የሚያወጣ ነው በመባሉ ሊወዳደረው አይችልም፡፡
የህዝብን አቴንሽን ካማስቄር አንግልም ቢሆን ቢታይ የአባይን ያህል ኢትዮጵያን ህዝብ አደለም ከነፃነት ጥያቄው ከቡና መጠጣት እሳቤውም ሊያስቀይሰው የሚችል አሳሳቢ ግድብ አደለም፡፡
ታዲያ የባሮ ግድብ መገንባቱ እና ሃገራችን ላንድ ኦቭ ኤሌክትሪሲቲ ዳም ማድረጉ ሳይከፋ የመገንቢያዋ ብር መጠን በረከተስ?
አስቡት አባይ ግድብ በሁሉም መልክ የተሸለና የተሸለ ጥሬ ሃብት የሚጠይቅ አስቸጋሪ ቶፖግራፊ ላይ የሚገነባ ከሆነ እና ለማጠቃለል ግንባታውን ማክሲመም ኦቭ 86 ቢሊዮን የሚጠይቅ ሆኖ 6000 ሜጋ ዋት የሚያስመርት ከሆነ ይህች 371 ሜጋ ዋት የምታመርተዋ ባሮ "ግድባቸው" እንዴት 13 ቢሊዮን ልትቆረጣጥም ትችላልች ያውም የሃገር ውስጥ ጥሬ ሃብትን በመጠቀሟ የውጭ ምንዛሬ ወጭን መቀነስ እየቻለች፡፡
አስቡት 86ቢሊዮን ወጭ ወጥቶ 6000 ሜ.ዋት ማምረት ከተቻለ በ13 ቢሊዮን ብር ምን ያህል ሜጋ ዋት ማምረት ሚችል ግድብ መገንባት እንችላለን ብለን መጠየቅ እንችላለን ሴትሪስባሪበስሊ ሳይሆን ኢን-ሴትሪስፓሪበስሊ ዊዝ ኖ ቫሪያብል ኖት ኮንሲደርድ፡፡
እሽ አሁን በብርና በሜጋዋት ቫሪያብልስን ብቻ በመውሰድ ለየብቻ እንይ፡፡
የተበጀተ በጀት ለአባይ ግድብ/አንድነት ግድብ/ ብየዋለው=86 ቢሊዮን
ለባሮ ግድብ የሚያስፈልገው /ጥረት ግድብ/ህወሐት ግድብ/ =13 ቢሊዮን
አሁን ለአባይ ግድብ የሚወጣው ወጭ 86 ቢሊዮኑ ስንት የባሮ ግድቦችን ሊያስገነባ ይችላል ብለን እንተይቅ፡፡

ስለዚህ ስናሰላ እናካፍል
86 ቢ/13 ቢ= 6.62
ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ቢያንስ የአባይ ግድብ ወጭ 7 ትንንሽ የባሮ ግድቦችን ሊያስገነባ ይችላል፡፡
ይህ ደግሞ ማለት
የአባይ ግድብ የሚያመነጨውን አንድ ሰባትኛ ያህል የባሮ ግድብ ማመንጨት መቻል አለበት ማለት ነው፡፡ ይህም ቢያንስ ነው እንዲያውም፡፡
ስለዚህ
6000 ሜ.ዋትን ለባሮ ሜጋዋት ማለትም ለ7 ስናካፍል በ13 ቢሊዮን ብር ልንገነባው የምንችለው አንድ ግድብ ሊያመነጨው የሚችለውን ኤሌክትሪክ ሃይል መጠን ማወቅ እንችላልን፡፡
ይህም ማለት
6000/7=817.142 ሜ.ዋት
ስለዚህ በ13 ቢሊዮን ብር አንድ 817.142 ሜጋ ዋት ማምረት ሚችል ግድብ መገንባት እየተቻለ በ13 ቢሊዮን ብር እንዴት 371 ሜጋዋት ብቻ ማምረት ሚችል ግድብ ሊገነባ ታሰበ?
ጥያቄ ነው ጎረምሰዋ ኢህአዴግ፡፡
ኦኬ በብር ተለዋዋጭ እንየው ደግሞ
6000 ሜ.ዋት ማምረት ሚችል ግድብ 86 ቢሊዮን አስፈለገው እና 371 ሜ.ዋት የሚያመርተው ደግሞ 13 ቢሊዮን እናም
እዩዩዩዩዩዩዩ…
6000ሜ.ዋት ሲካፈል በ371 ሜጋዋት=16.17
ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ በ86 ሚሊዮኑ ሂሳብ 16 ምርጥ ምርጥ የባሮ ግድቦችን ማስገንባት ይቻላል እያንዳንዳቸው 371 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት የሚችሉ፡፡
ታዲያ በዚህ መንገድ
86 ቢሊዮን ለ16 ባሮ ግድቦች ስናካፍለው አንድ ትክክለኛ ሂሳብ የተሰራለት እና አዋጭነት ስሌት ተሰላለት ግድብ ሊፈጅ የሚገባውን እናገኛለን፡፡
86ቢሊዮን ሲካፈል ለ16 ባሮዎች=5,375,000,000 birr/one baro dam
ስለዚህ ይህ ሆን ተብሎ ህዝብን ሃብት ሃገርን ሃብት ለመመዝበር እና እንደተለመደው ህዝቡን ራቁቱን ላስቀርት ህወሐት ድርጅቶች ጥረት እስከልጅ ልጆቹ የገቡበት መስመር ስለሆነ እንጅ ይህ የባሮ ግድብ 5,375,000,000 birr ብቻ የሚፈጅ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ታዲያ 13 ቢሊዮን መሆኑ ለጌጥ ነው እንዴ ኢትዮጵያዊያን…?

ሌቦች!!!! ሌቦች!!! ሌቦች!!! ለማንኛውም ዝርዝር ትንታኔውን ጠብቁኝ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልሳለን፡፡
እስቲ ይሕን ጉዳይ ይዘን አራት ጥያቄዎችን ለመመለስና ለማስላት እንጣር
1.      ባለቤቱ ማን ነው ይሕ ሃብት የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት እና ብሄራዊ ሃብት ወይስ የግለል ንብረት
2.     በየትኛው ህግ እና ስርዓት እዲሁም በየትኛው ግልፅ ጨሬታ ነው ይህ ግድብ ትግበራ እና ውል የሚያዘው
3.     ምን ያህል ንዘብ ይፈስበታል ከየት ነው የገንዘቡ ምንጭ ግንባታው ላይ የሚሳተፉት እነማን ናቸው
4.     ፋይናንሻው ትንታኔውና አዋጭነት ደረጃው ከሚፈጀው ወጭ አንግልና አማራጭ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አንፃር ሲወዳደር ኦኬ ከተሃድሶው ግድብ ጋር ሲነፃፀርስ እንዴት ነው ንጥጥሩ




ከወደ ባህረዳር በፖሊስና በህብረተሰቡ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ስዎች ሞተዋል የቆሰሉም አሉ፡፡ ከፖሊስም እንዲሁ የቆሰሉ አሉ፡፡ ተኩሱ ለተከታታይ ሶስት ሰዓታት የተደረገ ሲሆን ህዝቡ ቤታችን ለአምስትና ስድስት ዓመታት ያህል ሰርተን እየኖርንበት ያለ እና ሌላ ተለዋጭ ቤት የሌለን በመሆኑ ወይ ተለዋጭ ቦታና ቤት ስጡን ወይም ደግሞ አመት ባሉን እባካችሁን እንዋል አታፍርሱብን ሌላ መቀመጫ የለንም ብሎ ሲጮህ ማፍረሱን ቀጠለው በፖሊስ እና ሚሊሻ የታጀበው አፍራሽ ከህዝቡ ጋር ግጭት ጀምሮ…የተኩስ እሩምታ ህዝቡ ላይ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡም ምላሽ በመስጠት ሲብሰውም ወንጭፍ በመጠቀም ሴቱም ወንዱም አንድ ላይ ሆነው ትንሽ ትልቅ ሳይል ተማምለው በመውጣት ከፖሊስ ጋር ፖሊስ በጥይት ህዝቡም በድንጋይና ባገኘው ሁሉ ተኩስ ሲለዋወጡ ለሶስት ሰዓታት ቆይተዋል፡፡
በርካቶች ቆስለዋል ከፖሊስም ከህዝቡም፡፡ በኋላም ፖሊስ ህዝቡን ሲያባርር ህዝቡ እደገና ፖሊስን ሲያባርር ከቆዩ በኋላ ህዝብ ፖሊሱን ሁሉ እያባረረ ወደ መሃል ከተማው ቀበሌ አስራ ሶስት ጎፋ አካባቢ ሲደርሱ የመጣው ልዩ ሃይል ህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ለመበተን ቢሞክሩም ሳይችሉ ቀርተው ህዝቡ በአንድ ሆሆሆ ብሎ በመሄድ ልዩ ሃይሎችንም በድንጋይና ጠርሙስ መቀጥቀጥ ይጀምራል፡፡
በዚህ ሰዓት የሞቱና የቆሰሉ በርካታ ናቸው ለጊዜው ቁጥራቸው አልደረሰንም ከባህርዳር ያለው ምንጫችን ሲልክልን ለህዝብ እናደርሳለን፡፡ ፖሊስም ግሬደር በመያዝ ችግሩ ወደተፈተረበት አካባቢ በመሄድ አያሌው ጎበዜ የሚባለውን ሰፈር እስከ ቤት እቃዎቻቸው ድረስ ጠራርጎ በማፈራረስ እና በአካባቢው የሚንቀሳቀስን ወጣት በሙሉ ለቃቅመው በማሰር ላይ ሲሆኑ አልፎ አልፎም የተኩስ ድምፅ ይሰማል፡፡
ፖሊስ ሴቶችንም ወንዶችንም ሽማግሌ ህፃን ሳይል በማሰር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው ወንዶች የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም ሚስቶቻቸው እህት እናቶቻቸው አባት ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ እዛ አካባቢ ያለው ሁሉ ወደ እስር ቤት ተግዟል፡፡ ይህ ተኩስ ልውውጥ ላይ እንደ አይን እማኞች ከሆነ ከበርካታ የባህርዳር ቀበሌዎች የተሰባሰበ ህብረተሰብ የሰፈሩን ስዎች ሲያግዝና ፖሊስን አብሮ ሲያባርር ልዩ ሃይልን ሲያባርር እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ሌላ ቀበሌዎች ይህን ያደረጉበት ምክንያት ሲገለፅም ነግ በኔ እያሉ እንደሆን ታውቋል፡፡ ለጊዜው የአባቱ ስም ያልታወቀ ጨመረ የተባለ ወጣት ግንባሩ ላይ በጥይት ተመትቶ አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ፖሊሶች ቀምተው አስከሬኑን አንሰጥም ማለታቸውም ታውቋል፡፡
ለጊዜው አሁን ትንሽ ጋብ ያለ ቢሆንም አልፎ አልፎ በዚህ ሰዓትም ተኩስ ድምፅ ይሰማል፡፡ እነዚህ አካባቢዎች እና ቀበሌዎች ለፖሊስ ኢፍታዊ ድርጊት አንገዛም ላቤን ጠብ አድርጌ አፈር ቆፍሬ ደክሜ የሰራሁትን ቤት ሲያሰኝህ እየመጣህ ልታፈርሰው አትችለለም ፈቃድ አውጥቼ ስንት ጊዜ በሙሰኛ ባለስልጣናት ተበዝብዠ የሰራሁትን ቤቴን ሌላ መውደቂያ ሳይኞረኝማ አታፈርሰውም ብለው ለበርካታ አመታት ሲደክሙ ቆዩትን ቤት በሌሊት እንደ ሽፍታ የማፍረሻ ትዕዛዝ ሳያሳዩ ለማፍረስ መሞከር ህገወጥነት ሆኖ እያለ የንፁ ሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ የመንግስትን ወሮ በላነትና የፖሊስን ደደብነት የሚያሳይ አሮጋንተነት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የባህርዳር ነዋሪዎች ይሰጣሉ፡፡
ተጨማሪ ዘገባዎችን እንደደረሱን እናደርሳለን፡፡
ለሞቱት ነፍስ ይማር ለቆሰሉትም ቁስላችሁን ውሻ ቁስል ያድርግላችሁ እንላለን፡፡
ይህ ህገወጥ እርምጃ ህዝብ ላይ የሚፈፅም መንግስትን ምን ይሉታል፡፡


በወያኔ ፖሊስ እና ልዩ ሃይል በህዝቡ ላይ በከፈቱት ተኩስ የሞተው ወጣት ጨመረ ስርዓተ ቀብሩ በክብራን ገብርኤል ቤተክርስትያን ለማስፈፀም ወደዛው ምንጫችን ሄዷል ሌሎች ሟቾች ላይ አዲስ ነገር ካለም ከሆስፒታል የሚገኙ ምንጮችን በመጠቀም እናቀርባልን፡፡
ነፍሰ በላዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡ በነገራችን ላይ ገዳዮች ፖሊስ ሆነው እያለ ሚሊሻዎች እንደሆኑ አድርገው በመግለፅ ላይ መሆናቸው ሚሊሻዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡
 ነፍስ ይማር

በባህርዳሩ ግጭት ከወጣት ቸመረ በተጨማሪ አንድ በግ ጠባቂ እረኛ የ13 ዓም ልጅ ሆዱ ላይ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል መግባቱ ይታወቅ ነበር አርፏል፡፡
ነብስ ይማር
መንግስትና ነፍሰበላዎችን ደግሞ ነፍሳችሁን አይማረው

ባለፈው አርብ ዕለት የንፁሃን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት ድጋሚ ሊደገም እንደሚችልም እና ህዝቡም በምንም መንገድ ላቡን ጠብ አድርጎ የሰራውን ቤቱን እንደማያስፈርስ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ፖሊስም ይህ ማፍረስ ስራ ለመስራት መጀመሪያ የህዝቡን መሳሪያ ጠብመንጃ በቁጥጥር ስር ማዋል እንዳለበት በመመካከር ላይ ሲሆን በርካታ ፖሊሶችም ስራቸውን ለመልቀቅ እየተዘጋጁ መሆናቸውና አንድም ከህዝቡ ሁለትም ከመንግስት ምስጋና እንደማይቸራቸው ተራ የፖለቲካ መጠቀሚያ እንደሆኑ በማጉረምረም ላይ ናቸው፡፡
ምልቀቂያ ያስገቡ ፖሊሶች ምሬታቸው ይህ ምስጋና ማጣት አለማጣት ብቻ ሳይሆን ጊዜው ሲፈቅድ የሚተነፍሷቸው ታሪኮችና የመንግስት እግልቶችና ግፎች ያለአንዳች ጥቅም እንዳሉባቸው ለምንጮች ገልፀዋል፡፡
በዚህ ግጭቱ በተነሳበት አካባቢ ከዚህ ቀን በፊት ለበርካታ ጊዜያት ግጭቶች የተካሄዱ ሲሆን በእያንዳንዱ ግጭት የስዎች ሂዎት መቀጠፉንና ፌደራል ፖሊሶችም የህዝቡን ቆራጥነት በመመልከትና ቤቱ ፈርሶ ከሚያይ ለመሞት ዝግጁ የሆነ ህዝብ በማየታቸው ብቻ እጃቸውን እንደማይሰዱና እዛው ልዩ ሃይልና ፖሊስ ከሚሊሻ ጋር ይቻለው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ሚሊሻውም በበኩሉ እዚህ ጥፋት ድጋሚ እጁን እንደማይሰድ በማሳወቁ ሌሎች ሚሊሻዎች ከሌሎች ከተሞችና ገጠሮች እንደሚመጡ ታውቋል፡፡
ምንም ይሁን ምን ግን የዚህን ንፁህ ዜጋ ንብረትና ቤት በግሬደር እየገለበጡ አፈር ማልበስ ከሞት ሞት የማይሻል በመሆኑና ለዚህም ምንም አይነት ካሳም ይሁን ትክ የማይሰጣቸው መሆኑና ቃል ያልተገባ በመሆኑ ሁሉም ቤተሰቦች ሞታቸውን እነደሚመርጡ በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡
በነገራችን ላይ ባለፈው ከግጭቱ መልስ ህዝቡን ለቃቅመው ካሰሩ በኋላ ሊሾ ቤቶችንና ውስጣቸው ውድ ውድ ለባህል ማሳመሪያ ተብለው የገቡ እቃዎችን ለምሳሌ እንደ  ቡፌ ሶፋ እንዲሁም ቴሌቪዝንና ፍሪጅ አይነት ዕቃዎች ቤቱን በሚገለብጠው ግሬደር አፈር ለብሰዋል ነኳኩተዋል ዜጎችም ለችግር ተዳርገዋል መጭው ክረምቱ መሆኑ እንዴት ጠፋው ወይ ይህ አምባገነን መንግስት ሲሉም የተደመጡ አሉ፡፡
አንዲት እናት በዚሁ ቤቷ እንዴት እንደፈረሰ ስትናገር እንዲህ ብላለች
"…እኔ ቡና ተጠርቼ ወደ ጎረቤቴ ቤት አመራሁ…ከዚያም በኋላ አገር ጫታ ብየ ጨዋታየንና ቡናይን ስጠጣ ስሳሳቅ ቆይቼ ወዲያውኑ ጩኸት ሰማሁ…ስዎጣ ያየሁትን ማመን አቃተኝ፡፡ ቤቴን በአራቱም አቅጣጫ ግሬደር ግድግዳውን ይገፈዋል ቆርቆሮው 57 ዚንጎ ነው፡፡ ጣራው ወድቋል…ግድግዳው ቀርሸምሸም ብሎ ወደ መሃል ሁሉም ግድግዳ ወደቀ…እኔ ደንቅጨየ አልጮህኩም…ዝም ብየ ደንግዣለው…አስቡት ቤቴ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከአባቴ ወርሸው ነው የሰራሁት…ውስጡ አዲስ ቡፌ 12 ሽህ ብር ያሰራሁት ሌላ 16ሽህ ብር ያሰራሁት ሶፋ 8 ሽህ ብር የገዛሁት ፍሪጅ እና በጥሬ በር 30 ሽህ ብር ቴሌቪዥን ዲቪዲ ዲሽ እና ዲኮደር ጠፋኝ የባለቤቴም ህጋዊ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማን እንደወሰደው ሳላውቅ ይህ እና ቤቴ ሌላው የሚበላው እና የሚጠጣው ሁሉ ወድሞብኝ አሁን የምወድቅበት አጥቼ ጎረቤት ቤት ነኝ የእነርሱም ይሄው ፈራሽ ነው እየተባለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ በሉን!!! የባህርዳር ህዝብ ኑና አግዙን…"

ሲሉም ጥሬያቸውን በምሬት ገልፀዋል!!
አምባገነኖች በውድቃቸው ዘምን ለህዝብ የማይጠቅምና ባዶ ልማት ይለፍፋሉ…ነገር ግን ከህዝብ ድጋፍ ሌለው መሰረት እንደሌለው ቤት መሆኑን ትንሽ ዘግየት ብሎ ይረዳሉ!!! ይሕ በተዛባ መልክ በመንግስት ቴሌቪዥን የቀረበውን ዜና ሳይሆን እውነተኛውን ሁናቴ የያዘ ቪዲዮ የምንለቅቅ መሆናችን እናሳውቃለን፡፡
ድል ለጭቁኑ ህዝብ!!

በቀጣይ ዙር ምናልባትም ደም መፋሰስን ሊያስከትል የሚችል ግጭት ሊኖር የሚችልበት የባህርዳር ከተማ ቤት ማፍረስ ዘመቻ በዚህ ቀን ይሆናል ተብሎ ባይቆረጥም የት አካባቢ በዚህ ዙር ማፍረስ እንደሚጀመር ታውቋል፡፡
በመሆኑም
1.      ሰባታሚት አካባቢ
2.     ዘንዘልማ
3.     ይባብ አካባቢ
4.     ወራሚት…
ናቸው ምናልባትም ቀደም አያሌው ጎበዜ የሚባለው አካባቢ አሁን ደግሞ አያሌው ቦዘኔ ተብሎ ስሙ የሚጠራው ሰፈር ምናልባት ለሚቀጥለው ሶስተኛው ዙር ሊተላለፍ እንደሚችልና መፍረሱ ግን እንደማይቀር ተረጋግጧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሉም ቀበሌ ነዋሪዎች በምንም መልኩ ላባችን ጠብ አድርገን አፈር ፎግሰን ለአመታት ይዘን ኖርነውን ቤቶቻችን ገንዘባችን አፍስሰን የሰራነውን ንፁህ ንብረታችን አናስነካም ደማችን እዚሁ ጠብ ትላለች እንጅ ብለው እርስ በእርስ እየተነጋገሩ መሆኑንና ለመማማልም አመች ባለመሆኑ በቡድን በቡድን ሆነው እየተነጋገሩ መሆኑን እንዲሁም የሰባታሚትና ይባብ ቀበሌ ነዋሪዎች በጭራሽ አይነኳትም ብለው መወሰናቸውን ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡
አያሌው ጎበዜ አሁን አያሌው ቦዘኔ የሚባለው አካባቢ ደግሞ ለምን ለሶስተኛው ዙር ሊተላለፍ እንደቻለ እና ሌሎች ቀበሌዎችስ ለምን ቶሎ ማፍረስ እንዳስፈለገ ግልፅ ባይደረግም አንዳንድ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣን ግን ሰው እንዳይተባበርና የአንዱ ቀበሌ ወደ ሌላው የሚፈርስ ቀበሌ ሄዶ መንግስት ችግር ፈጣሪ የሚላቸው አናስፈርስም የሚሉ ስዎች ጋር እንዳይተባበሩና ምን አገባኝ እንዲሉ ለማድረግ የተደረገ ሴራ ነው ይላሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን ሰው እንደሚተጋገዝና አንዱ ቀበሌ ከሌላኛው ጋር ሊተጋገዝ እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በዚህም ምክንያት ፖሊስና የፀጥታ አካላት በምን መልክ ማፍረስ እዳለባቸው በመወያየት ላይ ሲሆኑ በርካታ ሚሊሻ አባላትና ፖሊስ ግን ወደ ግርግሩ ማለትም ማፍረስ ስራ እንደማይገቡና መልቀቂያቸውን እንዲቀበሏቸው በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
መንግስት አማራ ክልል ላይ ያጣውን ሙሉ በሙሉ ድጋፍ እንዴት እንደሚያስመልስ በመጣር ላይ ሲሆን ለዚህም እንዲረዳው 22 ባለስልጣናትን በእረፍት ስም ከስልጣናቸው እንዲርቁ በማድረግና ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡


ምነው የእግርኳስ ፌደሬሽኑ ኤርትራን ወደኢትዮጵያ ለማምጣት ከሚያስፈልገው ጥረት በላይ ሰርቢያዊው ጎራን ስቲቫኖቪችን ዋሊያዎቹን እንዲያሰለጥኑ  ለማስፈረም ደከሙ?
ኧረ በማሪያም እንዴ ምነው ይህን ያህል እኮ የህወሐት ጦረኞች በጎ ፈቃዳቸው ሆኖ ቢወያዩ እኮ ሰርቢያዊው ጎራን ስቲቫኖቪችን ለማሳመንና እንዲያሳለጥን ለመቅጠር የፈጁትን ጊዜ ያህል አይፈጅም…
ምናልባት ግን
የህዝቡን አቴንሽን ለማስየስ ይሆን ይህች ጎረምሳ ብልጥ ህወሐትና ጀሌዎቿ እኮ አልተቻሉም!!!!!!!
ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ…LOL

አቦ ይህ ጉዳይ አሁን የኢትዮጵያን ነፃነት ናፋቂ ህዝቦች አያስጨንቀንም…ከመለሳችሁ ሰውነት ቢሻውን መልሱልን ካልፈለጋችሁ የተሸለ ኢትዮጵያዊ ከየትኛውም ፤ብሄር ቋንቋ እምነት ወዘተ…ቅጠሩ ካልፈለጋችሁም ደግሞ
ዲና ሙፍቲ ሲያውደለድልና ሲያወራ ከሚውለው ሁሉ ሚኒስቴር አያም ደግሞ ቢሊቢሊ/እብድ ነው/
ቅጠሩት
አያስጨንቀንም
እኛ ያስጨነቀን ነፃነታችን ብቻ ነነው


ክብራችን አዋርደሃልና መቼም ቢሆን አንረሳህም!!! አማራው ህዝብ የተኛ አንበሳ መሆኑን እያየህ ሊሆን እንደሚችል ማስረዳት አይጠበቅብኝም!!!
አንተ ኮንዶም ሆድ!!
ውሸታም!!! ክብር የለሽ!!!
አለምነው መኮንን
ደደብ!!

በነገራችን ላይ ይህ አቶ አለምነው መኮንን የዘራውን መርዝ የረጨውን ያልተሰማ ሌላ ወንጀልና የአማራውን ህዝብ ከሌላው ብሄር ትዝብት እንዲወድቅ ለማድረግ ሆን ብሎ የተናገረው እንደሆነ… በደንብ ሰምታችሁታል… እንግዲያውስ እንደገና ስሙት…በነገራችን ላይ ቃለመጠይቁ ራሱ ተቆርጦ የተቀጠለ ነው… ይህንንም ለማረጋገጥ ሰውየው
የተባለውን ነገር አላልኩም ብሎ ሲቀጥልና ከማለቱ በፊት ያለውን ልዩነት አዳምጡት በደንብ
"…በስብሰባው ተሳታፊዎች ላይ አዲስ ከመሆናቸው ሊሆን ይችላል ወይም ከምንም አንግል ሊሆን ይችላል…የራሳቸውን ብሄር አማራን ለማለት ነው አማራን ከሌላው ብሄር አብልጦ የማየት… የፆታን እኩልነት መካድ ችግር ነበር…የአማራው ብሄር እንደተጎዳ…እምነት እኩልነት ላይም የአመለካከት ችግር ነበረባቸው…"

ይህን ያለው ለምንድን ነው?
እዛ ቦታ የተሰበሰበው ተሳታፊ ሁሉ አማራ ጋዜጠኞች ደህንነቶች ከሁሉም ብሄር በተለይ ከትግራይ እና አዲስ አበባ…እንዲሁም የክልል ባለስልጣናት ናቸው፡፡ እና የዚህ አባባል ሴራ እና ሌላ ወንጀል የሚሆንበት ምክንያት
"…የራሳቸውን ብሄር አማራን ለማለት ነው አማራን ከሌላው ብሄር አብልጦ የማየት…ችግር አለ!!..."
ለማለት የፈለገበት ምክንያት ህዝብን ሽምጥጥ አድርጎ ለመካድ ብቻ ሳይሆን ይህን ህዝብ ከሌላው ብሄር ዘንድ የሚኖረውን አመለካከት ለማዛባትና
እንዴ አሁንም አማራ ውስጥ እንዲህ አይነት አመለካከት አለ እንዴ
የሚልጥያቄ እንዲነሳ ለማድረግ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ ይህም አንዱ የህወሐት አንዱ አላማ ስለመሆኑ በታሪክና በ23 የግፍ ዘመናት ያየነውና የሰማነው ሁሉ በቂ ነው፡፡
"…የብሄር የሃይማኖት የእምነት እኩልነት መብትን የሚፃረሩ አመለካከቶች ነበራቸው…"
  መርዛሙ አለምነው መኮንን

ይህ ፕሮጀክት ኢንተርሎኪንግ ፕሪነሲፕል ፕሮጀክት ተብሎ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መንገድ በአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ የተቀረፀ ፕሮጀክት ነው፡፡ ከዚህ ፕሮጀክት ጋር ከአምስት አመት በፊት በ2001 ዓ.ም ሌሎች ፕሮጀክቶች ለምሳሌ
ምርት ገበያ ፕሮጀክትና ተያያዥ የባንክ ስራ ፕሮጀክቶች ከ30 በላይ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ለብሄራዊ ባንክ ቀርበው ከጀርባው አንዳች ሃይል አለ እንጅ አንተ ልትሰራው አትችልም ይሕን እና ሌሎች ፋይናንሻል ፕሮጀክቶችን እንዲተገበሩ ማድረግ ፖለቲካዊ ክስረት አለው ተብሎ ልጁ ፈቃድ ሳይሰጠው ቀርቷል፡፡
ለዚህ ተጨባጭ መረጃም አንድ ቀን እንደምናቀርብ ቃል እንገባለን፡፡ ከደህንነት አንግል


"…ድምፁ ጠቆርጦ ቀጥል ሴረኛ ተቃዋሚዎች ስራ እንጅ እኔ ብየ አደለም…ለዚህም ነው ህዝቡ እንዴት የራሱን የሚወደውን ህዝብ አለምነው ሊሳደብ ይችላል እያለ ሲጠይቃቸው አይናቸው የሚፈጠው በትክክልም ቆርጦ ቀጥልነታቸውን ህዝቡ ነቅቶባቸዋላ…!!!..."
ባዶ ጭንቅላቱ አቶ አለምነው መኮንን
ሲል የተሳለቀው አለምነው ደደቡ ባዶ ጭንቅላቱ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ህዝብ አላየም እንዳልል ያኔ ሰልፉ አልተካሄደማ…ኧረ ስዎች በጅል ነው ምንመራ….
ከተቃዋሚዎች ጋር ልዩነት ነጥባችን ብሎ የሚያቀርባቸውን ሃሳቦች በናታችሁ ተመልከቱማ…ስሙማ ልል ነው አቦ!!!
እበት ትል ይወልዳል አለ ባበይ
ባዶ ጭንቅላቱ አቶ አለምነው መኮንን ትል ነገር ነው አቦ!!
ይህንን ከሚዘበዝብ አማራ ህዝብ ሲጣላም የሚያምርበት ሲታረቅም ለይቅርታ ትልቅ ቦታ ያለው ህዝብ አልነበር ለምን በይፋ በቀዳዳው ሚዲያቸው ህዝቡን ይቅርታ አጥፍቻለው ለማለት ፈለኩት እንዲህ ነው ቢል ምን ነበረበት



የሰው ልጅ የሰውን ልጅ መፍራት ሲጀምር ነፃነት ትሸነቆራለች፤ የሰው ልጅ የሰውን ልጅ መድፈር ሲጀምር መብት ይረገጣል፡፡



"ለነገሩ ማወቅ ከሚገባቸው በላይ ያወቁና የእቅድ አጥር የሚዘልሉ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ሐውልት ሊሰራላቸው ይገባል፡፡ ሞት የሚገባው ሞት ሊገባው እውን ካልሆነ በስተቀር በርካታ ሞቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሞት ደግሞ ሳይሞቱ ከሚሞቱት በላይ ክብርና ዘለዓለማዊነት አለው፡፡ ‘…ሃገርን የሚሰራት የህዝብ አንድነት እንጅ ሃገር የህዝብ አንድነትን አይሰራውም፤ አያቆመውም፡፡ ነገር ግን ሃገር ታኖራለች፤ ታስመሰግነዋለች፤ መኖሪያና ሰፈሩ ሆና እውነተኛ ትውልድ ታስተላልፋለች፡፡ እናንተም ሆናችሁ እኔ ደከምን?... ለምን እንደምንሞትም ማወቅ የራሳችን መብት ነው፡፡ ነገር ግን መብታችን የራሳችን ሲሆን፣ ሞታችን ደግሞ በታሪክ የሚኖር ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሕይወት ነው፡፡ ስለዚህ በህይወታችን እንደምንኖር ቁጠሩት እንጅ ሳይሞቱ ከሞቱት ጋር ያለን እንዳይመስላችሁ፡፡ የኛ ሞት ሞታችን ለሚወደው ሁሉ ክብር ነው፤ በዚህም ሞታችን ጣፋጭ ማር እንጅ መራራ ሬት አይምሰላችሁ፡፡' ብሎ የተናገረው ማን ነበር ብቻ ግን ይህ ሞት የሚገባው ሁሉ መሞቱ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከሃገር ብሄራዊ ስሜት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም እንዳለው ነው የሚያሳይ… ሞቶ ህይወት ግን የለም:: በህይወት ነው ሌላ ህይወት ያለው፡፡ ስለዚህ እሜቴ ማንኛውም ለዚህ ኦፕሬሽን ሁሉ አስፈላጊ መስሎ የታየንን ማጥፋትና መገላገል መግደል ሳይሆን በርካታዎቹን ከማዳን አይን ብቻ ነው ማየት ያለብን:: በዚያ ላይ የእኛን ገዳዮች መቀነስም ነው¡"

ናታኒ ንግግሩ ምን ያህል አድማጮቹን ሊያሸማቅቃቸው እንደሚችል የገመተ አይመስልም፡፡ ለናታኒ ሞት ሲተነፍስና ሲኖርባት ለፈጣሪ አንድም ቀን የአገልግሎት ክፍያ ወይም ግብር መክፈልን አንድም ቅፅበት አስቦት የማያውቀውን ያህል ለማንም መሞት አንድም ቅፅበት ተጨንቆም አስቦም አያውቅም፡፡ በዚህም ቅንጣት ታህል የርህራሄ ፍንጣሬ አልጣለበትም፡፡ ለእርሱ ምቹ ጎዳናው ላይ ያገኘውን ሁሉ ያርማል፡፡ በዚህ ባህሪውም ከብልሃ ሰብ እና ሶምሶም ያልተናነሰ ነፍሳትን እንደ ድሃ ቆሎ ቆረጣጥሟል፡፡


ህትመቱ ያላለቀው አንድ የጓደኛየ መፅሃፍ ላይ የተወሰደ
ህትመቱ ያላለቀው አንድ የጓደኛየ መፅሃፍ ላይ የተወሰደ


አታጣልፍ አለች "ጉንቻችሪት"!!!
ሁለት ጠብደሎች ድብድብ ሲገጥሙ እገላግላለው ብየ ገብቼ ጉድ ሆንኩኝ እኮ አቦ…አንድ ጠብደል ያለ እንደጉሬዛ አይኑ የፈጠጠ ኮርማ መጥቶ አልገጠመኝም…ጉድ እኮ ነው፡፡
ተው ብለው ተው ብለው እምብኝ ሲለኝ ቀንዱን ይዤ ወደ እርሻ ወረወርኩት…አሉ እማ እርጥባን፡፡
አቦ በቅርቡ ፍልስፍናና ጣጣው የሚል መፅሃፌ ለህትመት ስለገባ ጉዴ ነው ተረኛ ሳልሆን አልቀርም፡፡ እንግዲህ ምን ይደረጋል መቻል ነው ወይ አታጣልፍ እያሉ፡፡
ሁለተኛው መፅሃፌንም በቅርቡ ለህትመት በፈጣሪ እርዳታ እንደሚበቃ ተስፋ አደርጋለው፡፡ ካልታተመመም ጉዳዩ ነው አቃጥለዋለው ስንት ተስፋ አድርጌ በስፖነሰር ማጣት አንጀቴ እንዲቆረጥማ ዕድል አልሰጠውም ለዳቢሎስ፡፡
ለማንኛውም ድብልቅልቅ ያለ ስሜቴን በተደበላለቀ መልኩ ከዚች ዕለት ጀምሮ ለውድ ጓደኞቼ አቀርባለው፡፡
ኧረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረ…እማማ እርጥባን ወጡ አረረረረረረረ!!! ያማስሉት እንጅ አለች አሉ የማይመለከታት ጎረቤት…ሃሃሃሃሃሃሃ…
በሉ እንብላ
ቻው!!

No comments:

Post a Comment